tgoop.com/kawgms_portal/182
Last Update:
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሶስት ሰሚስተሮችን ትምህርት ብቻ ይሸፍናል።
---------------------------------
የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ሶስት ሲሚስተሮችን ብቻ ያካተተ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትር ሚኒስቴሩ ጌታሁን መኩሪያ ( ፒ ኤች ዲ) ተናገሩ፡፡
በዚህም መሰረት የ11ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ12 ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር በፈተና አወጣጥ ሄደት ውስጥ የሚካተት ሲሆን በተመሳሳይ የ7ኛ ክፍል ሁለቱም ሲሚስተሮች እና የ8ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሲሚስቴር ብቻ በ8ኛ ክፍል ፈተና ውስጥ የሚካተት ይሆናል።፡
ትምህርት ቤቶችም ያለፉትን ሶስት ሲሚስተሮች ዋና ዋና ነጥቦች ላይ የማካካሻ ትምህርት ለ45 ቀን እንደሚሰጡ ተነግሯል።
ክልላዊ እና ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎችም ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እና አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዛሬው እለትም በአዲስ አበባ የሚገኙ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትምህርት ጀምረዋል፡፡
ያለፈው አመት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የ2012 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ተፈታኞችም ከጥቅምት 16 እስከ 30 2013ዓ.ም ምዝገባ እንደሚካሄድ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡
BY KAWGMS
Share with your friend now:
tgoop.com/kawgms_portal/182