tgoop.com/linkortodoxe21/2425
Last Update:
3.አንድም ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር መገኝታቸው ሙሴ በምድር ላይ እጅግ ትሁት ሰው ነበረ
“ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።”
— ዘኍልቁ 12፥3
ኤልያስ ደግሞ እጅግ ቀናተኛ ነበረ ለአምልኮተ እግዚአብሔር የሚቀና
“በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፦ በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም አለው።”
— 1ኛ ነገሥት 17፥1
ሰማይን የሚለጉም እሳትን የሚያወርድ ነውና ኤልያስን በደብረ ታቦር ጠራው ይህ ሚስጥሩ ምንድነው ቢሉ
የእኛ አገልግሎት እንደ ሙሴ በትህትና እና እንደ ኤልያስ በመንፈሳዊ ቅናት ከሆነ እግዚአብሔር አገልግሎታችንን እንደሚቀበል ከፍ ወዳለው ክብር እንደሚያሸጋግረን ሲያስተምረን ሲነግረን ነው።
4.አንድም ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሕግ ተሰቶታል ኤልያስ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ጠብቃል በዛም ኃይለኝ ማቅ የለበሰ አመድ የነሰነሰ ሰማይን የመዝጋት የመክፈት እሳት የማውረድ በእሳት ሰረገላ የማረግ ስልጣን አጊንታል እና ጌታችን በደብረ ታቦር ሙሴና ኤልያስ መጥራቱ ሕግን እንደ ሙሴ ተቀብለን እንደ ኤልያስ በቅንነት መተግበር እንዳለብን ሲነግረን ነው።
5.አንድም በደብረ ታቦር ላይ ከብሉይ ሙሴና ኤልያስ ከሐዲስ 3ቱ ሀዋርያት መገኝታቸው ጌታችን የብሉይ እና የሐዲስ ጌታ አምላክ እኔ ነኝ ሲለን ነው
6.አንድም ከብሉይ ነብያትን ከሐዲስ ሐዋርያትን ያስገኝበት ነብያት ስለ እኔ የተናገሩልኝ ሐዋርያት ስለእኔ የሚመሰክሩልኝ አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ሲል ነው
7.አንድም ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር መገኝታቸው ሁለቱም ሊያዩት ይመኙ ስለነበረ በኃለኛው ዘመን ታየኝለህ ብሎ ለሙሴ ቃል ስለገባለት ኤልያስም ብዙ ጊዜ ሊያየው ይመኝ ስለነበረ በብሉይ ለምን አላዩትም ቢሉ እግዚአብሔር በብርሀነ መለኮቱ አይቶ መቆም የሚችል ፍጥረት ስለሌ በኃለኝው ዘመን ሰው ሆኖ ታያቸው።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#join #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
BY ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
Share with your friend now:
tgoop.com/linkortodoxe21/2425