Telegram Web
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «🍃ሃናን 🍃 #ክፍል_ያያ_አራት 2⃣4⃣ ...ዩሱፍ የጠየቀኝ ጥያቄ እራስ ምታት ሆነብኝ ምክንያቱም ያኔ ሃላሌ "ልጅሽ ልጄ ነው። ለልጃችንም አባቱ እኔ እንደሆንኩኝ እንጂ ሌላ መሆኑን አንነግረውም" ብሎ ባማረ አነጋገሩ አፅናንቶኝ ነበር በዛ ላይ በሴት ልጆቻችን መሃል ወንድ ልጅ በመኖሩም ደስ ብሎት ነበር ቤታችንም ደምቆ ነበር ውስጤ ከአሳብ ነፃ ስለሆነልኝም ሃላሌን በመካደም በርትቼ ነበር እንደውም ሃላሌ…»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
••○●🍃የሰጠንን ብናውቅ የጎደለን የለም🍃●○••

እግር የሌለው ሰው እያለ በእርግጥ አንተ ጫማ አጣሁ ብለህ ታማርራለህ??

ቢሸጥ መነገጃ መሆን የሚችል ስልክ ይዘህ እየዞርክ ስራ አጣሁ ብለህ ታማርራለህ??

••○●🍃አንድ የወለቀ ጥርስ ለማስተከል🍃●○••

አስከ አስር ሺህ ብር ይፈጃል ታድያ የአንተን 32 ጥርስህን በአስር ሺህ ብር ስታበዛው ምን ያህል ሀብታም እንደሆንክና ስንት ሺህ ብር ተሸክመህ እንደምትዞር ትረዳለህ🤔!!

የጥርስህን ነገርኩህ እንጂ ልብ ብለህ እራስህን ብትፈትሽ የጎደለህ ነገር የሌለህ ሀብታም መሆንህን ትገነዘባለህ!! ምድረ ሀብታም ሁላ😋!!

••○●🍃እዚህ ምድር ላይ እኮ አንተን የሚመስል ሰው የለም🍃●○••

●○•• ወዳጄ!! የራሰህ የብቻ አሻራ ያለህ ልዩ ሰው ነህ፡፡ የራስህ የሆነ ልዩ ተፈጥሮ፡ የራስህ የሆነ የሚናፈቅ ባህሪ ያለህ፡ ድንቅ ችሎታ ያለህ ሰው ነህ!! ሌላው ቢቀር በዚህ ሞት በበዛበት አለም አንተ ግን በሂወት መኖርህ አያስገርምህም😳??

••○●🍃እና ምን ልልህ መሰለህ🍃●○••

ብራዘር?.....ባለህ ነገር እርካ!! ዝም ብለህ አታለቃቅስ!! ያለህን እየቆጠርክ ፈታ በል ልልህ ፈልጌ ነው!!

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንምግዜ ተወዳጅ ከዚህም ከዚያም TUBE የሆነው የናተው ቻናል!
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
••○●🌺 ሃናን 🌺●○••

#ክፍል_ሃያ_አምስት 2⃣5⃣

.."ወንድሜ ያመመህ ለታ ወይኝ ከባድ ችግር የገጠመህ ለታ ከዚ በፊት የሰራኸውን ወንጀሎችህን በማሰብ ከልብህ አልቅሰህ ለጌታህ አላህ ምህረትን ጠይቅ " እጅህን ወደ ቂልባ ( ወደ ላይ) አንሳና ያ....ረብ አውፍ በለኝ" በለው ከልብ በሆነ ተውበት ወደ ጌታህ ተመለስ እመነኝ ያኔ ዳግም ትነሳለህ ጀዲድ ሆነህ ስትገፋ የማትወድቅ ጠንካራ ሰው ትሆናለ ነገራቶችም ሁሉ ገር በገር ይሆንልሃል እመኚኝ እህቴ ምን አልባት ባለፈው ተሳስተሽ ይሆናል ስህተትሽን ለማረም ከተነሳሽ ጌታሽም አላህ ፈፅሞ እንቢ አይልሽም ይደሰትብሻል ወደፊት የሚመጡት ጊዜያትም ያማረ ይሆንልሻል ሁክቲ ስህተት የማይሰራ ሰው የለም ሁሉም የአደም ዘር በሙሉ ተሳሳቾች ነን ትልቁ ስህተት ግን ስህተትን ከሰራን በኃላ ተውበት ሳናደርግ ወደ አሄራ መሄዱ ነው...(አላህ ለሁላችንም እውነተኛ ተውበትን ይወፍቀን አሚን)

...ዩሱፍ የትኛውም ሰው እንደሚሳሳተው ስህተትን ሰርቶ ነበር ያውም ከባድ ስህተት በስህተቱም ልክም ተቀጣ እኔም እንደዛው, ለዩሱፍ ስህተት ምክንያት ሆኜ ነበር እኔም ተቀጣው አላህ ሲወደኝ ከልብ የሆነ ተውበትን ተወፈቅኩኝ ተውበትን አደረኩኝ ይኸው አሁኔን አምሮልኛል...

...ባለቤቴ ለዩሱፍ እንደወለድኩለት እንድነግረው ጠየቀኝ እኔ ግን ቅር ብሎኛል ለዩሱፍ የቱንም ያህል ባዝንለት ልጄን ግን አሳልፌ መስጠት አልፈልግም ልጄ ሁሌም አብሮኝ እንዲሆን እፈልጋለው ልጄ ሁሉ ነገሬ ነው ( ለ በሬ ቀንዱ አይከብደውም ይባል የለ?🤔 ለእናትም ልጆችዋ አይበዙባትም እነሱን ማሳደግ አይከብዳትም ብዙ ልጆች ቢኖራትም በቃኝ አትልም ልጅ አትጠግብም) ስለዚ የተውፊቅን አሳብ አልተቀበልኩትም ።

...ተውፊቅ ግን የሱን አሳብ ወደኔ ለማስተጋባት ብዙ ጣረ እኔም ድርቅ አልኩበት ተውፊቅ ምላሳም ነው ማለት የፍቅር ምላሳም ነው እና ድርቅ ስልበት በፍቅር መያዝ ጀመረ ሲቅለሰለስ ደሞ አያምጣው ነው "ማሽኑኮ እኛው ጋር ነው ከፈለግሽ መንታ አልያም ሲንግል ወንድ ትወልጃለሽ" አለኝ በዚ ጊዜ ሳላስበው ወደ ላይ አለኝ መታጠቢያ ክፍል ገብቼ እንደማስመለስ ብሎኝ ተታጥቤ ወጣው ሁለታችንም ደነገጥን "ምን ሆነሽ ነው?" አለኝ እኔም "አላውቅም እንዲሁ ነው እንደማስመለስ ያለኝ አልኩት" እንደነጋ አኪም ቤት መሄድ አለብን አለኝና ተኛን....

....አዳሩን ሆዴን እያመመኝ ስለነበርና ሃላሌንም ሳስጨንቀው ስለነበር እንደነጋ ወደ ሃኪም ቤት ይዞኝ ሄደ አኪሞቹ አይተውኝ ከጨረሱ በኃላ ፈገግ ብለው "እንክዋን ደስ አላቹ የ 2 ወር እርጉዝ ነሽ" አሉኝ እኔም ባለቤቴም ተደሰትን ባለቤቴ በችኮላ "ፃታውን ልታይልን ትችላለህ?" አለው ዶክተሩም አሁን እንደማይቻልና ከትንሽ ጊዜ በኃላ ተመልሰን እንድንመጣ ነገረን...

...ወደ ቤት እየሄድን ሃላሌ ሊያሳምነኝ ሞከረ ከብዙ ማቅማማት በኃላ ግን ተስማማው ወንዱ ልጄም (ሀሙድ) ቀስ በቀስ ዩሱፍን እየመሰለ መጣት...

..አንድ ቀን ዩሱፍ ጋር ደውለን እቤት እንዲመጣ ጋበዝነው በተባለው ቀን መጣ ፈገግ ብሎ "ዛሬ ስላስታወሳቹኝ ደስ ብሎኛል ምን ተገኝቶ ነው?" አለን ሃላለፀም ፈገግ ብሎ "ቆይ ይደርሳል መጀመሪያ የቀረበውን እንብላ" አለውና ምሳ በላን ከዛ በኻላ ነው ሃላሌ ሁሉ ነገር የነገረው በዚ ጊዜ ዩሱፍ ከደስታ ብዛት የሚይዘውን አጣ መናገር አቃተው ይቆማል ይነሳል ምን አለፋቹ (ሳይቅም መረቀነ😄) በመጨረሻም "ልጄ የታል አምጡልኝ አለ" ሃሙድንም ጠርቼ አገናኘዋቸው...

..የዩሱፍ ደስታ ልዩ ነበር ሁሌም ቀን በቀን ቤት መምጣት ጀመረ ለልጁ ብዙ ነገር ይዞ ይመጣል የሴት ልጆቼም እንደዛው ነገር ግን ቤት ውስጥ ብዙ ነገር መቀየር ተጀመረ በተሌ ሃላሌ መቀያየር ጀመረ የሱ መቀየር ምክንያቱ ደሞ ዩሱፍ ለልጆቻችን የሚያደርገው ከልክ ያለፈ ተግባሩ ነው ከዛም አልፎ ደሞ ብዙ ብር የሚያወጣ የአንገት የእጅና የጆሮ ጌጣጌጦችን ገዝቶ ለኔ በስጦታ መልክ መስጠቱ ነው .. እንደ ድንገት ሳላስበው ነበር የተቀበልኩት ከተቀበልኩት በኃላ ግን ትንሽ ደነገጥኩኝ ለ ሃላሌ ስነግረውም በጣም እንደደበረው ፊቱ ላይ ያስታውቃል ብቻ ሃላሌ ቀዝቀዝ እያለብኝ ነው...

ይቀጥላል...

#ሼር

ይቀላቀሉን👇 ይቀላቀሉን👇
@kezim_kezam @kezim_kezam

For any comment👇
@kezim_kezambot
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «​​••○●🌺 ሃናን 🌺●○•• #ክፍል_ሃያ_አምስት 2⃣5⃣ .."ወንድሜ ያመመህ ለታ ወይኝ ከባድ ችግር የገጠመህ ለታ ከዚ በፊት የሰራኸውን ወንጀሎችህን በማሰብ ከልብህ አልቅሰህ ለጌታህ አላህ ምህረትን ጠይቅ " እጅህን ወደ ቂልባ ( ወደ ላይ) አንሳና ያ....ረብ አውፍ በለኝ" በለው ከልብ በሆነ ተውበት ወደ ጌታህ ተመለስ እመነኝ ያኔ ዳግም ትነሳለህ ጀዲድ ሆነህ ስትገፋ የማትወድቅ ጠንካራ ሰው ትሆናለ…»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
••○●🌿ይቅር የት አባቱ🌿●○••

ፍቅርን ሰጥቼው ለሄደ ገፍትሮ
ልውደድህ እያልኩት አሻፈረኝ ብሎ
የምን መጨነቅ ነው የምንስ ትካዜ
እረሳው የለም ወይ በሂደት በጊዜ
አልለማመጥም ይቅር የት አባቱ
በኔ አልተጀመረም ሰው ወዶ ማጣቱ
እንኳን ይሄን ቀርቶ ስንቱን ረስቻለው
በመታገስማ ስንቱን አልፌያለው

አሁንም ብርቱ ነኝ ልቤ ነው ጠንካራ
ለወደደኝ እንጂ ለጠላኝ ማይራራ
በርግጥ ቢከብደኝም የጠላኝን መጥላት
ብልሁ ልቤ ግን ወሰነ ለመርሳት፡፡

ለወዳጅ ለጓደኛዎ 💌ሼር💌

 ┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗ #ፈጣሪ_ኢትዮጵያንና_ህዝቦቿን_ይባርክ

           ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

🌹▫️🍂ሼር💌 SHARE🍂▫️🌹

   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒🔛@kezim_kezam

       ✣🍂 ከዚህም ከዚያም TUBE🍂
🍃ሃናን🍃

#ክፍል_ክፍል_ሃያ_ስድስት 2⃣6⃣

"ትንሿ ቀዳዳ ትልቁን መርከብ እንደምታሰምጠው ሁሉ ትንሽ ጥፋት ብዙ ችግርና ብዙ ጥፋቶችን ይዞ ይመጣል"

...ሃላሌ ከተኛውበት ቀስቅሶኝ "የማወራሽ ነገር አለኝ" አለኝ ደንግጬ "ምነው በሰላም ነው?" አልኩት "አይ በሰላም አይደለም አንድ አሳብ ላቀርብልሽ ፈልጌ ነው" አለኝ ምንድን ውዴ ልስማዋ" አልኩት እሱም "ሃኒ ምን አልባት የማቀርብልሽ አሳብ ሊደብርሽ ይችላል ነገር ግን ግዴቴ ማቅረብ ስላለብኝ ነው ቤቴን አከብራለው ለቤቴ እለፋለው ቤቴን ለማቆም ሁሉንም አደርጋለው ሁሉንም እችላለው አንቺስ ውዴ?" ብሎ ጠየቀኝ እኔም እንዲ አልኩት "ውዴ አዎ እኔም ለቤቴ ሁሉንም እችላለው ሁሉንም አደርጋለው ግን በዚ ሳት ይህ ሚነሳ ነገር ነበር?" አልኩት ሃላሌም "ቆይ ላነሳልሽ የፈለኩት እሱን አይደለም በቅድሚያ እንድታውቂው ምፈልገው ነገር አለ ሃኒ ላንቺ ሂወቴን አሳልፌ እሰጥሻለው ከራሴም ከልጆቼም በላይ እወድሻለው አንቺ ማለት #ሃዋ_ነሽ_በዚ_አለም_ከሴቶች_አንቺ_ብቻ_ነው_ያለሺኝ ላጣሽ አልፈልግም" ሲለኝ በዚ ጊዜ የልብ ምቴ ጨመረ አቋረጥኩትና ባዘነ ድምፅ "ቆይ ምን አይነት መርዶ ልትነግረኝ ነው? ዳር ዳሩን ማለት ተውና እንቅጩን ንገረኝ" አልኩት እሱም "ሃኒ ለአላህ ብለሽ አሁን በማቀርበው ሃሳብ እንዳትናደጂብኝ ቅርም እንዳይልሽ" አለኝ እኔም እያለቀስኩኝና እየተጨነቅኩኝ "እሺ ምንድን ንገረኝ" አልኩት እሱም "እሺ እነግርሻለው" ብሎኝ አንገቱን አቀረቀረ...

ውድ አንባቢያን (😜እራሴን በደራሲ ሂሳብ አያለው እንዴ😂)
የማስተዋወቂያ ሰአት

"አንዳንዴ ውጥረት ውስጥ እንገባና ከዛ ውጥረት ለመውጣት ፈቺ የመሰለንን ቁልፍ እንሞክራለን ያ ቁልፍ ደሞ ፈቺ መሆኑ ቀርቶ እዛው ይሰበርና ከነ ጭራሹኑ መፈታቱ ቀርቶ ባልሞከርኩት ብለን እንድንፀፀት ያደርገናል" (የምላስ ወለምታ)

ከማስተዋወቂያ በኃላ

..አንገቱን ሲያቀረቅር መጥፎ ነገር ሊናገር እንደሆነ ገባኝና "ንገረኝ አንጂ የምን ማቀርቀር ነው" አልኩት ቀና አለና "ሃኒ ዩሱፍ እዚ ቤት ከመጣ ጀምሮ አንድም ቀን ሰላም ያለው እንቅልሽ ተኝቼ አላውቅም በንዴትና በቅናቻ ስገለባበጥ ነው ማነጋው ስለዚ ሃሙዱን (ልጅሽን) ይዞ ይውጣልኝ በቃ ልጅሽን አሳልፈሽ ስጪው በራሱ ቤት ያሳድገው አይሆንም ካልሽ ደሞ አንቺም ልጅሽን ይዘሽ መውጣት ትችያለሽ" አለኝ እኔም "ተውፊቅ ያልከውን ነገር ታውቆሃል?" አልኩት እሱም "አዎ ሃኒ አስቤበት ነው ያልኩሽ ሁሉ ነገር ካቅሜ በላይ ስለሆነብኝ ነው ለድፍረቴ ይቅርታ አድርጊልኘ" አለኝ በዚ ጊዜ ህልም ላይ ያለሁ መሰለኝ ከተውፊቅ ፈፅሞ የማልጠብቀውን ንግግር ሰማው ልቤ ለሁለት ተከፈለ ልቤ አካባቢ ህመም ተሰማኝ አይኔ ያለማቋረጥ እንባ አፈሰሰች ብቻ ያልጠበኩት ነገር ስለነበር በጣም አዘንኩኝ የኮራሁበትና አላህ ሁሌም እንዲጠብቅልኝ የምማፀነውን ትዳር ዛሬ ያበቃለት መሰለኝ የ ተውፊቅ ንግግር ውስጤን አሳመመው ቅስሜ ተሰበረ።...

...እኔ ለተውፊቅ በሁለቱም አሳብ እንደማልስማማ ነገርኩት ከዩሱፍ ጋር ምንም ግንኙነተ እንደሌለንና መቼምም እንደማይኖረን ላስረዳው ሞከርኩኝ "አትቅና እኔ ያንተው ብቻ ነኝ ይህ የመሰለ ጀነት የሆነውን ትዳሬን ላበላሽ አልፈልግም ሁሌም እታመንልሀለው እመነኝ" ብዬ መለመን ጀመርኩኝ ሃለሌ ግን ፈፅሞ አልተስማማም ከሁለት አንዱን ምረጪ ብሎ አንቆ ያዘኝ ...

ይቀጥላል

#ሼር


ይቀላቀሉን👇 ይቀላቀሉን👇
@kezim_kezam @kezim_kezam

For any comment👇
@kezim_kezambot
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «🍃ሃናን🍃 #ክፍል_ክፍል_ሃያ_ስድስት 2⃣6⃣ "ትንሿ ቀዳዳ ትልቁን መርከብ እንደምታሰምጠው ሁሉ ትንሽ ጥፋት ብዙ ችግርና ብዙ ጥፋቶችን ይዞ ይመጣል" ...ሃላሌ ከተኛውበት ቀስቅሶኝ "የማወራሽ ነገር አለኝ" አለኝ ደንግጬ "ምነው በሰላም ነው?" አልኩት "አይ በሰላም አይደለም አንድ አሳብ ላቀርብልሽ ፈልጌ ነው" አለኝ ምንድን ውዴ ልስማዋ" አልኩት እሱም "ሃኒ ምን አልባት የማቀርብልሽ አሳብ ሊደብርሽ…»
••○●🍃ሂጄ ነበር🍃●○••

ሂጄ ነበር አዎ ፍቅሬንም ገፍቼ
ራሴንም ጥዬ ማነቴን ትቼ

ዛሬ ግን በቅቶኛል በጣም ናፍቀኸኛል
የበደልኩህ በድል ያንገፋግፈኛል

እንዴት እንደመጣው እንዳትጠይቀኝ
ምክንያቱም አንድ ነው ስለምትናፍቀኝ

አንድ የበደለህ ሰው ናፍቀኸኛል ቢልህ
አቃለው አለሜ ፌዝ ነው የሚመስልህ

ስማኝ የምወድህ ጊዜ ስጠኝና
ጥቂት አዳምጠኝ ከልብህ ሁንና

እኔ ተራ ሰው ነኝ ህልሜን ያጠበብኩኝ
ስላለፈው ፍቅር ይቅርታህን ስጠኝ

ይቅር በላኝና ቃልኪዳን ላክልኝ
ጣትህ ከጣቴ ጋር ትቆላለፍልኝ



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ ከዚህም ከዚያም TUBE

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
🍃 ሃናን 🍃

#ክፍል_ሃያ_ሰባት 2⃣7⃣

"...ትዳር ማለት ይህ ነው, ኢማንህን ሲጠብቅልህ፣ ደስተኛ ሲያደርግህ፣ እንደተመኘኸው ቤትህ በሳሊህ ልጆችና በመልካም ሚስትህ ሲደምቅልህ፣ ባልሽ ፍቅር ሲሰጥሽ አክብሮሽና ወዶሽ ከፍ ያለን ደረጃን ሲሰጥሽ... ትዳር ማለት ይህ ነው ኩርፍያ ያለበት አንዱ ሲያኮርፍ ወይም ቅር ሲሰኝ አንዱ ተረድቶ ያበሳጨሽን ነገር ለማወቅ የሚጥርና ለጥፋቱም ይቅርታ የሚጠይቅ, ባጭሩ ትዳር ማለት ይህ ነው የዱንያን ጀነትን ሲያጎናፅፍ, ...ምክንያቱም በትዳር ውስጥ ብዙ ነገር አለና...."

...ህንዶች ምን ይላሉ መሰላቹ अगर किसी जोड़े का तलाक हो जाता है, तो उन्हें कभी भी किसी तीसरे पक्ष में प्रवेश नहीं करना चाहिए। यह बड़ों की जिम्मेदारी है, बड़ों की नहीं। अन्यथा, विवाह समाप्त हो जाएगा। ( ባልና ሚስት ከተጣሉ ሶስተኛ ወገን በጭራሽ መግባት የለበትም ግዴታ መግባት ካለባቸው ሽማግሌዎች እንጂ ሌላ አካል መግባት የለበትም ይህ ካልሆነ ግን ትዳሩ ወደ መፍረስ ይሄዳል )... እውነት ነው በትዳር መሃከል ሌላ ሰው ባይገባ ይመረጣል ከተቻለ እራሳችን ተነጋግረን መፍታት, ከከረረ ግን ሽማግሌዎች እንጂ ጋደኛ፣ ዘመድ ወዘተ አያስፈልጉም..

...ተውፊቅ ያ ከሱ የማይጠበቅን ንግግር ሲናገረኝ በጣም ከብዶኝ ነበር አሳቡን ለማስቀየር አልሞከርኩም ፎጣዬን ይዤ ከተኛሁበት አልጋ ተነስቼ ወደ ሳሎን ወርጄ አረብያ መጅሊሱ ላይ ደገፍ አልኩኝ እውነት ለመናገር በጣም አዝኛለው አንዳንዴ ከልባቹ ስታዝኑ ብዙ መለፍለፍ (ማውራት) አተችሉም አዘናቹን በውስጣቹ ይዛቹ ስለዛ እንድታዝኑ ስላደረጋቹ ነገር በማሰብ ሃዘናችሁን ይበልጥ ታማሙቁታላቹ።

...እኔም እንደዛ ነበር ያረኩት የፈጅር ሰላት እስኪያዝን ድረስ ተውፊቅ የተናገረኝ ነገር እያሰብኩኝ ማልቀሴን ቀጠልኩኝ ( እኔ ሳዝን አንድ የማደርገው ነገር አለ እሱም ከ ጌታዬ ጋር አወራለው ጌታዬን ልክ ጓደኛዬን እንደማወራ አድርጌ አወራዋለው (ክብሩና ፍራቻው እንዳለ ሆኖ) አላህን እጠይቀዋለው "ምኑ ጋር ነው ጥፋቴ? ለምንስ ይህ ሆነ? በትኛውስ ወንጀሌ ነው እየቀጣኸኝ ያለው?" በማለት ብዙ ጥያቄዎችን አቀርባለው ያኔ ማን ጥፋተኛ ማንስ ልክ እንደሆነ ይገለፅልኛል እስቲግፋር አድርጌ እነሳና ሰላቴን እሰግዳለው) ይህ ነው ልማዴ..

...የተውፊቅ ንግግር በጣም ከብዶኝ ስለነበር እኔም ከባድን ውሳኔ ወሰንኩኝ ሶስቱንም ልጆቼን ይዤ ወደ ቤተሰቦቼ ጋር ለመሄድ ወሰንኩኝ እንዳሰብኩትም በጠዋት የልጆቼንና የኔን ልብሶቼን መሰብሰብ ጀመርኩኝ ልጆቼንም ቀሰቀስክዋቸው በችኮላ አለባበስክዋቸውና ሻንጣዬን ይዤ ለመውጣት ተነሳው በዚ ጊዜ ልጆቼ ደንግጠው ማልቀስ ጀመሩ ሃያታቸው ጋር ይዣቸው ልሄድ እንደሆነ ብነግራቸውም ለቅሶአቸው አላቆሙም በዚ ጊዜ ተውፊቅ ለቅሶአቸውን ቀስቅሶት ተነሳ በድንጋጤ " ምንድን የምን ለቅሶ ነው " ብሎ ጠየቀኝ እኔ ግን አኩርፌ ሰልነበር መልስ አልመለስኩለትም በተደጋጋሚ ጠየቀኝ እኔ ዝም እንዳልኩኝ ነው ልጆቹም እጃቸውን ይዤ " ኑ ውጦ ኑ እንሂድ" እያልኩኝ በችኮላ ከቤት ወጣን ተውፊቅ ሁኔታዬ ግራ አጋብቶታል "ወዴት ነው ይዘሻቸው ምትሄጂው? "ሲለኝ እኔም "አይመለከትህም ማታ ያልከው እረሳኽ እንዴ? ውጪልኝ ብለኸኛል በቃ ልጆቼን ይዤ እየወጣሁኝ ነው" አልኩት በዚ ጊዜ ተውፊቅ በጣም ደነገጠ ማታ በተናገረው ነገር እንዳፈረና ይቅርታ ሊጠይቀኝ እንደሚፈልግ ነገረኝ ብዙ ተማፀነኝ እኔ ግን ተውፊቅን የቱንም ያህል ብወደው ማታ በተናገረው ንግግር ውስጤ ቁስል ያዘ ይቅርታውን እንደማልቃበልና ከመንገዴም ዞር እንዲልልኝ ነገርኩት እሱ ግን ይባሱንም እልህ ይዞት እግሬ ላይ በመንበርከክና እግሬን በመያዝ ይቅርታ ጠየቀኝ እኔ ግን አይምሮዬ የሚያስበው የሱ ይቅርታ መጠየቅ ሳይሆን ማታ ስለተናገረኝ ንግግር ነው በንዴት ገፍትሬው መንገዴን ጀመርኩኝ በዚ ጊዜ ተውፊቅ ከወደቀበት ተነስቶ በድጋሚ ፊት ለፊቴ በመቆም አይኑ እንባ አቅሮ ይቅርታ ጠየቀኝ አሁንም ድርቅናዬን አለቅ ብሎኛል በመጨረሻም ባዘነ ድምፅ እንዲ አለኝ

@kezim_kezam

"ሃኒ ብዙ ለመንኩሽ ለማታውም ንግግሬ ይቅርታ ጠየኩሽ ይቅር ግን ልትዪኝ አልቻልሽም ባለፉት ቀናቶችኮ ስለ ይቅርታ አስተምረሺኝ ነበር ዩሱፍ ያ በደል አድርሶብሽ ይቅር ብለሺዋል ታድያ ለምን እኔ ላይ ጨከንሽብኝ? ያውም እግርሽ ላይ ወድቄ እየለመንኩሽ" አለኝ በዚ ጊዜ የያዘኝ ሴጣን ቀስ በቀስ እየለቀቀኝ መጣ ግን አሁንም ቢሆን ይቅርታ ለማረግ ፍላጎቱ የለኝም።

"ሴት ልጅ አድማጭ ነች ከድርጊት በላይ ንግግር ይስባታል በወርቅ ላይ ከምታስተኛት ይልቅ « ቢኖረኝኮ በወርቅ ላይ አስተኛሽ ነበር» ብትላይ ይበልጥ ትደሰትብሃለች ( በወርቅ ላይ አታስተኛት ማለቴ አይደለም ድርጊት በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን የሌለህ ጊዜ እስኪኖርህ አትጠብቅ ቢያንስ እንክዋን ምላስህን ተጠቅመህ ለማስደሰት ሞክር እዚ ጋር ልብ በል ከላይ ምን አልኩህ? ሴት ልጅ ከድርጊት በላይ ንግግር ይስባታል ብዬሃለዋ አየህ አሁንም ሴት ልጅ በጥፊ ከምትመታት በላይ መጥፎ ቃላቶችህ ውስጥዋን ይሰብራታል በመጥፎ ቃላቶችህ ልብዋን ታደማዋለህ ( በጥፊ በላት ማለቴ አይደለም) በእውቀት የተሞላች ከሆነች እንጂ መቼም ቢሆን በንግግርህ ያስቀየምካት ሴት ይቅር አትልህም.."

... ተውፊቅ ቀጠል አደረገና "ሃኒ ይቅርታ ምጠይቅሽ ልጆቼን ይዘሽ ስለምትወጪ ፈርቼ አይደለም እንደጎዳሁሽ ስለተረዳው እንጂ የጎዳሁት ልብሽንም ልጠግንልሽ እፈልጋለው እክስሻለው ብቻ ይቅር በይኝና ተመለሺ የቤቱ መሪ አንቺ ትሆኛለሽ" አለኝ በዚ ጊዜ ሻንጣዬን አስቀመጥኩኝ ወደ እሱ ጠጋ አልኩኝና አንዴ በጥፊ አልኩት "ድጋሚ እንደዚ አይነት መጥፎ ንግግር እንዳትናገረኝ" አልኩትና እንባውን ጠርጌለት አቀፍኩት ይቅርታም አረኩለት ወደ ቤቴም ተመለስኩኝ አዘን መስሎ የነበረው ቤታችንን አደማመቅነው እንደገና ፍቅር ተዘራበት...

@kezim_kezam

...አመሻሽ አካባቢ ዩሱፍ መጣ ሃላሌ ሁሉ ነገር እንዲፈታና ትደራችን እንደገና ወደ ቀድሞውኑ እንዲመለስ ስለፈለገ ከይሱፍ ጋር ስለ ሁሉም ነገር በግልፅ ተወያየን ሌላ ትዳር እንድናሲዘው ጠየቅነው ዩሱፍም ተስማማ በመጨረሻ ግን "ልጄስ አብሮኝ ይሆናል?" ብሎ ጠየቀን በዚ ጊዜ እኔ ይኼን እንደሚጠይቀን ስለተረዳው መጀመሪያ ያዘጋጀሁትን ኡስታዝ ወይም ሼህ ጠራሁት በዚ ዙርያ እንዲያማክረን ጠየቅነው በኔ ሁኔታ ዩሱፍም ሆነ ተውፊቅ ተደናግጠዋል ሼሃችን ከትዳር በፊት ስለ ሚወለድ ልጅ ብዙ ነገር ከነገሩን በኃላ በስተመጨረሻም ለዩሱፍ እንዲ አሉት " ልጄ ይህ ልጅ ያንተ ልጅ አይደለም ምክንያቱም ቅድም እንደነገርኩህ ከትዳር በፊት የሚወለድ ልጅ አባት የለውም የወለደችልህን ሴት እስክታገባትና ከወንጀላቹ እስክትፀዱ ድረስ ልጅህ አይሆንም" አሉት በዚ ጊዜ ዩሱፍ ተደናገጠ ምን ማለት ነው ብሎ ጠየቁም ሼሁም ብዙ ማስረጃ በማቅረብ አብራሩለት ዩሱፍ አሁንም እንዲብራራለት ይፈልጋል...

ይቀጥላል

@ሼር

ይቀላቀሉን👇 ይቀላቀሉን👇
@kezim_kezam @kezim_kezam

For any comment👇
@kezim_kezambot
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «🍃 ሃናን 🍃 #ክፍል_ሃያ_ሰባት 2⃣7⃣ "...ትዳር ማለት ይህ ነው, ኢማንህን ሲጠብቅልህ፣ ደስተኛ ሲያደርግህ፣ እንደተመኘኸው ቤትህ በሳሊህ ልጆችና በመልካም ሚስትህ ሲደምቅልህ፣ ባልሽ ፍቅር ሲሰጥሽ አክብሮሽና ወዶሽ ከፍ ያለን ደረጃን ሲሰጥሽ... ትዳር ማለት ይህ ነው ኩርፍያ ያለበት አንዱ ሲያኮርፍ ወይም ቅር ሲሰኝ አንዱ ተረድቶ ያበሳጨሽን ነገር ለማወቅ የሚጥርና ለጥፋቱም ይቅርታ የሚጠይቅ, ባጭሩ…»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
🍃🍂ሃናን🍂🍃

#ክፍል_ሃያ_ስምንት 2⃣8⃣

...ዩሱፍ የተነገረው ሐዲስ (የሼሁ መልስ) አልተዋጠለትም በመጨረሻም ሲጨንቀው "ይህ ሐዲስ ለኛ ሃገር አይሰራም ያኔ ለአማጮዎች የተስፈራራበት ሃዲስ ነው" አለ ከጭንቀት የመነጨ ንግግር ነበር "ያ ሼህ ምንም ሊገባኝ አልቻለም እንዴት ይህ ልጅ በኔ አማካኝነት ተወልዶ እንዴት ያንተ ልጅ አይደለም ትሉኛላቹ?" ብሎ ጠየቀ ሼሁም በሎጂክ ሊያስረዱት ፈለጉና እንዲ አሉት "አንድ ሌባ ብዙ ብር ቢዘርፍና በዘረፈው ብር ሱቅ ከፈተ እንበል በከፈተው ሱቅ ብዙ ብር አገኘ ትርፋማም ሆነ ታድያ ይህ ሁሉ ገንዘብ የሱ ነው?" ብለው ለዩሱፍ ጠየቁት ዩሱፍም "አይ አይደለም ሁሉም ገንዘቡ የተዘረፈው ሰው እንጂ የሌባው አይደለም" አለ ሼሁም "ይህ እንዴት ይሆናል የዘረፈው ገንዘብ አዎ የሱ አይደለም ነገር ግን በከፈተው ሱቅ ያገኘው ገንዘብ የሱ የድካሙ ነው" አሉት ዩሱፍም "ያ ሼህ ተሳስተዋል እንዴት እንደዚ ሊሆን ይችላል? ሲጀመር የገንዘቡ ባለ ሃቅ ሌላ ሰው ነው ስለዚ በዘረፈው ገንዘብ ሱቁን ስለከፈተበትና ስለደከመበት ብቻ የሱ ሃቅ ሊሆን አይችልም ሙሉ ገንዘቡ የሌባው ሳይሆን የዛ የባለ ሃቁ ነው።" አለ ሼሁም "የሰረቀው እሺ የሰው ነው አልን ነገር ግን የለፋበት የደከመበት ገንዘብ እንዴት ለተዘራፊው ይሆናል?" ብለው ጠየቁት ዩሱፍም "ምንም ቢደክምበት የቱንም ያህል ቢለፋበት በሰረቀው ገንዘብ ስለሆነ አሁንም ቢሆን ሁሉም ገንዘቡ ለባለ ሃቁ ነው።" አለ ሼሁም በዚ ጊዜ ፈገግ አሉና

"ሃቅ ተናግረሃል አሁን ያልከው ሁሉ እውነት ነው አየህ ወጣቱ ሌባው ያልደከመበትን ገንዘብ አግኝቶ ነበር በዛ ገንዘብ ለፍቶና ደክሞ ላሌ ተጨማሪ ገንዘብ አገኝ ስለለፋበትና ስለደከመበት አሁን ያገኘው ገንዘቡ የሱ ነው ልንል እንችልም አንተም እንደዛው ያኔ ያለ ሃቅክ የሌላ ሰውን ሃቅ ወስደህ ነበር ባለቤቱ አንተ አልነበርክም ያንተ ያልሆነውን ሃቅ ደፈርክ ስሜትህን አስደሰትክ ከዛም አልፎ ደሞ ልጅ ተወለደልክ አስብ የተወለደው ልጅ ባንተ ሃቅ ሳይሆን በሰው ሃቅ ነው የሰዎች ሃቅ ደሞ ሁሌም የሰው እንጂ መቼም የኛ ሊሆን አይችልም" አሉት በዚ ጊዜ እኚህ ጥበበኛ አባት ዩሱፍን ወደ መስመር አስገቡት ለዛም ነው ዩሱፍ "እሺ ማካካሻው ምንድነው? ልጄ ልጄ የሚሆነው ምን ባደርግ ነው?" ብሎ ጠየቀ ሼሁም "ልጄ መስፈርቱ ተውበት ነው ከልብህ ተፀፃች ሆነህ ወደ ጌታህ አልቅሰህ ተመለስ ያኔ አላህ ይምርሃል ልጁ ያንተ የሚሆነው ግን የልጁን እናት ስታገባት ብቻ ነው" አሉት...

..አሁን የዩሱፍ መልስ እየጠበቅን ነው እኚህ አባት (ሼህ) ያማረ ምላሽን መልሰውለታል ይሱፍ እሺ ልጄ አይደለም በቃ ብሎ አምኖ ይቃበላል ወይስ ምን ይላል? ( እናንተ በዩሱፍ ቦታ ብትሆኑ መልሳቹ ምን ይሆን ነበር? እስቲ መልሱን ለራሳቹ መልሱትና ከታች ያለውን አንብቡ )....

...የትኛውም ሰው ጥሩ ነገር ስታቀርብለት ሊቃበልህ ወይም አንተን ሊከተልህ ይፈልግና በመሃል አሳቡን ይቀይራል ለምን ሃሳቡን ይቀይራል? (የራሱ ምክንያት አለው..)
ታድያ ዩሱፍም የኚህን አባት ሎጂክም ሆነ የረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሐዲስ (ንግግግር) ውስጡ ገብቶ አምኖበትም ለመቀበል ዝግጁ ነበር ነገር ግን በመሃል ድጋሚ ወደ ኃላ ተመለሰ "አይሆንም ልጄ ልጄ አይደለም ብሎ ማመኑ ይከብደኛል በዛ ላይ ሌላ ልጅ መውለድ አልችልም እንዴት ሆኖ ልጄን ለሌላ ልስጥ" አለ ሼሁም "አንተ ወጣት አትወላውል አላህ ወላዋዮችን አይወድም ምን ጊዜም ደሞ ለአላህ ብለህ ሁሉ ነገርህን ለአላህ ካስገዛህ በምላሹ ጥሩ ነገር ይገጥምሃል እንዳልኩህ ተውበት አድርግ ሌላ ሚስት አግባ ልጅም ታገኛለህ እኔም አብሬህ ነኝ ዱዓ አደርግልሃለው አንተም በዱዓ በርታ ያኔ ያጣኸውን ታገኛለህ ኢንሻ አላህ" ብለው አበሸሩት...

...በስተመጨረሻም ዩሱፍ የአላህን ታምር ለማየት ቋመጠ ወደ አላህ ለመመለስ ወሰነ አንገቱን አቀርቅሮ አለቀሰ እኔ እግር ስር በመውደቅም በድጋሚ ይቅርታ ጠየቀኝ "ከልብሽ አውፍ ካላልሺኝ ተውበት ማድረጌና ወደ አላህ መመለሴ ጥቅም የለውም ለአላህ ብለሽ ከልብሽ አውፍ በዩኝ" አለ እኔም ከልቤ አውፍ ማለቴን ገለፅኩለት በስተመጨረሻም ተስማማ "ሶስቱም ልጆችሽ በስጋ አባት ባልሆናቸውም እንደ ልጆቼ አያቸዋለው" አለ ወደ ተውፊቅ ዞር አለና "አንተ ተውፊቅ እንደ ባዳ ታባረኛለህ ወይስ ዝምድናችንን እንቀጥላለን?" ብሎ ተየቀው ሃላሌም "ዩሱፍ ቅድም በተናገርኩህ ነገር አትዘንብኝ ከልቤ አልነበረም ዝምድናን መቀጠሉንም እፈልገዋለው" ብሎት አቀፈው...

...ዩሱፍ በቶሎ ተዘወጀ (የዱዓ ሰው ከሆንክ....) ይባል የለ ዩሱፍ ከልቡ ተውበት አድርጉ ስለነበር፣ ወደ አላህም ቀርቦ ስለነበር (በዱዓ፣ በሰላት፣..) አላሁ ሱብሃነሁ ወተአላ ተቀበለው ዶኮተሮች ያሉት ውሸት ሆነ ብዙም ሳይቆይ አላህ መንታ ልጆችን ሰጠው...

( ወደ አላህ እየቀረባቹ በሄዳቹ ቁጥር የዱንያውን ጀና ትጎናፀፋላቹ መኖራቹ ተራ ነገር ሳይሆን ትርጉም መኖሩንም ትረዳላቹ...)

ይቀጥላል #የመጨረሻው_ክፍል

#ሼር

ይቀላቀሉን👇 ይቀላቀሉን👇
@kezim_kezam @kezim_kezam

For any comment👇
@kezim_kezambot
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «🍃🍂ሃናን🍂🍃 #ክፍል_ሃያ_ስምንት 2⃣8⃣ ...ዩሱፍ የተነገረው ሐዲስ (የሼሁ መልስ) አልተዋጠለትም በመጨረሻም ሲጨንቀው "ይህ ሐዲስ ለኛ ሃገር አይሰራም ያኔ ለአማጮዎች የተስፈራራበት ሃዲስ ነው" አለ ከጭንቀት የመነጨ ንግግር ነበር "ያ ሼህ ምንም ሊገባኝ አልቻለም እንዴት ይህ ልጅ በኔ አማካኝነት ተወልዶ እንዴት ያንተ ልጅ አይደለም ትሉኛላቹ?" ብሎ ጠየቀ ሼሁም በሎጂክ ሊያስረዱት ፈለጉና እንዲ…»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
••○●🍃 እኔ ግን ጀግና ነኝ🍃●○••

ፍቅርን እያሰቡ ማፍቀርን ሚመኙ
ውበትን ሲስሉ በቀለም ሚዋኙ
ፍቅርን ከውበት ጋር መዝነው ሚዳኙ
ድፍረት አልባ ሆነው በዚች ቅፅበት
ምድር እነሱ ተገኙ

እኔ ግን ኮራሁ፦

ፍቅሬን ነገርኩሽ ጥጉን አሳየሁሽ
ጀግና ሆኜ ቆሜ ያላንድች ፍርሀት
ፍቅሬን ገለፅኩልሽ

በሀሳብሽ መሀል እርቀሽ
ሳትሄጂ ይታይሽ ይሄንም
እንደ ሞኝ ፍጥረት ማፍቀርን
ፈርቼ ወደ ሁዋላ አላልኩም
ልነግርሽ ፈርቼ ሰዎች እንዲነግሩሽ
ከዳር ላይ አልቆምኩም

ብቻ አንቺ ተረጂ ፍቅሬ ይገለፅልሽ
አፍቅሬ መምጣቴ ውሸት አይምሰልሽ
መርበትበት መንቀጥቀጥ የፍቅር
መስፈርቱ መስሎ አይታይሽ
በጀግንነቴ ነው ይሄን የምነግርሽ


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ ከዚህም ከዚያም TUBE

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ
🍃ሃናን🍃

#ክፍል_29⃣

#የመጨረሻው_ክፍል

...ያ ሁሉ የሆን በምክንያት ነበር (የፃፍኩት) ምን አልባት በሆነው ነገር ጥቂት ሰው ትምህርት ወስዶበት ሊሆን ይችላል...

...ፍቅር የልብ መገጣጠም ነው! የምታፈቅራት ሴት እንደምታፈቅራት ባትነግራት እንክዋን እስዋም የምታፈቅርህ ከሆነ ፍቅርህ ይገባታል ከአይኖችህ ታነባለች በድምፅህ ቅላፄ የፍቅርህን መጠን ታውቃለች "ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?" ብላ አጠይቅህም ምክንያቱም በድምፅህ ቅላፄ የሚወጣው ቃላት ልብዋ ዘልቆ ይገባል በአይንዋ ሳይሆን በልብዋ ታይሃለች በልብ (ከውስጥ) የታየ እይታ ደሞ ምን ጊዜም ሃቅና ግልፅ ነው ለዛ ነው ብዙ ሰው ይሳሳትና በስህተቱ ልክ ልትቀጡት ስትፈልጉስህተቱን ለማስተባበል ይሞክራል "እኔኮ ለማለት የፈለኩት እንደዚ ነው" ወይም "እኔኮ ይሄን የምሰራው ለዚህ ብዬ ነው" በማለት ጥፋቱን ያስተባብላል የሱን ስህተት ከልብ ካያችሁት (በሱ ቦታ ሆናቹ ካያችሁት) ስህተቱ ስህተት ቢሆን እንክዋን ማስተዛዘኛ ትሰጡታላቹ "ይህ ያደረገውኮ ምን አልባት ለዚ ብሎ ይሆናል" ትላላቹ ይህ ነው የልብ እይታ ሚባለው ...(ከፈለጋቹ ፍልስፍና በሉተ)

...አንድ ያልነገርክዋቹ ነገር ላጫውታቹ በፊት ኮሌጅ እየተማርኩኝ ሳለው ጋደኛዬ አህላም ጋደኛችንን ሰሚራን ሁሌም በስህተት ትፈርጃታለች ከወንዶች ጋር ስትሆንና ስትሳሳቅና ስትጫወት ካየች ትናደድባታለች ትቆጣትም ነበር "ለምን ይህን ታደርጊያለሽ አላህን አትፈሪምን?" ትላታለች የሰሚራ መልስ ሁሌም "አንቺኮ አልገባሽም ተይው ምን አልባት አንድ ቀን ትረጂው ይሆናል" ትላትና ትሄዳለች አህላምም ተናዳባት ትተዋታለች ሁለቱም ግን በጣም ይዋደዳሉ እኔንም በጣም ይወዱኛል እንም እንደዛው...

...እንደነገርክዋቹ አህላም ሁሌም ሰሚራት ይህ ልክ አይደለም እንደዚ አድርጊ እያለች ትቆጣታለች ታድያ አንድ ቀን የኔን ልደት ለማክበር ይመስለኛል ቤት መተው ነበር ሰሚራ በለበሰችው ልብስ የተሸማቃለች የደበራት ትመስላለች እውነትም የለበሰችው ልብስ ይከብዳል ማለት ያን ያህል ባያጥርም አጥሮ ግን ነበር በማጠሩ ተሸማቃለች እንደ በፊቱ አትጫወትም ጥግ ቁጭ ብላ ነበር አህላም ያ ቀይ ፊትዋን እሳት አስመስላው ለሰሚራ እንዲ አለቻት "በለው ዛሬ ምነው ለቀቅሽ እንዴ? ምን አይነት አለባበስ ነው?" ብላ ልክ እንደናት ተቆጣቻት በዚ ጊዜ ሰሙ ተናዳ ከሳሎኑ ወጣች እኔም ለአህላም "ምነው አሁንስ አበዛሺው እንዴት እንደዚ ትናገሪያታለሽ ትንሽ እንክዋን ለሞራልዋ አትጨነቂም?" ብዬ ተቆጣዋት አህላምም "ሃኒ ወላሂ እንዲከፋትኮ አልነበረው የለበሰችው ልብስ የሙስሊም አደብ አይደለም በጣም አጥሯል ለዛ ነውኮ" አለቺኝ እኔም "እኮ እንደዚ አልነበረማ" ብያት ተነስቼ ወደ ሰሙ ሄዱኩኝ ሰሙን አይዞሽ ውዴ ብዬ አፅናናዋትና አቀፍጅዋት በዚ ጊዜ ልብ የሚነከ ፈፅሞ ያልጠበኩትን ንግግርን ነገረቺኝ፦

"ሃኒ ሳላውቅ ቀርቼኮ አይደለም ችግር ያለብኝ ሰው ነኝ ከወንዶች ጋር እንደዛ ምሳሳቀውና ምጫወተው ፈልጌው አይደለም ወንዶችን በጣም እፈራለው የሆነ ነገር ካረጉኝ ብዬ እሰጋለው የዘውትር ጭንቀቴ ወንዶች ካሁን አሁን ምን አረጉኝ የሚለው ነው ለዛ ነው ከወንዶች ጋር ቀርቤ እንደነሱ ምሆነው ቢያንስ እንክዋን እቺማ ዱርዬ ናት ብለው እንዲርቁኝ ወይም ስለኔ እንዳያስቡ ስለምፈልግ ነው...

...ዛሬ የለበስኩት ቀሚስ ደሞ በሰዎች እይታ ዱርዬ መስዬ ለመታየት ነው ምክንያቱም ለዱርዬ ሴቶች ማንም ቦታ አይሰጥም በተሌ ወንዱ" አለቺኝ በአነጋገርዋና በአስተሳሰብዋ በጣም አዘንኩኝ ሰሙ እንደዚ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር በራስ መተማመንዋ የገነነ ጀግና ሴት አድርጌ ነበር ምስላት ታድያ ያሰብኩት ያሰብኩት አልነበረም ሰሙ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብታ ነበር ...

...ለአህላምም ሁሉንም አጫወትኩዋት አህላምም ደነገጠች ያኔ ሳተውቅ በተናገገረቻት ነገር አዘነች አህላም አንባቢ ስለነበረች አንድ መፃፍ ሰጠቻት (ጠብታ ማር) የሚል ርዕስ ነበር (#በዚ_አጋጣሚ_ግብዣዬ_ነው እኔም አንብቤዋለው) ይህ መፃፍ ከአላህ በኃላ በራስ መተማመንዋን መለሰላት...

..ከሃሜቱ እንውጣ, ብዙዎቻችን የሆነ ጉድለት አለብን ያንን ለመሸፈን ብለን በዙ ያልተገቡና መሆን የሌለባቸውን ነገራቶች እናደርጋለን የምናደርገው ነገር ልክ እንሁን ወይም ስህተት አናውቀውም በቃ በሰዎች ፊት የበታችነት ስሜት እንዲሰማን አንፈልግም(ይህ ልክ ነው) ነገር ግን ከልክ ያለፈ ጥርጣሬና ፍራቻ ከውስጣችን እናውጠ ሁለተኛው ማንነታችንን እናዳምጠው ሁለተኛው ማንነታች ፍፁም ልክ ነው ሁለተኛው ማንነታችን መሪያችን ነው (ተረገግቶ አስቦ የተናገረ... ) ይባል የለ ስትረጋጋና ስታስብ ከሁለተኛው ማንነትህ ጋር ትነጋገራለህ ሁለተኛውም ማንነተህ ደሞ ቅኑን መንገድ ይጠቁምሃል...

የኔ ታሪክ እዚ ጋር አብቅቷል ማናችንም መጀመሪያችን ላያምር ይችላል ይህ የኛ ጥፋት ሳይሆን የፈጣሪያችን ውሳኔ ነው ስለዚ መጨረሻችንን ለማሳመር ሁላችንም እንሞክር, እንጣር ወደ ጌታችን እንቅረብ እመኑኝ ወደ ጌታው የቀረበ ሁሉ ልዩዎች ናቸው ሁሉ ነገራችን እያማረ ይመጣል ውዶቼ አንሰሳት ማለቴ አይደለም ስህተትን አናብዛ ስህተቶቻችን መማሪያ ይሁኑን... ውድዋ እህቴ ውዱ ወንድሜ ሰለ ነጊያችን እናስብ ጊዜያዊ ነገር ሁሉ ለተራ ሰዎች እንጆ ለኛ አይነቱ (ለሙስሊም) የተገቡ አይደሉም ጌዜያዊ ነገር እንዳያምረን እንዳያታለንም...

#ተፈፀመ❤️

አብራችሁኝ የቆያቹ ሁሉ ከልብ አመሰግናለው😘
የሃናን ታሪክ እንዴት ነበር? እስቲ በውስጥ መስመሬ ንገሩኝ ተማራቹበት ወይስ ...?👉
@Emodish



#ሼር
ይቀላቀሉን👇 ይቀላቀሉን👇
@kezim_kezam @kezim_kezam

For any comment👇
@kezim_kezambot
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «🍃ሃናን🍃 #ክፍል_2⃣9⃣ #የመጨረሻው_ክፍል ...ያ ሁሉ የሆን በምክንያት ነበር (የፃፍኩት) ምን አልባት በሆነው ነገር ጥቂት ሰው ትምህርት ወስዶበት ሊሆን ይችላል... ...ፍቅር የልብ መገጣጠም ነው! የምታፈቅራት ሴት እንደምታፈቅራት ባትነግራት እንክዋን እስዋም የምታፈቅርህ ከሆነ ፍቅርህ ይገባታል ከአይኖችህ ታነባለች በድምፅህ ቅላፄ የፍቅርህን መጠን ታውቃለች "ምን ያህል ታፈቅረኛለህ?" ብላ…»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​
••○●🍃"ፍለጋ"🍃●○••

ማልጄ ወጥቼ
ከደጄ ባሻገር ካለው
ተራራ አናት ዘውትር
የምቆመው
ወሬ ሽቼ አይደለም
አንቺን አይ ብዬ ነው።
ከዱር ከገደሉ
ከጋራ ሸንተረር
ስባዝን 'ምውለው
ዙረት እኮ አይደለም
አንቺን እያሰስኩ ነው።
ከባህር ከውቅያኖስ
ከሃይቅ ከወንዙ
ስጠልቅ የምከርመው
ዋና አምሮኝ አይደለም
አንቺን ስፈልግ ነው።
የማትመጪ እንደሁ
ወይ የማላገኝሽ
ላኪብኝ እባክሽ
ትርፍ እድሜ የለኝም
ከፍለጋው ድካም
ለኔ አይብስብኝም
"አልመጣም!" ብትዪኝ
የምስራች እንጂ
መርዶ አይሆንብኝም!!


━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን 😘

አዘጋጅ፦ ከዚህም ከዚያም TUBE

➳➳ ከወደዱት ለሌሎች ሼር ያድርጉ !! ➢➢
┄••○●🍃🍂ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ 🍂🍃●○••┄

ተጀመረ ተጀመረ
join ብለው አሁኑኑ ታሪኩን ይጀምሩ
ምርጥና አጓጊ የፍቅር ታሪክ ተጀመረ
ከዚህም ከዚያም
ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም
┈┈••◉❖◉●••┈
┄┄┉┉✽̶»̶̥✿🌺✿»̶̥✽̶┉┉┄┄

https://www.tgoop.com/joinchat-RdHDUi9DINRiMGNk
ً ̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUBEًٍٜ͜͡ pinned «┄••○●🍃🍂ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ 🍂🍃●○••┄ ተጀመረ ተጀመረ join ብለው አሁኑኑ ታሪኩን ይጀምሩ ምርጥና አጓጊ የፍቅር ታሪክ ተጀመረ ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም ከዚህም ከዚያም ┈┈••◉❖◉●••┈ ┄┄┉┉✽̶»̶̥✿🌺✿»̶̥✽̶┉┉┄┄ https://www.tgoop.com/joinchat-RdHDUi9DINRiMGNk»
Forwarded from Hi (̰̰̰̰̰̰̃̃̃̃̃̃ከዚህም ከዚያም TUßE✮ًٍٜ͜͡)
🍃ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ 🍃

🔥ክፍል 1⃣

ደራሲ ወንድማገኝ ለማ

#እዉነተኛ ታሪክ እንደወረደ

በከዚህም ከዚያም TUBE ብቻ በየቀኑ


(ርዕሱን ስታዩ አላመናችሁም አይደል? እኔም ልጅቷ ሙሉ ታሪኳን እስክትነግረኝ ድረስ አላመንኳትም
ነበር)
‘’ራሴን ላጠፋ ነው'ን በምፅፍበት ወቅት ላይ በሚሴጅ ራሔል የምትባል ልጅ በተደጋጋሚ "ወንዴ
ላገኝህ እፈልጋለሁ" እያለች ትጨቀጭቀኝ ነበር ፤ እኔም ጥያቄዋ ሲበረታብኝ እሺ ብዬ ስልኳን
ተቀበልኳት። ደውዬላትም ባልደራስ በሚገኘው ኮንዶሚኒየም ቤቷ ቀጠሮ ይዘን ተገናኘን።
ቤቷ እንደደረስኩም የሚያብለጨልጭ አረንጓዴ ድሪያዋን ለብሳ ፣ በግራ ጉንጯ ላይ ሚጢጢዬ
ተርዚና ይዛ ነበር። ሰላም ብያት ወደ ውስጥ ስገባ በሺሻ ጭስ ታውዷል ፣ አረቢያ መጅሊሷ ላይ
ደም የመሰለ ቃሙኝ ቃሙኝ የሚል ጫት ተቀምጧል። ቤቷ ብዙም ኮተት ያልበዛው ቀለል ያለ
ነው። በየግርግዳው ፣ በየመደርደሪያው ፣ በየፍሬሙ ላይ ድንቡሽቡሽ ያለ የህፃን ልጅ ፎቶ
ተሰቅሏል።
" ሪች ልጅሽ ነው?"
" አዎ ከአንድ ወር በኋላ አስር አመት ይሞላዋል። ቆንጅዬ ነው አይደል?"
"አዎ በጣም ያምራል" አልኳት። እውነት ለመናገር ልጁ ስዕል እንጂ ሰው አይመስልም። ጫት
እንድቅም ስትጋብዘኝ እንዳላሰኘኝ ነግሬያት፣ እሷ እየቃመችና ሺሻዋን እያንደቀደቀች ወሬዋን
ጀመረች።
"ቃላቶችን ግን እንደመጣልኝ ስለምጠቀም እንዳይደብርህ?!"
"ችግር የለውም.......በጣም የሚከብደኝን ስፅፈው ኤዲት አደርገዋለሁ"
"ግን ከምር ትፅፈዋለህ?"
"በደንብ እንጂ.......ታዲያ ለምን የምቀዳሽ ይመስልሻል?"
"ታዲያ ከምን ልጀምርልህ?"
"አንቺን ከተመቸሽ" (ትንሽ ሺሻዋን እየሳበች አሰብ አደረገችና)
......ተወልጄ ያደኩት እዚሁ አዲስአበባ አትክልት ተራ ገንዳ ስር ነው። እናቴን አላውቃትም ፤
ለነገሩ እንዳውቃትም አልፈልግም። ምክንያቱም ዘጠኝ ወር ሙሉ ያረገዘችኝን ልጇን ከማህፀኗ
ስወጣ ልክ እንደ አልሰፋልጊ ቆሻሻ ዕቃዋ ልክ እንደ ሽንቷ እንደ አክታዋ አይሆኑ ቦታ ነው
የጣለችኝ። እኔን የማሳደግ አቅሙ ባይኖራት እንኳን ምናለ መንደር ውስጥ ብትጥለኝ? ወይ
ወዲያውኑ አፍና ብትገድለኝ ይሻለኝ ነበር ገንዳ ውስጥ ከምትጥለኝ!! ታዲያ ይቺን የሰይጣን ሙሻራ
የሆነች ጨካኝ እን፡ እናት ተብዬዋን ባውቃትስ ምን ታደርግልኛለች? አባቴን ግን አውቀዋለሁ።
( ማለቴ እሱ አባትሽ ነኝ ስላለኝ ነው እንጂ ፣ እኔ እንኳን ምንም ማረጋገጫ የለኝም) የኔ ቢጤ
ነው። ኧረ ምን የኔ ቢጤ ለማኝ ነው! እሱ ለማኝ ነው!! አዎ ለማኝ ነው!!! እኔ ደግሞ የለማኝ
ልጅ!!!!
የማላውቃት እናቴን ብጠላትም የአባቴን ያህል ግን አይሆንም። እሱ ማለት እግዜር ከጭቃ
ጠፍጥፎ ሊሰራው አስቦ ገና ጭቃ እያለ ሁኔታው አላምር ስላለው እስትንፋሱን እፍ ሳይልበት
ረስቶት ገምቶ ሸቶ ከሚሊዮን አመታት በኋላ በዳርዊን የኢቮሊውሽን ቲዎሪ ወደ እበትነት የተቀየረ
ነው። እኔንም የአብራኩ ክፋይ ትል አድርጎ ራሱ የፈጠረኝ ነኝ። እሱ ሸንቶኛል ብዬ እንጂ ወልዶኛል
ብዬ ለአንዲት ሰከንድም አስቤ አላውቅም። ምክንያቱም እኔ ማለት ለሱ በመንግስቱ ሀ/ማርያም
ስም እንደሚለምንበት ቆማጣ እግሩ ታክስ የማይከፍልብኝ የገቢ ምንጩ ብቻ ነበርኩና!
ገና በአምስትና በስድስት አመቴ ለሊት 10:00 እየቀሰቀሰኝ አትክልት ተራ ከሚመጡ ነጋዴዎች
በብርድ እየተንዘፈዘፍኩ እንድለምን ያደርገኝ ነበር። ለእግሬ ጫማ ፣ ሀፍረቴን መሸፈኛ ቀሚስ/ሱሪ
ሳይገዛልኝ ለአመታት አንድ ቲሸርት ብቻ እየለበስኩኝ የምለምነውን እየተቀበለኝ በባርነት ገዝቶኛል።
አንዳንዴ መርካቶ እዛ ሞጣ ሰፈር ጠላውን ሲለጋ አምሽቶ መጥቶ ሲደበድበኝ ካመሸ እንቅልፍ
አምሽቼ ስለምተኛ ለሊት ሲቀሰቅሰኝ ቶሎ ካልነቃሁለት ገላዬን በሲጋራ እየተረኮሰ ይቀሰቅሰኝ ነበር።
(ጀርባዋ ላይ ያሉትን ብዙ ጠባሳዎች አሳይታኛለች)n
የሚገርምህ ነገር የጭካኔው ጭካኔ በየካፌው ፣ በየታክሲው ፣ በየሱቁ እየለመንኩ የሸቀልኳትን
ሳንቲም ሁሉንም ወስዶብኝ እንኳን "ልጄ ይቺን ሽልጦ ብይባት" ብሎ ስሙኒ አይሰጠኝም ነበር።
በዚህ የተነሳም ሁልጊዜ ረሀብ ስለሚጠናብኝ እዛችው የተወለድኩባት አትክልት ተራ ገንዳ ላይ
የተጣሉትን ማርች ሙዞች ፣ የተበላሹ አቡካዶዎች ፣ የፈራረጡ ፓፓዬዎች ከዝንቦች ጋር
እየተሻማሁ ነበር ከርሴን የምሞላው አንዳንዴ የፊቴን አጥንት መግጠጥ ፣ የሰውነቴን ከሲታነት ያዩ
ሰዎች የሚበሉትን ምግብ በፌስታል አድርገው ሲሰጡኝ እሱ ከኔ ምንም ሰርቀሽ እንዳትበይ ስላለኝ
እስኪመጣ ምንም ሳልቀምስ በምግቡ ሽታ ብቻ በረሀብ ሰክሬ እጠብቀዋለሁ። ታዲያ ልክ
እንደመጣ ክራንቹን በክንዱ ተደግፎ ምግቡን መንጭቆኝ ብቻውን መብላት ይጀምራል። እኔ ካሁን
አሁን ብይ ይለኛል ፣ በዛ ጥቁር ጥፍር ቀለም የተቀባ በሚመስለው ቆሻሻ እጁ ያጎርሰኛል ብዬ
ስጠብቅ "ቡዳ! ምን አባሽ ታፈጭብኛለሽ?! ሂጅ ጥፊ ከፊት ለፊቴ!!!" ብሎ በወጥ እጁ አይኔን
በጥፊ ይለኛል። በረሀብ ብዛት ጉልበቴ ስለመነመነ በክራንች የጠነከረ የእጁን ምት መቋቋም
ስለሚያቅተኝ ዞሮብኝ ፊቱ ፍንችር እላለሁ። እሱ ምንም ሳይመስለው አራዳ ጊዮርጊስ አጥር ስር
ካለው የላስቲክ ዳሳችን ውስጥ እየጎተተ አውጥቶ ይወረውረኛል። ሁልጊዜም እሱ እንዲህ
ሲበድለኝ አጥሩን ተንተርሼ የማድረው ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ዝም ብሎ ይሄንን ሁሉ ግፍ ማየቱ
ይገርመኝ ነበር። ታዲያ አንዳንዴ ሲከፋኝ ላለቅስ ቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ገብቼ የጊዮርጊስን
ምስል ሳይ ልክ በጣም የከፋኝ ቀን ሰማዕቱ የላስቲክ ቤታችን ውስጥ ከፈረሱ ወርዶ ይመጣና
ምስሉ ላይ እንደሚወጋው አውሬ አባቴንም "ራሔልን ለምን ትመታታለህ!?" ብሎ በጣም ተቆጥቶ
አባቴንም በራሱ ክራንች ወግቶ ይገድልልኛል እያልኩ በቁሜ ለአመታት እቃዥ ነበር። ታዲያልህ
አንድ ቀን ገላዬ ቆሽሾ ጭቅቅቱ ሊቆራርጠኝ ሲደርስ ፣ ፀጉሬ ቀምሎና ቀጭሞ ሌሎች የየኔቢጤ
ልጆች ሳይቀር እስኪጠየፉኝ ድረስ ገምቼ ስለነበር ለመተጣጠብ ወደ ራስ መኮንን ወንዝ
ወረድኩኝ። ትዝ ይለኛል በልጅነት ስሜት ራቁቴን ሆኜ እየተንቦራጨኩኝ ሳለ........ከፊት ለፊቴ
ከነበረ ጢሻ ውስጥ የተቋጠረ ጥቁር ፌስታል አይቼ ሌሎች የጎዳና ልጆች ሊበሉት ደብቀው
ያስቀመጥኩት ቡሌ መስሎኝ እየተንገበገብኩ ልብሴን እንኳን ሳላደርግ ወደ ላስቲኩ ሮጥኩኝ።
ምራቄን እየዋጥኩኝ በችኮላ ላስቲኩን ስቀደው.............ዓይኔ በሚያየው ነገር ፌንት ልሰራ ምንም
አልቀረኝም!........ያቺ የልጅነት ሚጢጢዋ ልቤ ግራ በመጋባት ልትፈነዳ ደረሰች...........
...የማየውን ነገር ማመን ስላልቻልኩኝ ዓይኔን በደንብ በልቅጬ ደግሜ ስመለከተው የባስ
አስደነገጠኝ።
.
.
ይቀጥላል... 50👍

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@kezim_kezam
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
4 any comment
@kezim_kezambot
❥❥________⚘_______❥❥
2025/07/14 17:49:18
Back to Top
HTML Embed Code: