tgoop.com/kibirenaw/530
Last Update:
ችግራችሁ ለምን እንደማይፈታ!
በሕይወታችሁ ያለ ማንኛውም ችግር . . . የገንዘብ፣ የኑሮ፣ የስራ ማጣት፣ የእኔ ነው የምትሉት ሰው ማጣት . . . እና የመሳሰሉት ችግር በቀላሉ አልፈታ አለኝ የምትሉ ከሆነ፣ የሚከተሉት የችግር አፈታት እንቅፋቶች እስቲ ተመልከቷቸውና መንገድ ፈላልጉ፡፡
1. ለችግራችሁ ሰዎችን የመውቀስ ዝንባሌ
ለችግራችን ሰዎችን የመውቀስ ዝንባሌ ችግራችንን ለመፍታት ሃላፊነትን እንዳንወስድ የማድረግ ተጽእኖ አለው፡፡ ምንም እንኳን ሰዎች ለችግራችን በሃላፊነት ቢጠየቁም፣ ለመፍትሄው ግን ሃላፊዎቹ እኛው ነን፡፡
2. መፍትሄ ላይ ከማተኮ ይልቅ ችግሩ ላይ ማተኮር
ሁል ጊዜ ችግሩን የሚያሰላስልና የሚያወራ ሰው ተጨማሪ ችግርን ይወልዳል፡፡ ከዚያ ይልቅ ለችግሩ የመፍትሄ መንገድ ላይ የሚያተኩር ሰው ፈጣን ለውጥን ያመጣል፡፡
3. ችግሩ ሊያስከትል የሚችልውን የከፋ ሁኔታ ጥጉ ድረስ በማሰላሰል መፍራት
ፍርሃት ያስረናል፣ የማሰብ አቅማችንን ያዳክመዋል፣ ተስፋችንን ያጨልመዋል፣ የመፍትሄ ሃሳብ እንዳንፈጥር ያደነዝዘናል፡፡ ከዚህ ይልቅ የተመረጠው መንገድ ችግራችንን ለመጋፈጥ ቆፍጠን ማለት ነው፡፡
4. ከችግሩ ባሻገር የምናየው ጠንካራና ግልጽ የወደፊት ዓላማ አለመኖር
ወደፊት እስከምናይ ድረስ ከዛሬው ችግራችን ለመውጣት መራመድ አንችልም፡፡ ከችግራችን የጠነከረ ራእይና ከዛሬው ሁኔታችን የላቀ የወደፊት እስኪኖረን ድረስ ከችግራችን የመላቀቅ አቅም አይኖንም፡፡
@kibirenaw
BY ማራናታ Maranata
Share with your friend now:
tgoop.com/kibirenaw/530