tgoop.com/kinexebebe/10035
Last Update:
# ስንት ቀን ፈጀብህ?
/መንፈሳዊ መነባንብ /
-----------------✞-------------------
ለአዳም ኪዳን ሰጠህ
እንደምትወለድ ወደ ምድር ወርደህ
እንዴት ነበር ያኔ..?
ወደ እኛ ስትመጣ መላእክትን ትተህ?
………
የሔዋን እርግማን
የባሏም የውርስ ኃጢአት መዘገን
እንዲያ አሳሰበህና
መጣህልን ሁሉን አደረግህ በፅሙና
.........
እንዴት ነበር ያኔ..?
ያችን ንጹሕ ለመፈለግ የወሰደብህ ጊዜ
አድርገህ የሰጠኸንን ፈውስ በበድልን ጊዜ
ግን ምን ያህል ነው ልፋትህ?
ድንግልን ስትፈልግ የፈጀብህ?
.........
ከሰማያት ስትወርድ አጀቡህ መላእክት?
ዓለሙስ ተናወፀ በይባቤ በስብሐት?
ያ ምቀኛ ዲያቢሎስ ግን ምን አለ?
ወደ እኛ ስትመጣ አለ አይደል ኮበለለ?
ነው ሥጋ ለብሶ ጉድ ሠራኝ አለ?
........
እንዴት ነው እርቀቱ
የሰማይ ምጥቀቱ
የምድርስ ሥፋት
ከሷ እስክታርፍባት?
ግን ጌታ...?ሰማያት ምን አሉ
ትትሀቸው መጠህ ባንተ አጉረመረሙ?
ፍጥረታትስ ቢሆን ማሕሌት አቆሙ?
.......
ምሥጢረኛው ጌታ
መንገድህ በየት ነው ወደ እኛ ስትመጣ?
ቤተ ልሔም ስትደርስ
ማን አገለገልህ?ምን አለች ምድሪቱስ
እያቄም ወሐናን እንዴት መረጥሃቸው
አንተ እንድትወለድ ምክንያትህ ናቸው
.......
ሰማዩ ሰፊ ነው
ምድርንም ታውቃለህ
እንዴት እንድትሰፋ ሆና መረገጫህ
ግን እና ጌታ ሆይ ምኑ ነው የቻለህ?
የድንግል ማሕጸን እሳት መሸከሙ
ምድርም መልኮት በእሷ ላይ መቆሙ
..........
እንዴት ነበር ያኔ
በቤተ ልሔም ውስጥ
አንተን የሚያሞቅ ከእንስሶች ስትሰጥ?
........
ዮሴፍ ምን አለ
አንተን በማየቱ እርጅናው ታጎለ?
አንተን የጠበቀህ አዳምስ በግርማህ ምን አለ?
........
እንዴት ነው ስጦታው
የሰብአ ሰገሉ ወርቅ እጣን አምኃው
የእረኞቹ ደስታ
የመላእክት ብሥራት የልደትህማታ
.........
እንዴት ነበር ያኔ
የልደትህ ማታ
የዝማሬው ለታ
የእናትህ ደስታ
የፍጥረት እልልታ
ሚዳቋ ስትዘል ከኢትዮጵያ አይታ
ግን ጌታ እረቂቁ አምላክ
በየትስ መጠህ ነው ከኛ የተወለድክ
✞
✞ስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞
✞
*ከሮቤል ጌታቸው
@kinexebebe
BY መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
Share with your friend now:
tgoop.com/kinexebebe/10035