tgoop.com/linkortodoxe21/2439
Last Update:
ሌሎች የእንቁጣጣሽ መዝሙሮችን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forwarde በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን
🌺🌼አበባዮሽ🌺🌼
እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(፪)🌼
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን🌻
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ዘመን መጣ ብለን
🌼🌼
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ባልንጀሮቼ - - - ለምለም
ግቡ በተራ - - - ለምለም🌼
በእግዚአብሔር መቅደስ - - - ለምለም
በዚያች ተራራ - - - ለምለም
እንድታደንቁ - - - ለምለም
የአምላክን ሥራ - - - ለምለም
ህይወት ያገኛል - - - ለምለም
እርሱን የጠራ - - - ለምለም
🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼
አበባዮሽ - - - ለምለም (፪)
ክረምት አለፈ - - -ለምለም
ጨለማው ጠፋ- - - ለምለም
የመስቀሉ ቃል - - -ለምለም
ሆነልን ደስታ - - -ለምለም
እናገልግለው - - - ለምለም
ቤቱ ገብተን - - - ለምለም
ትንሽ ትልቁ - - - ለምለም
ተሰልፈን - - - ለምለም🌾
🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼
አበባዮሽ - - -ለምለም(፪)
ያንን ኩነኔ - - - ለምለም
ዘመነ ፍዳ - - - ለምለም
የሞቱ በራፍ - - - ለምለም
ያ ምድረበዳ - - - ለምለም
ልክ አንደ ክረምት - - - ለምለም
ሄደ ተገፎ - - - ለምለም
ፀሐይ ወጣልን - - - ለምለም
ጨለማው አልፎ - - - ለምለም🌼
🌸አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌺
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው መስከረም - - - ለምለም
ይኸው ፀሐይ - - - ለምለም
ንጉሡ ወርዶ - - - ለምለም
ከላይ ሰማይ - - -ለምለም🌼
አውደ ዓመት ሆነ - - - ለምለም
ደስታ ሰላም - - - ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ - - - ለምለም
በአርያም🌿 - - - ለምለም
💐አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌻
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው አበባ - - - ለምለም
ለምለም ቄጤማ🌾 - - - ለምለም
አዲሱ ዘመን - - - ለምለም
አምጥቷልና - - - ለምለም
በሩን ክፈቱ - - - ለምለም
መኳንንቶቹ - - - ለምለም
የክብር ንጉሥ - - - ለምለም
ይግባ ቤታችሁ - - - ለምለም
🌹አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪) 🌼
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ቤታችሁ ይሙላ - - - ለምለም
ሰላም ደስታ - - - ለምለም🌼
ሰጥቷችሁ እርሱ - - - ለምለም
የሁሉ ጌታ - - - ለምለም
ከዘመን ዘመን - - - ለምለም
ያሸጋግራችሁ - - - ለምለም🌺
የሽበትን ዘር - - - ለምለም
ይሸልማችሁ - - - ለምለም
🌼አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ🌼
ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ🌼
አብዬ ኧኸ አባብዬ
ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ🌺
ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት
አደረሰዎት ብዬ💐
🌼
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው🌼
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው🌸
መዝሙር
🌺በዘማሪያን🌼
ወርቅነሽ ተፈራና ፅጌሬዳ ጥላሁን
<< በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል >>
መዝ ፷፭፥፲፩🌼
@linkortodoxe21
BY ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
Share with your friend now:
tgoop.com/linkortodoxe21/2439