tgoop.com/kibirenaw/547
Create:
Last Update:
Last Update:
ከአምስት አመት በኋላ!
• የዛሬ አምስት አመት በዙሪያችሁ የሚኖሯችሁን አልሚ ወይም አጥፊ ጓደኞች የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት አመለካከት ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖራችሁን የፍቅር ወይም የትዳር ግንኙነት አይነት የሚወስነው የዛሬ ወዳጅነት ምርጫችሁ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የሚኖራችሁን እውቀት የሚወስነው ዛሬ የምታነቧቸው መጻሕፍትና የምትወስዷቸው ስልጠኛዎች ናቸው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትገቡበትን አዲስ የሕይወት ምእራፍ የሚወስነው ዛሬ ለማድረግ የቆረጣችሁት ለውጥ ነው፡፡
• የዛሬ አምስት አመት የምትኖሩትን የኑሮ ጥራት የሚወስነው ዛሬ ያዳበራችሁት ልማድ ነው፡፡
ጥራት ያለው ሕይወት በአንድ ጀንበር አይመጣም፡፡ በአንድ ጀንበር ብቅ ያለ ነገር ካለም ደግሞ በአንድ ጀንበር ጥልቅ ማለቱ ስለማይቀር ጥራትን ዛሬ ጀምረውና በምንም ነገር እንደማይቀለበስ ሆኖ እንዲበቅል ጊዜ ስጠው፡፡
1. የሕይወታችሁን ዋነኛ ራእይና ዓላማ ለይታችሁ እወቁ፡፡
2. የምትመጧቸውን ጓደኞችም ሆኑ የምትውሉበትን ቦታ ከዚያ ዓላማ አንጻር ቃኙት፡፡
3. አብዛኛው አእምሯችሁን የምትመግቡት አመለካከትም ሆነ የእውቀት ዘርፍ ከዋና ዓላማችሁ አንጻር አድርጉት፡፡
4. የየቀን ልምምዳችሁንና ልማዳችሁን ከዋናው ዓላማችሁ አንጻር ቃኙት፡፡
@Kibirenaw
BY ማራናታ Maranata
Share with your friend now:
tgoop.com/kibirenaw/547