tgoop.com/hollypoem/10680
Last Update:
#ገጣሚ_ሰለሞን_ሳህለ
#ያችን_ልጅ_ንገርዋት
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሉዋት
አወ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…
ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት
እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኝዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በልዋት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሱዋ ፍቅር እንዴት እንደምሆን
እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል
ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኩዋት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ
እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን
ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…
እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በልዋ
.
.
BY ግጥም ፍቅር ቅኔ
Share with your friend now:
tgoop.com/hollypoem/10680