tgoop.com/kedmtochu/2986
Last Update:
ክፍል ፫ ፦
የድሜጥሮስ ጳጳስነት
✍🏾.አስረኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ የሆነው ዮልዮስ ሕዝቡን ሰብስቦ እኔ አርጅቻለው ከእኔ ቀጥሎ የሚሾመውን ምረጡ አለ።እነርሱም አንተ ምረጥልን እኛ ምን እናውቃለን አሉት እርሱም እንግዲያውስ ሁላችንም ሱባዔ እንግባ አለ።ጳጳሱ ሱባዔ እንደገባ መልአኩ ተገልጾለት 3(፫) የወይን ዘለላ ይዞ የሚመጣ አለ እሱን ሹመው ብሎ በራዕይ ነገረው።
✍🏾.ድሜጥሮስም የወይን ዘለላውን ለማስባረክ ይዞ በሚመጣ ሰዓት ጳጳሱ ከባረከለት በኋላ ለህዝቡ ይሄን ነው የምትሾሙት ብሎ ሳይውል ሳያድር አረፈ።"ወንበር ያለ ሹም ሀገር ያለ ዳኛ ከብት ያለ እረኛ አይውልም አያድርምና"ህዝቡም ዮልዮስን ቀብረው ከተመለሱ በኋላ ህዝቡ በግድ ሊቀ ጳጳስ አድርገው ሾሙት።
✍🏾.ድሜጥሮስ ከተሾመ በኋላ ህዝቡን አንተ ሐጢያተኛ ነህ አንተ ሐጢአተኛ አይደለህም ፣አንተ መቁረብ ትችላለህ አንተ አትችልም እያለ ሲገፅሳቸው እርሱን ማማት ጀመሩ።መልአኩም ወርዶ እያሙህ ከሚጎዱ ክብርህን ግለፅላቸው አለው።ለህዝቡም አዋጅ አስነግሮ ሁሉም ሰው አንድ አንድ እንጨት ይዘው እንዲመጡ አዘዘ ካመጡ በኋላ ደመራ ደምሩ አላቸው ከዛም ለኮሱት ከተለኮሰ በኋላ ድሜጥሮስ እስከ ልብሰ ተክህኖው 3 ጊዜ ገብቶ ወጣ ይሄም የ3(፫) ቱ አቅማራት ምሳሌ ነው።እነርሱም፦
~.ንዑስ ቀመር
~.ማዕከላዊ ቀመር
~.አብይ ቀመር ናቸው።
📚.መልአኩም ለድሜጥሮስ ከቀኑ 7(፯)
ሱባዔ በ7(፯),ከሌሊቱ ደግሞ 23(፳፫) ሱባዔ በ7(፯) ግባ ተባለ።
~.7*7=49 ይሆናል በአንድ ሰላሳ ስንገድፈው 19(፲፱) ይሆናል ይሄም የጥንተ መጥቅዕ ምሳሌ አመጣጥ ነው።
~.23*7=121 ይሆናል ይሄም በ5(፭) 30(፴) መግደፍ ነው ከዚህም 11(፲፩) ይቀራል ይሄም የጥንተ አበቅቴ ምሳሌ ይሆናል።
📚.ድሜጥሮስ ሱባዔ የጀመረው ቅዳሜ ነበርና ቅዳሜ 8(፰)የወይን ዘለላ መልአኩ አምጦቶ ሰጠው ይህም የቅዳሜ ተውሳክ(ጭማሪይ) ይሁንህ ሲለው ነው እንደዚህ እያሉ እስከ አርብ 2 ድረስ እየቀነሱ መሄድ ነው።
💪🏾.ክብር ይሄን እውቀት ጠብቀው ላቆዩልን አባቶቻችን ይሁን።
BY የቀደምት ኢትዮጵያውያን ታሪክ እና ጥበብ
Share with your friend now:
tgoop.com/kedmtochu/2986