tgoop.com/jimmadiocese/6046
Last Update:
የመስቀል ደመራ በዓል ውብ፣ ደማቅና ሃይማኖታዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በጅማ መስቀል አደባባይ እና በሀገረ ስብከቱ ሥር በሚገኙ በሁሉም ወረዳዎችና ከ200 በላይ በሚሆኑ የመስቀል ማክበሪያ ቦታዎች በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁ ተገለጸ።
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜⚜
መስከረም 17 ቀን 2017 ዓ.ም (ጅማ፤ ኢትዮጵያ)
@የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን!!
የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ ሆኖ እንዲከበር ከተረኛው ደብር የጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እና በሀገረ ስብከት ደረጃ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ በሙሉ ማለትም የከተማችን ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፣ የከተማችን ወጣቶች፣ ስታስተባብሩ የነበራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች በተለይም ከክቡር ከንቲባችን አቶ ጣሃ ቀመር ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ፣ ዶፍ ዝናብ ሳይበግራችሁ በዓሉ ደማቅ በሆነ መንገድ እንዲከበር ያደረጋችሁ የጸጥታ ሃይሎችና የከተማችን ነዋሪዎች እንዲሁም የዞን አመራሮችና በየወረዳው ያላችሁ የጸጥታ ኃይሎች በሙሉ በጅማ ሀገረ ስብከት ስም ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በዓሉ በሠላም ተከብሮ መጠናቀቁን አስመልክተው መልእክታቸውን ያስተላለፉት ክቡር መልዐከ ሠላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንደገለጹት በተለይም የጅማ ከተማ አስተዳደር ለበዓሉ መሳካት ከበጀት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ በማድረግ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
BY የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን
Share with your friend now:
tgoop.com/jimmadiocese/6046