tgoop.com/kedmtochu/3018
Last Update:
ክፍል ፭፦
📜ባሕረ ሐሳብ📜
✍የባሕረ ሐሳብን ፍቺ ከላይ የተመለከትን ሲሆን ዛሬ የመባጅ ሐመር፣የወንበር፣የጥንተ ዮን እንዲሁም አበቅቴና መጥቅዕ አወጣጥ የምንመለከት ይሆናል።
✍.ዓመተ ፍዳ ማለት ከክርቶስ ልደት በፊት ያለው ሲሆን ይኸውም 5500 ዘመን ነው።
✍ .ዓመተ ምህረት ማለት ከክርስቶስ ወዲህ ያለው ዘመን ነው ይኸውም 2014 ዘመን ነው።
📚.ዓመተ ዓለም = ዓመተ ምህረት + ዓመተ ኩነኔ = 2014+ 5500 =7514
📖.ወንጌላዊው ማን እንደሆነ ለማወቅ፦
~7514 ÷ 4 = 1878 ደርሶ ቀሪ 2 ይሆናል።
~1878 ፦ መጠነ ራብዒት ተብላ ትጠራለች፡፡
~ቀሪው 1 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
~ቀሪው 2 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ
~ቀሪው 3 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ሉቃስ
~ቀሪው 0 ከሆነ ዘመኑ ዘመነ ዮሐንስ ይሆናል።
✍.ስለዚህ ቀሪው 2 ስለሆነ የዘንድሮው ወንጌላዊ ማርቆስ ሲሆን ዘመኑ ዘመነ ማርቆስ ይባላል።
ጥንተ ዮን(ኦን)
~ጥንተ ዮን ማለት መስከረም አንድ የሚውልበት ቀን ማለት ነው፡፡
ጥንተ ኦን= ዓመተ ዓለም + መጠነ ራብዒት÷7(ሰባቱ ዕለታት)
= 7514 + 1878 =9392
= 9392 ÷ 7 = 1341 ቀሪ 5
✍.ከዚህ ቀጥሎ ከቀሪው 5 ላይ 1 እንቀንሳለን ለአለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ ተብሎ 1 ይታተታል(ይቀነሳል) ስለዚህ ከ5-1=4 ይሆናል።
✍.ጥንተ ኦን ከረቡዕ ይጀምራል፦
ቀሪው 1 ከሆነ ረቡዕ
ቀሪው 2 ከሆነ ሐሙስ
ቀሪው 3 ከሆነ ዓርብ
ቀሪው 4 ከሆነ ቅዳሜ
ቀሪው 5 ከሆነ እሁድ
ቀሪው 6 ከሆነ ሰኞ
ቀሪው 7 ከሆነ ማግሰኞ ይሆናል ማለት ነው። በመሆኑም የዘንድሮ 4 ስለሆነ ጥንተ ዮን(የመስከረም መባቻ)ቅዳሜ ይሆናል።
ወንበር
📚.ወንበርን ለማግኘት የአብይ ቀመር የጊዜው መደቡን በእድያው አባዝተን ከዓመተ ዓለሙ ላይ መቀነስ ከዛ በ19 መግደፍ ማለትም፦
~14*532=7448
~7514-7448=66
~65፥19=3 ቀሪ 9
ከቀሪው ላይ ላለፈው መሸኛ ለሚመጣው መቀበያ አንድ እናትታለን ከዛ ወንበርን እናገኛለን።
ወንበር =9 - 1= 8 ይሆናል።
አበቅቴ
📚.አበቅቴ ፦ጥንተ አበቅቴን በወንበር አባዝተን በ30 ገድፈን እናገኛለን።
አበቅቴ = ጥንተ አበቅቴ*ወንበር
11*8=88
88፥30= 2 ደርሶ ቀሪው 28 ሲሆን የዘንድሮ አበቅቴ 28 ይሆናል።
አበቅቴን ለማግኘት ሌላው አማራጭ አበቅቴ እና መጥቅዕ ድምራቸው ከ30 አይበልጡም አያንሱም ስለዚህ አንዱን ካገኘን ከ30 ላይ ቀንሰን ማግኘት ይቻላል። ይህም ማለት የ2013 ዓ.ም አበቅቴ 17 ነበር፤ ስለዚህ 30-17=13 ይሆናል ስለዚህ የ2013 መጥቅዕ 13 ነበር ማለት ነው።
መጥቅዕ
📚.መጥቅዕ፦ ጥንተ መጥቅዕን በወንበር አባዝተን ለ30 በመግደፍ(በማካፈል) እናገኛለን።
መጥቅዕ =ጥንተ መጥቅዕ*ወንበር
19×8 = 152
152 ÷ 30= 5 ቀሪው 2 ስለሆነ መጥቅዕ ዘንድሮ 2 ይሆናል።
መጥቅዕን ለማግኘት ሌላው አማራጭ መጥቅዕን ወይ አበቅቴ ካገኘን ከ30 መቀነስ ነው።
“አበቅቴ ወመጥቅ ክሌሆሙ ኢይበዝሁ እም30 ወኢይኅዱ እም 30 ወትረ ይከዉኑ 30 "አበቅቴ ቢበዛ መጥቅ ቢያንስ መጥቅ ቢበዛ አበቅቴ ቢያንስ ከ30 አይበዙም አያንሱም” ይህም ማለት በሌላ አገላለጽ መጥቅዕና አብቅቴ ተደምረዉ ዉጤቱ ከ30 መብለጥና ማነስ የለበትም፤ ሁሌ 30 ይሆናል፡፡ የዘንድሮዉ ~የ2014 ዓ.ም = 28+2= 30
✍.መጥቅዕ ከ14 በላይ ከሆነ በታህታይ ቀመር በመስከረም ይውላል።
✍.መጥቅዕ ከ14 በታች ከሆነ በላዕላይ ቀመር በጥቅምት ይዉላል።
~መጥቅዕ በመስከረም ቢዉል ጾመ ነነዌ በጥር፣ መጥቅዕ በጥቅምት ቢዉል ጾመ ነነዌ በየካቲት ይብታል።
ስለዚህ በዚህ ዓመት መጥቅዕ 2 ሲሆን ከ14 ያንሳል፤ ስለዚህም መጥቅዕ በጥቅምት ይዉላል።
ስለዚህ የ2014 መጥቅዕ ጥቅምት 2 ነው ሲሆን ዕለተ መጥቅዕ ማግሰኞ ይሆናል፡፡
መባጅ ሐመር
📚.የዕለት ተውሳክን ከላይ ስለተመለከትን ቀጥታ ወደ አወጣጡ እንሄዳለን።
📚.መባጃ ሐመርን ለማግኘት መጥቅዕንና በዓለ መጥቅዕ የዋለበትን ዕለት ተውሳክ መደመር ነው።በዓለ መጥቅዕ የዋለው ጥቅምት ላይ ሆኖ ማግሰኞ ስለሆነ የማግሰኞ ተውሳክ 5 ነው።መባጃ ሐመር= 2+5=7
መባጃ ሐመር ከ30 ስለሚያንስ ራሱ 7 ይያዝና መጥቅዕ በጥቅምት ስለዋለ ጾመ ነነዌ በየካቲት 7 በዕለተ ሰኞ ይውላል ማለት ነው።
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።✝
BY የቀደምት ኢትዮጵያውያን ታሪክ እና ጥበብ
Share with your friend now:
tgoop.com/kedmtochu/3018