Telegram Web
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ማን ይሉታል ብሎ የጠየቀው ለምን ነበር ?? ❓❓❓❓


ሙሴና ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት ምን ነበረ???❓❓❓❓

አዕማድ ተብለው የሚጠሩትን ሶስቱን ሐዋርያት ጴጥሮስ፣ያዕቆብ፣ ዩሐንስ ለምን ወደ ደብረ ታቦር ተራራ ይዞ ወጣ????❓❓❓❓

የጅራፉ፣ የሙልሙሉ፣ ምሳሌ ምንድነው????❓❓❓❓❓

ሁሉንም መልሱን ዛሬ ማታ ይጠብቁን።።

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
🪴🪴#ደብረታቦር 🪴🪴


ደብረ ታቦር ከገሊላ ባሕር በምዕራባዊ በኩል 10 ኪሎ ሜትር ርቆ የሚገኝ ተራራ ሲሆን፤ ከፍታው ከባሕር ወለል በላይ 572 ሜትር ይሆናል፡፡ በዚህ ተራራ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን እንደሚገልጽ ምሳሌና ትንቢት ተነግሯል፡፡

ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በትንቢቱ â€œá‰łá‰Śáˆ­áŠ“ áŠ áˆ­áˆžáŠ•áŠ¤áˆ á‰ áˆľáˆ á‹°áˆľ á‹­áˆ‹á‰¸á‹‹áˆâ€ á‰ĽáˆŽ የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተአምራቱን በዚህ ተራራ ላይ ገልጧል /መዝ. 88፥12/፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን በቂሳርያ â€œá‹¨áˆ°á‹áŠ• áˆáŒ… áˆ›áŠ• á‹­áˆ‰á‰łáˆ?” á‰ĽáˆŽ ከጠየቃቸው ከስድስት ቀን በኋላ አዕማድ ተብለው የሚጠሩ ሦስቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ ረጅም ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በፊታቸውም ተለወጠ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ፡፡ እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱን ለሙሴ አንዱን ለኤልያስ በዚህ እንሥራ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፡፡ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ ተሰማ፡፡ ሐዋርያት ይህንን ሰምተው የጌታችንን መለኮታዊ ክብር አይተው በፊታቸው ወደቁ እጅግ ፈርተው ነበር፡፡ ጌታችንንም ተነሡ አትፍሩም አላቸው፡፡ በዚህ መልኩ አምላክነቱን ገለጠላቸው /ማቴ. 17፥1-10/፡፡

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
አዕማደ (የምስጢር) ሐዋርያት ለምን ተመረጡ?❓❓❓

አዕማደ ሐዋርያት ተብለው የተጠሩት ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስና ያዕቆብን â€œáŠ á‹•áˆ›á‹ľ áˆá‹‹áˆ­á‹Ťá‰ľâ€ áŠĽá‹Ťáˆˆ ጠርቷቸዋል /ገላ. 2፥9/፡፡ ስያሜውን ያገኙበት ዋናው ምክንያት የኢየሩሳሌምን ቤተ ክርስቲያን በሓላፊነት ያስተባብሩ ስለነበረ ነው፡፡ ከዚህን በተጨማሪ ጌታችን በኢያኢሮስ ቤት ልጁን ሲፈውስ፣ በጌቴ ሴማኒ ሲጸልይና በደብረ ታቦር ምስጢረ መለኮቱን ሲገልጥ ከእሱ ስላልተለዩና ይዟቸው ስለሔደ ነው /ማር.5፥37-43/፡፡

ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሦስቱ ደቀ መዛሙርት የተመረጡበትን ምክንያት ሲያትቱ እንዲህ ብለዋል፡፡ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ሹመት፣ ሽልማትና ክብር ፈላጊዎች ነበሩ፡፡ ከዚህ ሃሳብ እንዲወጡ ከብልየታቸው እንዲታደሱ ለይቶ አውጥቷቸዋል፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ለድኅነተ ዓለም የመጣው በሕማማቱ በሞቱ ቤዛ የሚሆነን አምላክ “#ልሰቀል_ነው” ባላቸው ጊዜ “#አይሁንብህ” ብሎት ነበር፡፡ እንዲህ ያለው ሃሳብ የጠላት እንጂ የሰው ልጆች ሊሆን አይችልም ከሞቱ በቀር ድኀነት ሊያስገኝልን የሚችል የለምና፡፡ ደቀ መዝሙሩ ግን ከሞተ ክብሬ ምንድን ነው ብሏልና “አይሁንብህ” አለ፡፡ /ማቴ. 16/

በሌላም ስፍራ እንዲሁ “ሁሉን ትተን ተከተልንህ እንግዲያስ ምን እናገኝ ይሆን?” በማለት ይጠይቃል፡፡ /ማቴ.19/፡፡ ጌታ ግን ዋጋችሁ ሰማያዊ ክብራችሁ ዘላለማዊ ነው ሲል እስከ ፍጹማን መዓርግ /ነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ/ አድርሶ ብርሃነ መለኮትን ገልጦ ተስፋውን ነገራቸው፡፡

ሁለቱ ወንድማማች ደቀ መዛሙርትም #እናታቸውን_ልከው_ሹመት_ሽልማት መዓርግ ለምነዋል፡፡ ስለዚህም ጌታችን በደብረ ታቦር “በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው ነገር” ስለሞቱ እንዲነጋገሩ አደረገ፡፡ ሞቱ እርግጥ ሆነ ማለት ነው፡፡ አባቱም “ኦሆ በልዎ ለክርስቶስ”፤ እሺ በሉት እርሱን ስሙት፡፡ ሞቱ እርግጥ በመሆኑ ከልባቸው እንዲጠፋ መርጦ ወደ ቅዱስ ተራራ ይዟቸው ወጥቷል፡፡

“እኔ እግዚአብሔር አልለወጥም” áŠĽáŠ•á‹˛áˆ /ሚል 3፥6/ በእርሱ ዘንድ ወረት የለም፡፡ አስቀድሞ ከተዓምራቱ ከምሥጢሩ አይለያቸውም ነበርና ብርሃነ መለኮትን ለማየት አበቃቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለማወቅ፣ ለመማር፣ ለመጠየቅ ያሳዩት ትጋት ምስጢር ተገልጦላቸዋል፡፡ ይህ ምስጢር ለሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተገልጦ የሚቀር አይደለም፡፡ እስከ ዓለም ፍፃሜ እግዚአብሔር ለመረጣቸው ሲገለጥ፣ በመረጣቸውም ሲነገር የሚኖር ነው፡፡

 á‹°á‰€ መዝሙሩ ጴጥሮስ â€œáŠ áˆáŠ­á‹ľáˆ…ም አልተውህም” á‹¨áˆšáˆˆá‹ /ማቴ. 26፥35/ ቢወድደው አይደለምን? ፍቅሩን መግለጡ ለክብር አብቅቶታል፡፡ ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም “ጽዋዬን ልትጠጡ አትችሉም” ቢላቸውም /ማቴ. 20፥22/ አንዳችን በቀኝ ሌላችን በግራ ሆነን አብረንህ እንሞታለን ሲሉ በምስጢር ለምነዋል፡፡ ሞታቸውን ከሞቱ ጋር መደመራቸው ፍቅራቸውን መግለጣቸው ነው፡፡

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
ሙሴና áŠ¤áˆá‹Ťáˆľ áˆˆáˆáŠ• á‰°áˆ˜áˆ¨áŒĄâ“❓❓❓

 #ሙሴንና_ኤልያስን ወደ ደብረ ታቦር እንዲመጡ ያደረገበት ምክንያት የባሕርይ አምላክ መሆኑን እንዲመሰክሩ ነው፡፡

🍂🍂ሙሴን ከመቃብር ተነሥቶ ስለጌታችን እንዲህ የሚል ምስክርነት ሰጥቷል፡-

“እኔ ባሕር ብከፍልም፤ ጠላት ብገድልም፤ ደመና ብጋርድም፤ መና ባወርድም እስራኤልን ከክፋታቸው መልሼ ማዳን ያልተቻለኝ ደካማ ነኝ፤ የእኔን ፈጣሪ እንዴት ሙሴ ይሉሃል? የሙሴ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!”

ኤልያስም ደግሞ ከብሔረ ሕያዋን መጥቶ

“እኔ ሰማይ ዝናብ እንዳይሰጥ ብለጉም፣ እሳት ባዘንብም፣ እስራኤልን ከክፋታቸው ማዳን የማይቻለን ነኝ እንዴት የእኔን ፈጣሪ ኤልያስ ነህ ይሉሃል? የኤልያስ ፈጣሪ እግዚአብሔር ይበሉህ እንጂ!” ብለው የባሕርይ አምላክነቱን በደብረ ታቦር ላይ መስክረዋል፡፡ በማቴ.16፡14 ላይ “አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።” ይላልና፡፡

ሙሴና ኤልያስ የተመረጡበት ሌላው ምክንያት ሙሴ “ጀርባዬንም ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም”  á‰°á‰ĽáˆŽ ስለተነገረለት /ዘጸ.33፡23/ ኤልያስ “በኋለኛው ዘመን ምስክሬ ትሆናለህ” ስለተባለ ያንን ለመፈጸም ነው፤ ካገቡት ሙሴን ከደናግል ኤልያስ ያመጣቸው መንግሥተ ሰማያት በሕግ የተጋቡ ሕጋውያንና ሥርዐት ጠብቀው የሚኖሩ ደናግላን እንደሚወርሷት ለማስተማር ሁለቱን መርጧቸዋል፡፡

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
የደብረ á‰łá‰Śáˆ­ áˆáˆłáˆŒáŠá‰ľ

የወንጌል ምሳሌ ነው፡፡ ተራራ ሲወጡ በጣም ያስቸግራል፤ ከብዙ ድካምና ውጣ ውረድ በኋላ ተራራውን ጨርሰው ከላይ ሲወጡ ግን አባጣ ጎባጣውን ሜዳና ገደሉን ያሳያል፡፡ ወንጌልንም በሚገባ ከተማሯት ጽድቅን ከኃጢአት ለይተን እንድናውቅ ታደርገናለች፡፡

ለቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነው፡፡ በደብረ ታቦር ምስጢረ ሥላሴ እንደተገለጠ በቤተ ክርስቲያንም የቅድስት ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት ይነገርባታል፡፡ ተራራ መሠረቱ ከመሬት አናቱ ከሰማይ እንደሆነ ሁሉ፤ ቤተ ክርስቲያንም መሠረቷ በምድር ሲሆን ልሡ በሰማይ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮቿ የተጠሩት ከምድር (ከዓለም) ሲሆን ክብራቸው ግን በሰማይ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ â€šâ€šáŠĽáŠ›áˆľ ሀገራችን በሰማይ ነውና›› áŠĽáŠ•á‹˛áˆ /ፊልጵ. 3፥20/፡፡

የደብረ ታቦር ተራራ ይህን ሁሉ ምስጢር የያዘ በመሆኑ በክርስትና ታሪክ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ደብረ ታቦር ምሥጢረ መለኮት የተገለጠበት፣ ከዘጠኙ የጌታችን ዐበይት በዓላትም አንዱ ነው፤ በምእመናንም ዘንድ ቡሔ ይባላል፡፡


 á‰Ąáˆ„

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡

ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፤ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡


 áŒ…áˆŤá

 á‰ á‹°á‰Ľáˆ¨ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር ይዞ የሚከወን ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ እንዲሁም ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፣ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡


ችቦ



 á‰˝á‰Ś የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
 https://www.tgoop.com/betelhem29
#ፍቅር_ከለለኝ_ከንቱ_ነኝ‼️‼️‼️‼️

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ

🥀🥀በሰዎችና በመላእክት ልሳን ብናገር #ፍቅር ግን ከሌለኝ እንደሚጮኽ #ናስ ወይም #እንደሚንሽዋሽዋ ጸናጽል ሆኜአለሁ።

🔴ትንቢትም ቢኖረኝ #ምሥጢርንም ሁሉና እውቀትን ሁሉ ባውቅ

🟠ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።

🟡 ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል ሥጋዬንም ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ #ፍቅር ግን ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም።

❤️ፍቅር ይታገሣል፥

💛ቸርነትንም ያደርጋል፤

💚ፍቅር አይቀናም፤

💙ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም
የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥

💜አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤
ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤


💖 ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።
ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም።።።።


1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13 ÷1_8

እግዚአብሔር ለሁላችንም ፍቅርን ያድለን🙏 ከዚህ ሌላ የሚያስፈልገን ነገር የለም።።
ላንተ‼️‼️ላንቺ‼️‼️ ነው‼️‼️

አንድ አባት ሁሌ በቅዳሴ በኪዳን ሁሌ ቤተ መቅደስ ያገለግሉ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን በምስጋና እንዳሉ በተመስጦ ቁጭ ብለው ያለቅሱ ጀመረ እንባቸው መሬት ጠብ..ጠብ አለ። ምእመኖቹ ጨነቃቸው ምን ሆነው ይሆን ብለው አዘኑ። መምህሩ ባፋቸው የሚሉት ነገር አላቸው። ጠጋ ብለው አደመጧቸው "
#ጌታዬ_ሆይ_እባክህ_ለቅዱስ_ስጋህና #ለክቡር_ደምህ_አብቃኝ" ነበር የሚሉት።

ምእመናኑ ተገርመው አባ ምነው ምን እያሉ ነው ብለው አፋጠው ያዟቸው። እርሳቸውም "አንተን ለማገልገል ለስጋና ለደምህ አብቃኝ" እያልኩ ነው። አሏቸው። ምእመኖቹም አባታችን ይህን ያክል ዘመን እያገለገሉ እንኳን ለርሰዎ እኛን እያቆረቡ እንዴት እንድህ ይላሉ አሏቸው።


እርሳቸውም "
#የመስቀሉ_ፍቅር_ገብቶኝ ለሰው ሳይሆን ለራሴ ብየ የማገለግልበት ስጋና ደሙንም ፍቅሩ ገብቶኝ የምቀበልበትን ቀን ነው የምለምነው" ብለው መለሱ።

ወዳጆቼ

✍✍✍✍✍✍
ብዙ ጊዜ እንዲህ አይነት ክርስትና በየሰፈሩ አለ። ለስው የምንሰራ ወይም ግዴታ ተጥሎብን የምናገለግል ብዙ ነን። "አገልግሎት ማለት የፈቃደኝነት ባርነት ነው" እንዲሉ በእንዲህ መልኩ መጓዝ ሲገባን ሰው አይተን ጀምረን በሰው አገልግሎት ያቆምን ብዙ ነን። አንዳንዶቻችን፦ ቤተ ክርስቲያን መሄድ፣ መፆም፣ መስገድ፣ መፀለይ፣ መቀደስ፣ መዘመር፣ መስበክ፣ነጠላ መልበስ ግዴታ አልያም ህግ ነው ብለን የምንተገብር ብዙ ነን።
#መቼ_ነው_ግን_ፍቅሩ_ገብቶን_ስለፍቅሩ እነዚህን የምንተገብራቸው። ሰው ያየናል ይደረስብናል ብለን ሃጢአትን ከመስራት የምንከለከል ብዙ ነን።


አምላክን ፈርተን ሲኦል እንገባለን ብለን ክፉ ነገርን ሁሉ እንተዋለን። ግን ስለ ፍቅሩ ብለን ፍቅሩ ገብቶን ሃጢአት የሆነውን ሁሉ የምንተወው መቼ ይሆን? ወገኖቼ እየሰበክን እየዘመርን እያስቀደስንና እየቀደስን ያልዳን አለንና እርሱ ፍቅሩን ይሳልብን።።።። ሌላ ምንም አልላችሁም ‼️‼️‼️‼️‼️

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
ቤተ ማርያም


🌷🌷🌷 ጳጉሜን 🌷🌷🌷


12ቱን ወራት (360ውን ቀናት) በእድሜና በጤና ያቆየ::
ይልቁኑ በሃይማኖታችን ያሰነበተን የቅዱሳን አምላክ #መድኃኒታችን #እግዚአብሔር . . . ቸርነቱ ምን ይረቅ!!! ምንስ ይጠልቅ!!!

<< #የእመ_ብርሃን áˆáˆáŒƒáŠ“ #የቅዱሳኑ áˆ¨á‹ľáŠ¤á‰ľáˆ ድንቅ ነው:: >>

☞የነደደው ኃጢአት፡ መከራ፡ ስጋትና ፍርሐት ይወገድ ዘንድም ንስሃ እንግባ! ንስሀ ግቡ አላልኩም ንስሀ እንግባ ነው።። መፀፀቱን ያድለን  ከድፍረት ኃጢአት ይሰውረን በምህረቱ ብዛት እስከዚች ዕለት ደርሰናልና የአባቶቻችን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን።።
🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴

እንዲሁ እስካሁት አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን።። በአዲሱ አመት በተሻለ ለመቅረብ የእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልኝ 🙏🙏🙏🙏
ጾመ_ጳጉሜ___ ቤተ_ማርያም በቴሌግራም.pdf
79 KB
ስለ ጾመ_ጳጉሜ ጠቅለል ባለ መልኩ

Size 80Kb

Title__ጾመ ጳጉሜ



https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
ጳጉሜን ማለት ምን ማለት ነው
Anonymous Quiz
4%
ተውሳክ
43%
ጭማሪ
54%
ሁለቱም መልስ ነው
ጳጉሜ ወይም ጾመ…… ማን ትባላለች
Anonymous Quiz
11%
ጾመ ጽጌ
81%
ፆመ ዩዲት
7%
ጾመ ነቢያት
🌻🌻🌻🌻#ቤተማርያም🌻🌻🌻🌻

#ጳጉሜን_3
እንኳን ለርኅወተ ሰማይ: ለቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።


🌿🌿 ርኅወተ ሰማይ

🌿🌿 ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት: አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት: ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ-ሰማይ የሚከፈትባት ቀን::" ትባላለች::

አሁን በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም:: የሰው ልጆችን #ልመና_ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት: አንድም #ቅዱስ_ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ::

#እመቤታችን_ድንግል_ማርያም #ለአጼ_ናዖድ እንደ ነገረቻቸው

👉👉በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ: #የእግዚአብሔር_የምሕረት መዝገቡ #ስለሚከፈት_ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል:: በቅዱስ ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት #ለዓመት_የሚበቃ_ምሕረት ይገኛል::

#ስለዚህም_አባቶቻችን_በዚህች ሌሊት ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ:: በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል::
ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን::አሜን

ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት

🌿🌿🌿🌿ቅዱስ ሩፋኤል በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት በደረጃው ሦስተኛ ነው:: በመጀመሪያዋ ዕለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክትን ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው የቅዱስ ሩፋኤል ዕድል ፈንታው ራማ ሆነች::

በዚያም "መናብርት" ተብለው ለሚጠሩ አሥሩ ነገድ አለቃ (መሪ) ሆኖ በፈጣሪው ተሹሟል:: በኋላም "መጋብያን" በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ሹሞታል:: ይህች ዕለትም በዓለ ሲመቱ ናት::

አንድ ቀን ጌታችን ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ሐዋርያቱ ቅዱስ ሩፋኤልን እንዲያስተዋውቃቸው ለመኑት:: ጌታም ሦስቱን ሊቃናት (ሚካኤል: ገብርኤል እና ሩፋኤል) ይመጡ ዘንድ አዘዛቸው::

ቀጥሎም ቅዱስ ሩፋኤልን "ክብርህን ንገራቸው::" አለው:: እርሱም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምሥጢር ነገራቸው:: በተለይ ስሙን ለሚጠሩ: መታሰቢያውን ለሚያከብሩ የሚደረገውን ጸጋ አብራርቶላቸው ዐረገ::

በመጽሐፈ ጦቢት ላይ ተጽፎ እንደምናገኘው ቅዱሱ መልአክ ሰው (አዛርያን) መስሎ: ጦብያን ለትዳር አብቅቶ: ሣራን አስማንድዮስ ከሚባል ሰይጣን አድኖ: የጦቢትን ዓይን አብርቷል:: በገድላተ ቅዱሳን እንደምናየውም ለብዙ ቅዱሳን ረዳታቸው ሆኖ ገድላቸውን አስፈጽሟል::

ታሪክ እንደሚለው ይህች ቀን ለቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱም ናት:: በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በቅዱስ #ቴዎፍሎስ ዘእስክንድርያ አማካኝነት ቤቱ ታንጿል:: የሚገርመው ደግሞ የታነጸው በዓሣ አንበሪ ጀርባ: ደሴት ላይ ነው:: በመልአኩ አጋዥነትም ለሦስት መቶ ዓመታት አገልግሏል::

#ቅዱስ_ሩፋኤል

መስተፍስሒ (ልቡናን ደስ የሚያሰኝ)
አቃቤ ሥራይ (ባለ መድኃኒት ፈዋሽ)
መዝገበ ጸሎት (#የጸሎት_መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው)
ሊቀ መናብርት (በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ)
#ፈታሔ_ማኅጸን (የሰውንም ሆነ የእንስሳትን ማኅጸን የሚፈታ)
¤መወልድ (አዋላጅ: ምጥን የሚያቀል) ይባላል::
"ለሰብእ ወለእንስሳ ፈታሔ ማኅጸኖሙ አንተ" እንዲል::

https://www.tgoop.com/kidstarsema6
🌷🌷🌷🌷#ቤተማርያም 🌷🌷🌷
🌻🌻🌻🌼🌼🌼🌷🌷🌷🪴🪴

#ጳጉሜን 3

ይህ መዝሙር ደግሞ ዝናብ እየዘነበ የምንዘምረው መዝሙር ነው።።።።።።።



ሩፋኤል ደገፋየ
እንደ እማየ እንደ አባየ

ትልቅ ልሁን አሳድገኝ
ከክፉ ሁሉ ታደገኝ

ፀበልህን ተጠመኩት
ዝናብ ሁኖ አገኘሁት

በጳጉሜን ወር አመቱ ሲያልቅ
በረከትህን ስንጠብቅ

ይኸው ሰማይ ተከፍቶልን
በረከትህ ወረደልን

የዛሬ አመት እንመጣለን
በዚች ቀን ልብስ አውልቀን


🌧🌧
@KIDSTARSEMA6🌧🌧
🌧🌧
@KIDSTARSEMA6🌧🌧
🌧🌧
@KIDSTARSEMA6🌧🌧
🌧🌧
@KIDSTARSEMA6🌧🌧
ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ


🌼#ልጄ_ሆይ..ወጣትነት ፈትኖ፤ለስጋህ አድልተህ ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

🌻#ልጄ_ሆይ .. በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ

🌷#ልጄ_ሆይ ... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ

🌱#ልጄ_ሆይ . በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

🪴#ልጄ_ሆይ ... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

🍇#ልጄ_ሆይ ..ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

🌧#ልጄ_ሆይ ...ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

🍁#ልጄ_ሆይ ..የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

💐#ልጄ_ሆይ..አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
ለእግዚአብሔር የቀረበ የአዲስ ዓመት ልዩ ሥጦታ

በአንድ ወቅት አንድ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፊት ቆሞ "ጌታዬ ሆይ! አንተ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ? ምንስ ባደርግልህ ደስ ትሰኛለህ? . . እስቲ ንገረኝ ረጅምና በቁመቴ ልክ የሆነ ከሰም የተሠራ ሻማ እንዳመጣልህ ትፈልጋለህ?" አለው። ጌታም መልሶ "ለሻማው መሥሪያ የሚሆነው ሰሙም የእኔ ነው ፤ ሰሙ የሚገኝበት የማር እንጀራውም የእኔ እኮ ነው" አለው።

ሰውየውም መልሶ "ይሁን እንግዲህ ፤ ወይ ለሰንበት ቅዳሴ የሚሆን ለሥጋወደሙ የሚሆን መገበሪያ ይዤልህ እመጣለሁ" አለ። ጌታችንም መልሶ "ሥጋወደሙ የሚዘጋጅበት ስንዴም ቢሆን የእኔ እኮ ነው" አለው።

ያም ሰው ቀጥሎ "እንግዲያውስ ድኆችን ለመርዳት ይሆን ዘንድ 100,000 ብር እሰጥሃለሁ" አለው። ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "አንተ አለኝ ያልኻቸው ነገሮች ሁሉ የእኔ ናቸው ፤ 'ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።' (መዝ. 24:1)" አለው።

ሰውየውም እንዲህ አለ "ጌታዬ ሆይ! እሺ . .ምን እንዳመጣልህ ነው የምትፈልገው?"

ኢየሱስ ክርስቶስም መልሶ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ ፤ ስለ አንተ ብዬ ተጠምቼአለሁ ፤ ስለ አንተ ፍቅር መስቀል ላይ ወጥቻለሁ" አለው።

+++

+ እግዚአብሔር ካለን ነገር በፊት እኛን ይፈልገናል። ራሳችንን ሳንሠጠው ብንደክም ብንለፋ "የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው" (ሉቃ. 10: 42) ይለናል ፤ ይህም ልባችንን ለእርሱ(በቃሉ ለመኖር) መሥጠት ነው።

+ እውቀታችንን ሠጥተን ፣ ገንዘባችንን ሠጥተን ፣ ጉልበታችንን ሠጥተን እኛ የእርሱ ካልሆንን ምን ይጠቅማል? ኃጢአት ከእርሱ ለይታናለችና ፣ በንስሓ ልባችንን እንድንሠጠው ፤ በመንፈሳዊ ምሥጢራት ከእርሱ ጋር አንድን እንድንሆን ይሻል። ስለዚህ በአዲሱ ዓመት ራሳችንን ለንስሓ አቅርበን ልባችንን እንሥጠው!!!

🌻 መልካም አዲስ ዓመት 🌻

https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ ዐዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።

መንፈሴንም በውስጣችሁ አኖራለሁ በትእዛዜም አስሄዳችኋለሁ ፍርዴንም ትጠብቃላችሁ ታደርጉትማላችሁ።

https://www.tgoop.com/kidstarsema6
#ወዳጄ_ሆይ!!!!!!

❓❓ቤቱ ቆሽሾ ሳለ ውጫዊ በሩን ብቻ ለማሽቀርቀር ለምን ትጨነቃለህ????????

❓❓ነፍስህ በኀጢአት ተዳድፋ ሳለ ሥጋህን ብቻ ለማስደሰት ለምን ትሮጣለህ????????

❓❓ አስቀድመህ ቤቱን (ነፍስህን) ለማስዋብ አትሽቀዳደምምን?????

አስቀድመህ ለነፍስህ የምታስብ ከኾነ ከሰው እጅ ሳይኾን ከክርስቶስ እጅ ሹመት ሽልማት ትቀበላለህ፡፡ ኹል ጊዜ “የማደርገው ነገር እግዚአብሔር ይከብርበታልን?????” ብለህ አስብ እንጂ እንዲሁ በዘልማድ የምትመላለስ አትኹን ብዬ እመክርኻለሁ፡፡።።።

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጳውሎስ_ሲመክረን፡- “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትኾኑ ወይም ማናቸውም ነገር ብታደርጉ ኹሉን #ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት”

ያለንም ስለዚሁ ነውና
#በአዲሱ_ዓመት በድርጊቶቻችን ኹሉ እግዚአብሔርን ለማክበር እንዘጋጅ (1ኛ ቆሮ.10፡31)

👉👉👉👉
#አዲስ_ዓመት_ማክበር_ማለት_ይኼ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
https://www.tgoop.com/kidstarsema6
"#እገድልሐለሁ_ያልከኝ_እውነትም_ገደልከኝ።"

በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን
ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሠውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስጸያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውሐ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብህ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሠውየውን "እገድልሐለሁ።" ብሎት ይሄዳል። ሠውየውም ይሄ ዲያቆን እገድልሐለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው? ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል።

. ከእለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሠዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ
ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው
ሠውየ ልጅ መሆኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ
ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሠውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል
ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ? ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን
አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሠውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ "እገድልሐለሁ ያልከኝ
እውነትም ገደልከኝ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? " ሲለው
ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይህን ብቻ
ነው።" ብሎ አለው።

.በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሠውየዉን እገድልሐለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው
ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልሐለሁ ያልኩት ሠውየውን
አይደለም እኔ እገድልሐለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው።
#እግዚአብሔርም
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን
ገደልኩት።" ብሎ አላቸው።

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
እንሆ፥የባሪያዎች ዐይኖች ወደጌታቸው እንደ ሆኑ፥የባሪያዪቱም ዐይን ወደእመቤቷ እጅ እንደሆነ፥እንዲሁ እስኪምረን ድረስ ዐይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው።

መዝሙር 122÷2

#መልካም_ዕለተ_ሰንበት

https://www.tgoop.com/betelhem29
https://www.tgoop.com/betelhem29
2025/01/07 11:16:11
Back to Top
HTML Embed Code: