Telegram Web
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
😍እንካን ለ126ተኛው የአድዋ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን

'''ወስልተህ የቀረህ እንደሆን ማርያምን ትጣላኛለህ'''

"አንተ ፀጉረ ልውጥ የአውሮጳ ሰው ባህልህን ሳይሆን ስልጣኔህን ላክልኝ"

"የአገር ሰው አንተ ትውልዱ የአንገትህን ማህተብ ሳትፈታ ባህልህን ሳትጥል እንደ ባህር ማዶ ሰው ሰልጥን"

@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ(የአርምሞ አባት) በድካም ከዚህ ዓለም አርፈዋል
በረከታቸው ይደርብን🙏🙏🙏
🙏በረከታቸው ይደርብን
ዓብይ ጾም››

ጾም የቃሉ መሠረታዊ ትርጉም መታቀብ መከልከል ማለት ነው በቤተክርስቲያናችን እምነትና ትምህርት ጾም ማለት የሰው ልጅ ሕይወቱን ለሰጠው የሕይወትን መመሪያ ላዘጋጅለት ፈጣሪ እየታዘዘ ኃጢዓትን ለማስተሰረይ የምኞት ፍትወትን ኃይል አድክሞ ሥጋ ለነባቢት ነፍስ ትገዛለት ዘንድ በሕግ በታወቁ ጊዜያት ከመብል መጠጥ በመከልከልና የመንፈስ ብርታት ማግኛ የጥበብ መንገድ ነው::

ጾም ጸሎት ምጽዋት የተያያዙ የሥነ ምግባር ሰንሰለቶች ስለሆኑ በተግባር ተጠብቀው ሲተረጎሙ የእኛንም ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር ያገናኛሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እንደምናነበው አበው ማንኛውንም ሥራ ለመሥራት ሲያስቡና ሲያቅዱ፣ ሲጀምሩና ሲፈጽሙ በጾም በጸሎት ነው፡፡

ሐዋርያው ጳውሎስ ‹‹የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ›› እንዲል (ኤፌ 6፡10) የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር የተባሉ መሣሪያዎች ጾም፣ ጸሎት ፣ ምጽዋት አጠንክሮ የሚጠቀምባቸው ክርስቲያን የችግርን ጊዜ የማለፍ ኃይል ይኖረዋል፡፡

ጸሎት እምነት እንዲለመልም እንዲፋፋ እንዲያፈራ ይረዳል፣ ጾም ደግሞ እምነትን ጸሎትን እያጠናከረ ብዙ ድንቅ ሥራዎች እንዲሰሩ ያደርጋል፡፡

ጾም ነፍስን በእግዚአብሔር ፊት ትሑት ያደርጋል የሥጋን ፈቃድ አስገዝቶ ነፍስ እንድትነፃ እንድትቀደስ አቋሟን እንድታስተካክል ይረዳታል ጾም ለነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋ ሕይወትም ለሆድ ዕቃዎች (ለሰውነታችን) የውስጥ የምግብ ማዘጋጃ ክፍሎች ዕረፍትን ይሰጣል ጾም ትሑትና ቅን ያደርጋል በሥጋዊ ፍላጎቶቻችን ፈቃዶቻችን ላይ አዛዦች መሆናችንን ያረጋግጥልናል፡፡

ጾም ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ተቃራኒ በሆኑ ርኩሳን መናፍስትና በአጋንንት ላይ ኃይል እንድናገኝ ከፈተናዎች እንድንድን ይረዳል ክህደትን ጥርጥርን ያጠፋል እምነትንና በእምነት የምንሰራቸውን ሥራዎች ያጠናክራል የጥበብን መንገድ የሕይወትን ጎዳና ይገልፃል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትና ድንጋጌ (የሕግ ምንጭ) በሆነው ፍትሐ ነገሥት ስለጾም በተመለከተው አንቀጽ እንደተገለጸው ጾም

_ ጾመ ሕግ

_  ጾመ ፈቃድ ተብሎ በሁለት ይከፈላል

ጾመ ሕግ ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ የኒቂያ ጉባኤ ሊቃውንት አበው በወሰኑት መሠረት ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ላይ የተመለከቱትና ክርስቲያኖች ሁሉ እንዲጾሟቸው የታዘዙት አፅዋማት ሰባት ሲሆኑ

ዐብይ ጾም

ጾመ ድህንት (ረቡዕና ዓርብ)

ጾመ ነነዌ

የልደትና ጥምቀት (ጋድ/ገሐድ ጾም)

የሐዋርያት (የሰኔ) ጾም

የነቢያት (የገና) ጾም

የፍልሰታ ጾም ናቸው

እነዚህ አጽዋማት የየራሳቸው የሆነ ታሪክና ትንታኔ ያላቸው ሲሆኑ ሁሉም ያለ ልዩነት በሁሉም ክርስቲያኖች በይፋ በማህበር እንዲጾሙ የተወሰኑ ናቸው፡፡

ጾመ ፈቃድ በግል ውሳኔ በኀጢዓት ስሜት የሻከረ ኅሊናን ለማጥራት ወይም ቅድስናን ጸጋና የበለጠ መንፈሳዊ ክብር ለማግኘት በመምህረ ንስሐ አማካኝነት አለዚያም ብቻ ለብቻ በሥውር አይቶ በግልፅ የሻቱትን ለሚሰጥ አምላክ የሚቀርብ ነው፡፡

ከሕግ አጽዋማት መካከል በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አቢያተ ክርስቲያናት እምነትና ሥርዓት በየአመቱ ከሚመላለሱት አጽዋማት ዋናውና ትልቁ ጾመ ሁዳዴ (አብይ ጾም) ነው፡፡

ይህንን ጾም የምንጾመው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን  አብነትና አርአያ አድርገን ነው:: አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ከመጀመሩ በፊት በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ በኋላ ሳይውል ሳያድር ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ በመሄድ ከቆመ ሳይቀመጥ፣ ከዘረጋ ሳያጥፍ እህል ውሃ ሳይቀምስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾሞ የዚህ ዓለም ተፈታታኝ የሆነ ዲያብሎስን ከነፈተናው ድል ነስቶታል፡፡ በስስት ፣ በትዕቢት፣ በፍቅረ ንዋይ የመጣውን ፈተና አጥፍቶ የኃጢዓትን እሾህ አቃጥሏል፡፡

–    ስስት ያልተሰጡትን መሻት የሌሎችን ድርሻ በይበልጥ ለመሻማት መሞከር

–    ትዕቢት አምላክ እሆናለሁ ማለት በሌሎች ላይ ታላቅነትን፣ የበላይነትን መመኘት

–    ፍቅረ ንዋይ ያለኝ ይበቃኛል አለማለት በተሰጡት አለማመስገን ነው
እነዚህ ሦስቱ አርዕስተ ኃጣውዕ ይባላሉ፡፡ እያንዳንዳችን የልቡናችን በር ከፍተን እንደገና ካላስገባናቸው በቀር በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጾም ተወግዷል

ሀ/ ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመ

እርሱ ሠራዔ ህግ (ህግን የሠራ) ነውና፣ ሕግንና ነቢያትን ያጸና ዘንድ አንድም ሕግን ይሠራ ዘንድ ጾምን የሥራው መጀመሪያ አደረገ

አንድም ለሐዋርያት ለሊቃውንት እንዲሁም ከዚያ በኋላ ለሚነሱት ክርስቲያኖች ሁሉ አርአያና ምሣሌ አብነትም ለመሆን 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ሥራ ጀምሯል፡፡ ከዚያ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ከእርሱ በተማሩት መሠረት የሥራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ጾምን ነው፡፡ (ሐዋ 13፡1)

መብል ለኃጢዓት (ለጥንተ አብሶ) መሠረት በመሆኗ በመብል ምክንያት ኃጢዓት ወደ ዓለም መጥቷልና፣ በመብል ምክንያት ወደ ዓለም የገባው ኃጢዓትና ኃጢዓት ያስከተለው ሞት ከሥራቸው ተነቅለው ተደምስሰው፣ የጠፋው የሰው ሕይወት የታደሰው በጌታችን ጾም ነው:: ሰው በሥጋዊ መብልና መጠጥ ብቻ ሰውነቱ የሚያምር በጾም የሚጠወልግ የሚጎዳ እየመሰላቸው ጾምን የሚፈሩት የሚሸሹት ጥቅም እንደማይሰጥ ሰው ሰራሽ ሥርዓት አድርገው የሚመለከቱትም ብዙ ናቸው፡፡ አስተዋዮች ግን ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃለ እግዚአብሔር ጭምር እንጂ በእህል ውሃ ብቻ ሊኖር እንደማይችል ጠንቅቀው አውቀው እየጾሙ ይጠቀሙበታል አስፈላጊም በሆነ ቦታና ጊዜ ከማይፈለግ ጮማና ወይን ይልቅ ጥራጥሬ ተመግቦ መውዛት ማማር እንደሚኖር ከሶስቱ ወጣቶች (አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል) ታሪክ መማር ይቻላል፡፡ (ዳን 1፡8-16)

ምሳሌው ይደርስ ዘንድ (ለጊዜው)

ቀድሞ አባቶቹ ነቢያት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጾመዋል ከዚያ ቢያተርፍ አተረፈ ብለው ቢያጎድል አጎደለ ብለው አይሁድ ደገኛይቱን ሕግ ሕገ-ወንጌል ከመቀበል ይከላከሉ ነበር፡፡

‹‹እኔ ሕግና ነቢያትን ልፈጽም እንጂ ልሽር አልመጣሁም›› ብሏልና (ማቴ 5፡17) ሕግና ሥርዓትን እየፈጸመ ከሕግ በታች ሆኖ ተመላለሰ

ሀ/ ሙሴ በአርባ ዘመኑ ለዕብራዊው ወገኑ አግዞ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ ቀብሮታል (ዘጸ 2፡11) ሙሴ የወልድ እግዚአብሔር፣ ዕብራዊው ወገኑ የአዳም ፣ ግብጻዊው የዲያብሎስ፣ አሸዋው የመስቀል ምሳሌ ነው፡፡

ሙሴ ግብጻዊውን ገድሎ በአሸዋ እንደቀበረ ጌታችንም ጾሞ ጸልዮ ዲያብሎስንና ፈተናዎቹን ድል ነስቷል፡፡

ለ/ ሙሴ 40 ዘመን በምድያም ኖሮ እስራኤልን ከግብፅ የባርነት ቀንበር ነፃ አውጥቷል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስም እንጂ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ነፍሳትን ከሲኦል ነጻ ያወጣልና

ሐ/ ሕዝበ እስራኤል የገዳም ምሳሌ በሆነው በቃዴስ በረሃ 40 ዘመን ኖረው ምድረ ርሥት ኢየሩሳሌም ገብተዋል፣ (ዘጸ 14፡19 ፣ 32፡34) እናንተም 40 ቀንና 40 ሌሊት ብትጾሙ ርስት መንግስተ ሰማያትን ትወርሳላችሁ (ዘጸ 16፡4-17)

መ/ ሙሴ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸልዮ ለሕይወታችን መመሪያ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉ አስርቱ ቃላት ያለባቸው ጽላቶች ተቀብሏል፡፡ ሕገ – ኦሪትን ሠርቷል (ዘጸ 34፡28)

ኢየሱስ ክርስቶስም እንጂ 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾሞ ጸሊዮ ሕገ-ኦሪትን አጽንቶ ደገኛይቱን ሕግ ህገ-ወንጌልን (ስድስቱን ቃላተ ወንጌል) ሠርቷል፡፡

#join #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

#መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
👍1
ዘወረደ

ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡ ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤›› የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው፡፡ ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡

ጾሙን ሐዋርያት፣ ስያሜውንና የምስጋናውን ሥርዓት ቅዱስ ያሬድ አዘጋጅተዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ ነቢያትን በንባብ፤ ሐዋርያትን በስብከት፤ ሊቃውንትን በትርጓሜ፤ መላእክትን በዜማ ይመስላቸዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድ የመላእክትን የምስጋና ሥርዓት ወደ ምድር አምጥቷል፡፡ የነቢያትን ትንቢት፣ የሐዋርያትን ትምህርት በሚገባ ተርጒሞ፣ አብራርቶ፣ አመሥጥሮ አዘጋጅቶታል፡፡ ሐዋርያት ጾሙን ጾመው የጾም ሕግ ደንግገዋል፤ ቅዱስ ያሬድም ለጾሙ ስያሜ ሰጥቶ ምስጋና ከነሥርዓቱ አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡ቤተ ክርስቲያናችንም የመጀመሪያው የዐቢይ ጾም ሳምንትን (ዘወረደን) ስያሜ እንደ ቅዱስ ያሬድ ከሐዋርያት ተቀብላ ታስተምራለች፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ፮፻፲፬ ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ ሙሉ ታሪኩ በፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ አንቀጽ ፲፭ ላይ ይገኛል፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ቅድስት

‹ቅድስት› ማለት ‹የተለየች፣ የነጻች፣ የከበረች› ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት፣ ልዩ፤ የተቀደሰች፤ የከበረች፤ ልዩ፣ ንጹሕ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡ ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡ ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም፡- ትዕቢት፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡ ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡

#join or #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21

መንፈሳዊ ህይወት (ሰው)
Forwarded from Deleted Account
ምኩራብ
ይህ ስያሜ ከአቢይ ጾም ሳምንታት የሦስተኛው እሁድ ስያሜ ነው
ስለዚህ ምኩራብ ማለት ቤተ መቅደስ ወይም በእኛ አጠራር ቤተክርስቲያን ማለት ሲሆን በዚህ ቀን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ እግዚአብሔር የሚመለክበትን እና ስሙ የሚጠራበትን ቤት ሰዎች መሸጫና መለወጫ በማድረጋቸው በቁጣ መንፈስ ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል እናንተ ግን የንግድ ቤት አደረጋችሁት በማለት
። የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፥
ርግብ ሻጪዎችንም። ይህን ከዚህ ውሰዱ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉት አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 2 :15-- 16 ያለውን ሃይለ ቃል በመጠቀም ቤተ መቅደሱን ያፀዳበት ዕለት ምኩራብ በመባል ይታወቃል
በዚህም መሰረት ነው ደቀ መዛሙርቱ የቤትህ ቅንአት ይበላኛል ተብሎ ተፅፏል ብለው ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት የተነበየውን ጠቅሰው የተናገሩት
እንግዲህ ቤተ መቅደስ ስንል ስንት ዓይነት ቤተመቅደስ እንዳለ ለመረዳት እንደሚከተለው እንመለከታለን
አንደኛ ቤተመቅደስ ማለት ከሌሎቹ ቦታዎች የተለየና የተቀደሰውን ቦታ ነው ይህም ልዩ ሥፍራ እግዚአብሔር የሚያድርበት ስለመሆኑ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ በማለት ይገልፀዋል
። ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
መዝሙረ ዳዊት 122 : 1
በዚህ ሁኔታ ይህ ቤተ መቅደስ በእግዚአብሔር ጥያቄ የተሠራ ስለመሆኑ በኦሪት ዘፀአት እንዲህ እናነባለን
። በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ።
ኦሪት ዘጸአት 25 : 8
በዚህ መሠረት በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዲሠራ የተፈቀደውን ቤተ መቅደስ ቅዱስ ዳዊት በብዙ ምኞትና ሀሳብ ሊሠራው ያልቻለውን ልጁ ሰሎሞን ውብና ድንቅ አድርጎ የሠራው ለዚህ ነው
ቅዱሳን ሐዋርያትም በዚሁ ቤት እንደኖሩ ወንጌላዊ ሉቃስ በመጨረሻው ምዕራፍ
። ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ።
የሉቃስ ወንጌል 24 : 53
ሁለተኛ መቅደስ የተባለው የሁላችን አካል ወይም ሰውነታችን ነው ጌታችንም የተናገረው እና የገለፀው ይህንኑ ነው
። ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
የዮሐንስ ወንጌል 2 : 19
አይሁድም ይህን ሲናገር ስለ ልዩ ቦታው ስለ ቤተ መቅደሱ ብቻ የተናገረ መስሏቸው እንደ ተጠራጠሩና እንዳልገባቸው አውቆ በቁጥር 21 ላይ
። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር። በማለት አብራርቶላቸዋል
ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም በአንደኛ የቆሮንቶስ መልእክት
። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3 : 16---17
ሦስተኛ በእኛ አጠራር ቤተ ክርስቲያን ( ቤተመቅደስ) የተባለው ጉባኤያችንና ኅብረታችን ነው
ምን ጊዜም ቤተ መቅደስ ወይም ቤተክርስቲያን የሚለው መጠሪያ እግዚአብሔር የሚያድርበት ስለሆነ በፍቅርና በአንድነት በተሰበሰቡት ሰዎች መካከል ጌታችን እንደሚገኝ እንዲህ ይላል
። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።
የማቴዎስ ወንጌል 18 : 20
በተጨማሪም የክርስቲያኖች ኅብረት ቤተክርስቲያን እንደሚባል ይህ ጥቅስ በጉልህ ያስረዳል
። በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።
የሐዋርያት ሥራ 8 : 1
በዚህ መሠረት የተሰደደውና የተበተነው የክርስቲያኖች ህብረትና ጉባኤ መሆኑን ቃሉ በግልፅ ያስረዳናል
እነዚህ ከአንድ እስከ ሦስት የተጠቀሱት ነገሮች የእግዚአብሔር ማደሪያዎች መሆናቸውን ተገንዝበን
የኃጢአትና የርኩሰት የክፎችም የጥላቻ ማህበር እንዳናደርጋቸው እያሳሰብኩ የቤቱ በዓለቤትም ሲመጣ በመአትና በቁጣ ጅራፍ ከቤቱ እንዳያወጣን ተጠንቅቀን እንድንኖር እግዚአብሔር ይርዳን ። አሜን።
Forwarded from ሰላም ለኪ ማርያም (EMANDA💗💖)
​​በጾም ወራት "ዓሳ" መብላት ይቻላልን???

ክፍል አንድ

ብዙ ጊዜ ይህ ከላይ ያነሳነው ርዕሰ ጉዳይ ሰዎችን ሲያከራክር እንሰማለን በተለይ በዚህ በያዝነው በዐብይ ፆም ደግሞ ሁኔታው ከፍ ብሎ ምዕመኑ ውዥንብር ውስጥ ሲገባ ይሰተዋላል ዓሳ ፆም አለው የለውም በሚል ንትርክም ጊዜውን ያጠፋል።

ዓሳ ፆም የለውም ብለው የሚከራከሩ ሰወች እንደ መነሻ ምክንያት አድርገው የሚያነሷቸውና የሚከራከሩባቸው ከእውቀት ማነስ የመጡ ሁለት ነጥቦች አሉ።
እነሱም ፦
1ኛ፨ በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት ) ስለ ፆምና ሥርዓቱ በሚዘረዝረው አንቀፅ 15 ላይ ያለውን "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ አሳ" የሚለውና
2ኛ፨ በአብይ ፆም ጊዜ ጌታ ለሐዋርያቱ አሳ አበርክቶ መግቧቸዋል የሚለው ናቸው።

እነዚህን ሁለት ነጥቦች በዝርዝር ስንመለከት
1ኛ. በፍትህ መንፈሳዊ (በፍትሃ ነገስት )ላይ እውነት ነው " ኢትብልዑ ... ስጋ ዘእንበለ አሳ " የሚል ትዕዛዝ አለ። እዚህ ትዕዛዝ ውስጥ ለክርክሩ መነሻ የሆነው <ዘእንበለ> የሚለው የግእዝ ቃል ነው! ይህ ቃል በግእዙ ሁለት ትርጉም አለው እነሱም፦
ዘእንበለ = በስተቀር
ዘእንበለ = ሳይቀር (ጭምር) የሚል ነው።

በነዚህ ትርጉሞች መሰረት የትዕዛዙ ትክክለኛ የአማርኛ ፍቺ "ኢትብልዑ ስጋ ዘእንበለ ዓሳ " ለሚለው "ስጋን ሁሉ አትብሉ ዓሳንም ሳይቀር (ዓሳንም ጭምር) ማለት ሆኖ ሳለ አንዳንድ
ሰዎች ይህንኑ ትዕዛዝ "ስጋን አትብሉ ከዓሳ በቀር" ብለው አጣመው በሁለተኛው ፍቺ በመተርጎም ዓሳን በፆም ወቅት ሲበሉና መብላትም እንደሚቻል
ሲናገሩ እንሰማለን።

ይህ ነገር የቤተ ክርስቲያን አስተምሮ እንዳልሆነ ቅዱስ ሲኖዶስም እንደከለከለ ምዕመኑ ተረድቶ ነገርየውን ከመፈፀም መቆጠብ ያልተፃፈውን የሚያነቡትንም ተው ማለት ይገባዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘም ደግሞ ዓሳ ደም ስለሌለው በፆም መመገብ ይቻላል የሚሉ አሉ። ይህ ከየዋህነት የሚመጣ አስተሳሰብ ነው ምክንያቱም ሲጀመር ዓሳ ደም አለው ሲቀጥል እነ እንቁላል እነ ወተት እነ አይብና ቅቤ ደም ሳይኖራቸው ነው የፍስክ ሆነው በፆም የማይበሉት።

ይህ ነገር የሚደረገው መፆም ማለት ስጋን ጎድቶ ለነፍስ ማስገዛት እስከሆነ ድረስ አበልፃጊ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ስላለብን ነው ዓሳ ደግሞ ከበግና ከበሬ ስጋ የተሻለ ጥቅም
እንዳለው ይታወቃልና ከበግና ከበሬ ተከልክሎ አሳን መብላት እራስን ማታለል ነው የሚሆነው ስለዚህ አንድ ክርስቲያን በጾም ሰአት ዓሳን መብላት አይችልም ማለት ነው።

ሼር
ክፍል 2 ይቀጥላል


@Ortodox_Ringtones
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
መጻጒዕ

አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል፡፡ ስያሜው በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩ ላይ ከሚገኘው ኃይለ ቃል የተወሰደ ነው፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ጌታችን በቤተ ሳይዳ ሕሙማንን እንደ ፈወሰ ተነግሮአል፡፡ ብዙ ሕሙማን ፈውስ ሽተው አንዲት የመጠመቂያ ሥፍራን ከበው ይኖሩ ነበር፡፡ በዚያች ሥፍራ ቀድሞ የወረደ እና የተጠመቀ አንድ በሽተኛ ብቻ ይፈወስ ነበር፡፡ ጌታችን በዚህ ሥፍራ ተገኝቶ በሽተኞችን ጐብኝቷል፡፡ በዚያም ልዩ ልዩ ደዌ ያለባቸው አምስት ዓይነት ሕሙማን እንደ ነበሩ ተገልጧል፤ እነዚህም፡- ሰውነታቸው የደረቀ፣ የሰለለና ያበጠ፤ እንደዚሁም ዕውራን እና ሐንካሳን ነበሩ፡፡ ከዚህ አምስት የተለያየ ዓይነት በሽታ ከተያዙ ሰዎች መካከል ደዌው የጸናበት፣ ለሠላሳ ስምንት ዓመታት በደዌ ዳኛ፣ ባልጋ ቍራኛ ተይዞ የኖረው፤ ከደዌው ጽናት የተነሣ ‹መጻጒዕ› ተብሎ የተጠራው በሽተኛ አንዱ ነበር፡፡ መጻጒዕ ስም አይደለም፡፡ ደዌ የጸናበት በሽተኛ ሕመምተኛ ማለት ነው እንጂ፡፡ ሰውየው ከበሽታው ጽናት የተነሣ ስሙ ጠፍቶ በበሽታው ሲጠራ የነበረ ነው፡፡ አምላካችን ይህን ሰው ‹‹አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› ብሎ ሠላሳ ስምንት ዘመን የተኛበትን አልጋ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እንዲገባ ማድረጉ የሚነገርበት ወቅት በመኾኑ ሳምንቱ ‹መጻጒዕ› ተብሎ በተፈወሰው በሽተኛ ስም ተሰይሟል፡፡ (ሙሉ ታሪኩን በዮሐንስ ወንጌል ፭፥፩-፲፯ ይመልከቱ)፡፡ ዛሬም ቢኾን በሰዎች ላይ ልዩ ልዩ ደዌያት አሉ፤ የሥጋውን ደዌ ሐኪሞች ያውቁታል፡፡ ከዚህ የከፉ የነፍስ ደዌያት እጅግ ብዙዎች ናቸው፡፡ በኃጢአት ብዛት ልባቸው የደረቀና ያበጠ፤ ሰውነታቸው የሰለለ፤ ዓይነ ሕሊናቸው የታወረ፤ እግረ ልቡናቸው የተሰበረ ብዙዎች ሕሙማን አሁንም አሉ፡፡ ፈውስን ይሻሉ፤ ድኅነትን ይፈልጋሉ፡፡ እንደ መጻጕዕ ቦታቸውን ሳይለቁ እግዚአብሔርን በተስፋ ቢጠብቁት አንድ ቀን ይፈወሳሉ፡፡


#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
ገብር ኄር

ስድስተኛው ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡ ስያሜው ከማቴዎስ ወንጌል ፳፭፥፲፬ የተወሰደ ሲኾን፣ ታሪኩም እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ በታማኝነት ማገልገል የሚያስገኘውን ዋጋ ያስረዳል፡፡ አንድ ሰው አገልጋዮቹን ጠርቶ ወጥተው፣ ወርደው፣ ነግደው እንዲያተርፉ ለአንዱ አምስት፤ ለአንዱ ሁለት፤ ለአንዱ ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸው፡፡ አምስት መክሊት የተቀበለው በተሰጠው መክሊት ነግዶ፣ ሌላ አምስት መክሊት አትርፎ፣ ዐሥር አድርጎ፣ ‹‹ጌታዬ አምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ ወጥቼ ወርጄ አምስት አትርፌአለሁ›› ብሎ ለጌታው አቀረበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ጎበዝ እና ታማኝ ባሪያ! በጥቂቱ ታምነሃልና በብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ ሁለት መክሊት የተቀበለውም ወጥቶ፣ ወርዶ፣ አትርፎ አራት አድርጎ አቀረበ፡፡ እርሱንም ጌታው ‹‹አንተ ታማኝ ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃልና ወደ ጌታህ ደስታ ግባ!›› አለው፡፡ አንድ የተቀበለው ሰው ግን መክሊቱን ወስዶ ቀበራት፡፡ ጌታው በተቈጣጠረው ጊዜም የቀበራትን መክሊት አምጥቶ ‹‹አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ እንደ ኾንኽ ዐውቃለሁ፡፡ ስለዚህ ፈራሁና የሰጠኸኝን መክሊት ቀበርኳት፤ እነሆ መክሊትህ!›› ብሎ ምንም ሳያተርፍ መክሊቱን ለጌታው መልሶ አስረከበ፡፡ ጌታውም ‹‹አንተ ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ! ወርቄን በጊዜው አታስረክበኝም ነበር? ነግዶ ለሚያተርፍ እሰጠው ነበር፡፡ ይህን ክፉና ሐኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አስራችሁ ጨለማና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ሥፍራ ውሰዱት! መክሊቱን ቀሙና ለባለ ዐሥሩ ጨምሩለት!›› ብሎ አዘዘ፡፡

በዚህ ታሪክ እንደምናየው በተሰጠው መክሊት ያተረፈ ሰው (ክርስቲያን) ዋጋ አለው፡፡ በፈጣሪው ዘንድ መልካም፣ በጎ፣ ታማኝ ባሪያ ተብሎ ይሸለማል፡፡ ባያተርፍ ደግሞ ሐኬተኛ ባሪያ (አገልጋይ) ይባላል፤ ቅጣቱንም ይቀበላል፡፡ እንግዲህ እኛም ታማኝ አገልጋይ መኾን ይጠበቅብናል፡፡ ሳምንቱ ይህ መልእክት የሚተላለፍበት ወቅት ነው፡፡ በዚህ ዘመን በመክሊታቸው የሚያተርፉ እንዳሉ ዅሉ፣ መክሊታቸውን (ጸጋቸውን) ዝገት እስከሚያጠፋው ድረስ የሚቀብሩ ብዙዎች ናቸው፡፡ መክሊትን (ጸጋን) መቅበር ዋጋ የማያሰጥ መኾኑን ተገንዝበን በቻልነው መጠን ለማትረፍ መትጋት እና ታማኝ አገልጋይ መኾን እንደሚገባን ከገብር ኄር ታሪክ እንማራለን፡፡


#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
ልጆቼ! የእግዚአብሔር ትእዛዝ እንዴት ቀላል እንደሆነ የምታስተውሉ ሁኑ፡፡ ምክንያቱም ታስሬ አስፈትታችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ታምሜ አድናችሁኛልና ሳይሆን ጠይቃችሁኛልና፤ ተርቤ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መዓድ ሳይሆን አንዲት ዳቦ አብልታችሁኛልና፤ ተጠምቼ በየዓይነቱና ውድ የሆነ መጠጥ ሳይሆን አንዲት ቀዝቃዛ ኩባያ ውኃ አጠጥታችሁኛልና ነው የሚለን፡፡

በጣም የሚያቀለው ደግሞ እነዚህን ቀላል ትእዛዛት በራሳችን ጥረት የምናደርጋቸው አይደሉም፡፡ ምክንያቱም በቃሉ "ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ስለሚለን ጸጋ መንፈስ ቅዱስን አጋዥ አድርገን ነው፡፡ እንግዲያውስ ድሀ ስለሆንኩ እነዚህን ማድረግ አልችልም ብለን ራሳችን ሰነፎች የምናደርግ አንሁን፡፡ ሺህ ጊዜ ደሀ ብንሆን ሁለት ሳንቲም ከሰጠችው መበለት በላይ ድሀ ልንሆን አንችልምና፡፡ ስለዚህ ስንፍናን ከእኛ እናርቅ፡፡

ልጆቼ! እነዚህን በእርሱ እርዳታ ስላደርግንስ ምን እንደምንባል ትገነዘባላችሁን? “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን!” ካላደረግንስ? “እናንተ ርጉማን ከእኔ ዘንድ ሂዱ!” እንግዲያውስ ለእኛ ሳይሆን ለሰይጣንና ለመላእክቱ የተዘጋጀውን እሳት ከሚያገኘን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለእኛ የተዘጋጀውን መንግሥት እንወርስ ዘንድ ዛሬ አብዝተን ዘይት የምንገዛ እንሁን፡፡ እንደነዚያ ሰነፍ ደናግላን እዚያ መግዛት በማይቻልበት ቦታ ሄደን ከምንጠይቅ ዛሬ ሳይመሽብን የሚበቃንን ያህል ዘይት እንግዛ፡፡ ዘይቱ የሚገዛውስ የት ነው? የታመሙት ጋር፤ እስረኞች ጋር፤ ቁርና ሀሩር በሚፈራረቅባቸው ወንድሞቻችናነ እኅቶቻችን ጋር፡፡

ልጆቼ! እንደ ነዌ እዚህ ምድር ባለጸጎች ሆነን ያኔ ከምንለምን ዛሬ አልዓዛርን ልናስበው ይገባል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
(ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53)
----------
4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

@linkortodoxe21
(የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 15)
----------
17፤ ቀይ ልብስም አለበሱት፥ የእሾህ አክሊልም ጎንጉነው ደፉበት፤

18፤ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤

19፤ ራሱንም በመቃ መቱት ተፉበትም፥ ተንበርክከውም ሰገዱለት።

20፤ ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።

21፤ አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።

22፤ ትርጓሜውም የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደተባለ ስፍራ ወሰዱት።

@linkortodoxe21
እንካን አደረሳችሁ 😍😍😍
@linkortodoxe21
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤አሰሮ ለሰይጣን፤አግዐዞ ለአዳም፤ሠላም እምዕይዜሰ፤ኮነ ፍስሐ ወሠላም።

'ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሣ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍጽም ሰላምና ደስታ ሆነ'

" እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም"
(የማቴዎስ ወንጌል 28:6)

😊እንካን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ😊
2025/07/14 14:37:32
Back to Top
HTML Embed Code: