tgoop.com/kibirenaw/536
Create:
Last Update:
Last Update:
ንስርን የሚገዳደር ብቸኛው የወፍ ዝርያ ቁራ ነው።
ቁራ በንስሩ ጀርባ ላይ ይቀመጥና አንገቱን ይነክሰዋል። ንስሩ ምላሽ አይሰጥም ፣ ከቁራ ጋር አይጣላም ፣ ከቁራ ጋር አይታገልም ፣ በቁራ ላይ ጊዜና ጉልበቱን አያጠፋም ይልቁንም ክንፉን ዘርግቶ ወደ ሰማይ ከፍ በማለት መብረር ይጀምራል።
በረራው ከፍ ባለ መጠን ቁራው ለመተንፈስ ይቸገራል። በመጨረሻም ቁራው በኦክሲጅን እጥረት ምክንያት ይወድቃል።
🎯.ዛሬ በህይወታችሁ የሚገዳደራችሁን ምንም አይነት ነገር አትታገሉት ፣ ጉልበታችሁን እና ጊዜአችሁን በእርሱ ላይ አታጥፉ ይልቁንም ከፍ ባለ አስተሳሰብ በልጣችሁ ውጡ ፣ በእውቀት ጠንክሩ ፣ መልካም ሥራችሁን ጨምሩ።
ንስሩ በጀርባው ላይ የተንጠለጠለውን ቁራ ትቶ ከፍታው ላይ እንደሚያተኩር የሌሎችን አሉባልታ ፣ ሀሜት ፣ ማስፈራሪያ ወደታች ትታችሁ ከፍታችሁ ላይ አተኩሩ።
ቁራው ከፍታውን መቋቋም እንዳቃተው እናንተም ከነገሮች በላይ ከፍ ስትሉ የእናንተም ተግዳሮት ከፍታውን መቋቋም አቅቶት ቁልቁል ይፈጠፈጣል ።
መልካም ቀን
@kibirenaw
BY ማራናታ Maranata
Share with your friend now:
tgoop.com/kibirenaw/536