tgoop.com/ikramsualih/2290
Last Update:
ከዶክቶር ሸይኽ ጀሚል ሀሊም አል ሁሰይኒይ የተላለፈ መልዕክት (አሏህ ይጠብቃቸው)
ምስጋና ለአለማቱ ጌታ አሏህ ይሁን አሏህ በሰይዳችን ሙሀመድ እና ንፁህ ፣ ደጋግ በሆኑ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ሶላትን ያውርድ ፦ በመቀጠል ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ በተከበረው ፣ በተላቀው እና በተባረከው የሂጅራ አመት መጀመሪያ ላይ እኔንም እናንተንም ወደ አሏህ ተውበት እንድናደርግ አስታውሳለው ፤ ሰዎችን ተውበት እንዲያደርጉ እና ወደ አሏህ ፣አሏህን ወደ መታዘዝ ፣ አሏህን ወደ መገዛት እና አሏህን ወደ ማውሳት ፣ ወደ ዲናዊ ዕውቀት እና ዲናዊ ዕውቀትን ተግባር ላይ ወደ ማዋል እንዲመጡ እንድትጠሯቸው አስታውሳቹሀለው።
ይህንን ጠቃሚ ጉዳይም አስታውሳቹሀለው ዲየሪቢይ "ሙጀረባቱ ሷሊሂን" ላይ የጠቀሱት ሲሆን ፦ ከሙሀረም የመጀመሪያው ቀን ላይ አየቱል ኩርሲይ ሶስት መቶ ስልሳ ጊዜ (360) ይቀራል ፡ መጀመሪያቸው ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል) ማለትም ሁሉንም እያንዳንዱን ሲቀራ መጀመሪያ ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል)። እናም (ዲየሪቢይ) እንዲህ ይላሉ ፡ (ይህንን የቀራ) በዛ አመት ከተረገመው ሸይጣን መጠበቂያ ምሽግ ይሆንለታል። እንደዚሁም በውስጡ አሏህ እንጂ ሌላ የማያውቀው ብዙ ጠቃሚ ነገሮች አሉት። ከዛም (አየቱል ኩርስይን ቀርቶ) ሲያበቃ እንዲህ ይላል፡
"اللهمَ يا مُحَوِّلَ الْأَحْوَالْ حَوِّل حَالِي إِلَى أَحْسَنِ الأحوال بِحَوْلِكَ وَقُوَتِكَ يَا عَزيزُ يَا مُتَعَالْ، وَصَلَى الله على سيّدّنا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم".
❮❮❮www.tgoop.com/shamilunkamil❯❯❯
BY Bint habeshy//ቢንት ሀበሽይ
Share with your friend now:
tgoop.com/ikramsualih/2290