tgoop.com/kibirenaw/532
Create:
Last Update:
Last Update:
የሕይወት ጥያቄዎቻችን ጉዳይ
ብዙ ሰዎች፣ “በሕወቴ ያሉኝ መልስ የሚፈልጉ ጥያቄዎቼ ብዙ ናቸው” በማለት የሁኔታውን አሉታዊ ጎን ብቻ በማጉላት ይናገራሉ፡፡ ልክ ነው! ማንም ሰው ያልተመለሰ ጥያቄ እንዲኖረው አይፈልግም፡፡
አንድ ነገር ግን መዘንጋት የለብንም፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ሲኖሩን ብቻ ነው አእምሯችንን በትክክል የማሰራትና የፈጠራ ብቃታችንን የማሳደግ እድሉ ያለን፡፡
ከልጅነታችን በትምህርት ቤት ስናልፍ እኮ አስተማሪዎቻችን ካስተማሩን በኋላ ብዙ ጥያቄዎች እየጠየቁ ነው አእምሯችንን እንድናዳብር የረዱን፡፡ መልሱን ብቻ እያቀበሉ ቢሸኙን ኖሮ የማያስብና የማያድግ አእምሮ ይዘን እንቀር ነበር፡፡
ሕይወትም ብትሆን እኮ መልሱን ብቻ ብታቀብለን ኖሮ አእምሯችን የማያድግና ዝግ ይሆን ነበር፡፡ ሕይወት ግን በየእለቱ ከባባድ ጥያቄዎችን ስለምታቀብለን የነቃ፣ የሚያስብና መልስን ከዚህም ከዚያም ፈልጎ የሚያመጣ አእምሮን ወደማዳበር እናድጋለን፡፡
ሕይወታችሁ በጥያቄ መሞላቱ አያሳስባችሁ፡፡ ይልቁንስ ራሳችሁን ነቃ በማድረግ ሕይወት ለምታቀብላችሁ ጥያቄዎች ከዚህም ከዚያም መልስን ፈልጎ የሚያመጣ ማንነትን ገንቡ፡፡ መልስ የሌለው ጥያቄ የለምና!
@kibirenaw
BY ማራናታ Maranata
Share with your friend now:
tgoop.com/kibirenaw/532