tgoop.com/linkortodoxe21/2437
Last Update:
አዲሱ አመት ባርክልን
አሮጊ አመት አልፎ አዲሱ ዘመን መጣ
ምድረ በዳው ሁሉ አበባን እንዲያወጣ
ጭጋጉ ዝናብ ዘመኑን ጨርሶ
ርዕሰ አውዳመት መጣ ተመልሶ/2/
በአድይ አበባ ምድሩ ተንቆጥቁጦ
ጨለማው በብርሃን ደምቆ ተለውጦ በወርሃ መስከረም ቅዱስ ዮሐንስ
እንደ ምን ደስ ይላል ጌታ ሲወደስ
አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርክልን/4/ አዲሱ አመት ባርክልን
አውዳመቱን ባርክልን /2/
/አዝ====
የጠራውን ሰማይ እንድናይፈቀደ አዲስ
ቀን ሊሰጠን እግዚአብሔር ወለደ
በዳዩን ሰውነት ጥለን እንድንመጣ
ለአዲስ ማንነት አዲስ አመት መጣ
አበባ አየሽ ሆይ እንበል/4/ .............
/አዝ =====
በችቦ ብርሃን ስንሰንቅ ተስፋ ችግርና
ስደት ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ እንዲሰማን
አምላክ ምህረት እንዲመጣ ከወቀልና
ግፍ ከቁጣም እንድንወጣ
አበባ አየሽ ሆይ /4/ ................
/አዝ =====
በዙፋኑ ያለ በዘመን የሚኖር አመትን ሊሰጠን ስለ ድንግል ብሎ ልክ እንደ ዘመኑ ልባችን ይለወጥ በቀኙ እንድንቆም ለፍርድ ሲቀመጥ
አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን /2/
/አዝ =====
በተሰጠሽ ኪዳን ባንቺ አማላጅነት
ለአስራት ሃገርሽ ይምጣላት ምህረት
የፍቅርን ሸማ ኢትዮጵያ ትልበስ
እርጋታን ያድላት የእግዚአብሔርመንፈስ
ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን
አርቲስት ዘማሪ ይገረም ደጀኔ /አስቴር /
ዘማሪ ዲ/ን ሄኖክ ሞገስ
╔✞═══●◉❖◉●═════7
✥ @linkortodoxe21 ✢
╚✞═══●◉❖◉●═════✞╝
✍ ዜማ ቅዱስ ያሬድ
BY ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
Share with your friend now:
tgoop.com/linkortodoxe21/2437