tgoop.com/linkortodoxe21/2442
Last Update:
✟የአዋጅ ነጋሪው ቃል✟
የአዋጅ ነጋሪው ቃል በበረሃ አየለ
የእግዚአብሄርን መንገድ አስተካክሉ እያለ
ምስክርነቱን ዮሃንስ ካስረዳ
ልባችን ለጌታ መልካም መንገድ ይሁን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
ተራራው ዝቅ ይበል ጠማማውም ይቅና
ካልተስተካከለ መንገድ የለምና
የእግዚአብሄርን መንግስት እንመስክር ሁላችን
ማረፊያ እንዲሆነን ለመጪው ሀብታችን
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
ዘማ___________________
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
ዘማ-___________________
ሁለት ልብሶች ያሉት ከማብዛት ልብስን
ለሌለው ያድለው ሁለተኛውን
ከበደላችን አንጻን አደራህን
በክፋ እንዳንጠፋ እኛ ባሮችህ
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገደማ
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
ዘማ-___________________
ክፋትና ተንኮል ከልባችን ይጥፋ
ጽድቅና ርህራሄ በእኛ ላይ ይስፋፋ
ስጋና ደምህን በክብር አግኝተናል
ህይወት እንዲሆነን አምላክ ተማጽነናል
የደናግል መመኪያ የነቢያት ገዳም
አወደ አመቱን ባርኪልን ድንግል ማርያም/2/
እ______ን_______ዘ______ም___ር
@linkortodoxe21
BY ✝መንፈሳዊ ህይወት✝
Share with your friend now:
tgoop.com/linkortodoxe21/2442