tgoop.com/kawgms_portal/168
Last Update:
የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነትን የሚያጣራ ኮሚቴ ወደ ስራ ገብቷል።
------------------------------------------------
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ዶ/ር ኢንጂ.) ትምህርት ለማስጀመር የ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገለፀዋል።
የትምህርት ቤቶችን ዝግጁነት ለ ማረጋገጥ ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጣ ኮሚቴ መዋቀሩን እና ኮሚቴውም ስራዎችን በባለቤትነት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ኮሚቴውም ከጤና ፣ ከትምህርት ፣ ከአስተዳደር ዘርፍ እንዲሁም ከወላጆች የተወጣጡ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለይ ወላጆች በአብላጫው የሚሳተፉበት ነው፡፡
የተዋቀረው ኮሚቴ በሚቀጥሉት 3 ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ቤቶች ያሉበትን ሁኔታ የሚገመግም፣ ከትምህርት ሚኒስቴር የሚላኩ ቁሳቁሶች መድረሳቸውን የሚያጣራ ፣ ሌሎች ድጋፎችን የሚያስተባብር ፣ በትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ግብዕቶች መኖራቸውን የሚመለከት እንዲሁም ትምህርት ቤቱ በአጠቃላይ ትምህርት ማስኬድ የሚችልበት ሁኔታ ላይ ስለመሆኑ ይገመግማል፡፡
የተዋቀረው ኮሚቴ የትምህርት ቤቶችን ነባራዊ ሁኔታ ገምግሞ ውሳኔ ሲያስልፍ ትምህርት ቤቶች የሚከፈቱ ሲሆን ትምህርት ቤቶችን የመክፈት ሁኔታም የሚወሰነው የትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን ለመቀበል የሚያስችል ዝግጁነቱ ሲኖር መሆኑን ተነግሯል፡፡
በግል ትምህርት ቤቶችም የወላጅ ኮሚቴዎች የትምህርት ቤቱ ዝግጁነቱን ካላረጋገጡ እና ካላመኑበት ትምህርት ቤቱ ትምህርት መጀመር እንደማይችል ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
BY KAWGMS
Share with your friend now:
tgoop.com/kawgms_portal/168