tgoop.com/hutoffun/927
Create:
Last Update:
Last Update:
📜📜📜📜📜📜📜📜📜📜
በአንድ ወቅት አንዲት የሒሳብ መምህርት የሚከተለውን በሰሌዳ ላይ ጻፈች፦
9×1= 9
9×2= 18
9×3= 21
9×4= 36
9×5= 45
9×6= 54
9×7= 63
9×8= 72
9×9= 81
9×10= 90
ጽፋ እንደጨረሰችም ወደ ተማሪዎቿ ዞራ ስትመለከት ሁሉም እየሳቁባት ነው፣ ሶስተኛውን ስሌት ተሳስታለችና።
ይህን ጊዜ መምህርቷ እንዲህ አለች፦ "ስህተት የጻፍኩት በዐላማ ነው፤ ከነገሩ ጠቃሚ ትምህርትን እንድትወስዱ ስለፈለግሁኝ። ይኸውም፥ በውጪ ያለው ዓለም እንዴት እንደሚቀበላችሁ ታውቁ ዘንድ ነው። 9 ጊዜ ትክክለኛ ነገር እንደጻፍኩ ማየት ትችላላችሁ ይሁንና አንዳችሁም ስለዛ አላበረታታችሁኝም፤ ነገር ግን ሁላችሁም ስለ ሠራሁት አንድ ስህተት ሳቃችሁብኝ፣ ነቀፋችሁኝም።
እናም ለዛሬ የምነግራችሁ ቁም ነገር ይህ ነው።" ብላ መናገር ቀጠለች፤
• ዓለሙ፥ ሚሊዮን መልካም ሥራን ብትሠሩ አያበረታታችሁም ግን አንድ የሠራችሁትን ስህተት ይዞ ይነቅፋችኋል። በዚህ ግን ተስፋ ልትቆርጡ አይገባም። ሁልጊዜም ቢሆን ከሳቅና ከነቀፋ በላይ ወጥታችሁ ቁሙ፣ ጽኑ፣ በርቱም!"
@hutoffun
BY የጥበብ ጎጆ
Share with your friend now:
tgoop.com/hutoffun/927