tgoop.com/kibirenaw/540
Last Update:
#ጓደኝነት(ወዳጅነት)_በዛፍ_ይመሰላል ያለው ማን ነበር?
ይህንን የወዳጅነትን መግለጫ ማን እንዳለው ባላስታውስም እውነቱ ግን ይህው ነው።
ወዳጅነት በዛፍ ይመሰላል፦
1) #ቅጠል፤ በቅጠል የተመሰሉት ሲያጅቡ ብዙ ውበት ይሆናሉ። ቶሎ ለሁሉ ይታያሉ። ለሁሉ ሳቢ ናቸው። ግን ምን ያደርጋል በመጀመሪያው ንፋስ ይረግፋሉ። የመከራን ሰአት ወዳጅ መሆን አይችሉም። ጓደኝነታቸው እስከ ንፋሱ መንፈስ ድረስ ብቻ ነው።
2) #ቅርንጫፍ፤ እነዚህ ከቅጠሉ ይልቅ የተቀራረቡ ናቸው። ቅጠሎቹን የተሸከሙ ለመስፋፋት ምክንያት የሆኑ ናቸው። ግን ቢንጠለጠሉባቸው ወይም ልደገፋችሁ ሲባሉ ይዘው ይወድቃሉ። ማስደገፍ የሚችሉበት የወዳጅነት ጥንካሬ የላቸውም። ወዳጅነት የሚያስከፍለውን ዋጋ ስለማይገነዘቡ መነካካትን አይፈልጉም። ለእነሱ መንካት እንጂ መነካት ነውር ነው። ስለዚህ...
3) #ግንድ፤ እነዚህኛዎቹ ወዳጆች (ጓደኞች) አብሮነትን በመከራም በምቾትም ቀን ማስቀጠል የሚችሉ ናቸው። በሁሉ ሁኔታ ውስጥ አብሮ መጽናትን የተማሩ ወይም የቻሉ ናቸው። ደክመሃል ብለው በምድረበዳ ለአውሬ ጥለው የማይሄዱ ጠንካሮች ናቸው። ይጠብቁሃል እንጂ በአደባባይ አያሰጡህም። እንደ ዮናታን ከእነሱ መብት የሚያስቀድሙህ ናቸው።
4) #ስር፤ እነዚህ ደግሞ ታዋቂና በየቅያሱ አብረው የሚታዩ አይደሉም። ቅን ለአንተና ለጓደኝነትህ ሕይወትን ሲመግቡ ይኖራሉ። በጎደኝነት ጉዞ ውስጥ ሁሌም ደግሞ ደግሞ የሕይወት ሽታና ኃይል እንዲኖር የሚተጉ ናቸው።
"ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወዳል፤" ምሳ 17:17
እንደ ግንድም እንደ ስርም የሆነ ጓደኛ እንሁን። ቅጠልና ቅርንጫፍ ለሆኑትም ልብ በመስጠት ጉዳትን አናብዛ።
የእውነት ጓደኛ ነህ? የእውነት የሆኑስ ጓደኞች ዛሬ ላይ አሉህ?
@kibirenaw
BY ማራናታ Maranata
Share with your friend now:
tgoop.com/kibirenaw/540