Telegram Web
ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ። እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን #በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን #በኑሮ_ዕወቃት። ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ። እሊህም፦ ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
"ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።"
#ቅዱስ_ሚናስ

@linkortodoxe21
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
🔸መንፈስ ቅዱስ ስንቀበል🔸


(የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1)
----------
41፤ ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥

42፤ በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።

43፤ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?

44፤ እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።

45፤ ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት።

እንደ ኤልሳቤጥ ድንግልን አመስግነን ሰግደን በደስታ ሆነን ተጽናንተን እንጂ የምን ለቅሶ ነው ጉድ እኮ ነው
መንፈስ ቅዱስ ደቀ መዛሙርቱን ሲሞላባቸው ተደሰቱ እንጂ ጮሁ አለቀሱ ተበሳጩ የሚል የለም

" በደቀ መዛሙርትም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው።
"
(የሐዋርያት ሥራ 13:52)

እና የፕሮቴስታንት እምነት ከየት አምጥቶት ነው

#join
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
☺️መልካም ወጣት ዘተዋሕዶ 😊

" ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2:3-4)

@Ortodoxe19
Forwarded from ✟ የተዋህዶ ልጆች ✟ (✟Mentesenhot✟)
"ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡

ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡"

#join
🔸 @Ortodoxe19
🔸 @Ortodoxe19
🔸 @Ortodoxe19
ኃያሉ ሚካኤል
ዝማሬ ዘኦርቶዶክስ
✞ ኃይሉ ሚካኤል

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ለሶርያው ሰው ለማኑሄ እንደነገረው
በመሰዊያው ነበልባሉ ውስጥ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከዳር ወገን የሆነ በእግዚአብሔር ያመነ
ማኑሄ የሚባል ሰው የጌታ መላዕክ ታየው
ሚስቱ መካን ነበረች ልጅንም ያልወለደች
ሚካኤል ተገልጦላት በዘር ፍሬ ባረካት

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦፍራ አድባር ለጌድዬን የተገለጠው
እስራኤልን ከምድር ረሀብ ታደገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

አንተ ጽኑ ሃያል ሰው እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው
ክንድህን ላበረታ ተልኪያለው ከጌታ
አይዞህ ጌድዮን ያለው ቁርባኑን ያሸተተው
ከኛ ጋር ነው ሚካኤል ሰልፋችንን ይመራል

አዝ


የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
በኦርና አውድማ ሰይፍን ይዞ ቆሞ የታየው
ዳዊት በመንቀጥቀጥ ፊቱን ፈለገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

በ3 ቀን ቸነፈር እንዳትጠፋ ምድር
70ሺ ሰዎች ወድቀው መላዕኩ በቃህ አለው
ለምህረት ይመጣሉ ለመአት ይላካሉ
ሰይፉን ካአፎቱ ከቷል ሚካኤል ለህዝቡ ቆሟል

አዝ

የእግዚአብሔር መላዕክ ስሙ ድንቅ ነው
ስምኦን ጴጥሮስን ከወይኒ ቤት ገብቶ ያወጣው
የእጆቹን ሰንሰለት ፈቶ አረገ
ኃያሉ ሚካኤል ድንቅን አደረገ/2/

ከጠባቂዎች መሃል ኬፋን ከእንቅልፉ አንቅቷል
የተዘጋውን ደጃፍ አልተሳነውም ማለፍ
ሚካኤል እየመራው ጰጥሮስ እግሩ የቀናው
አውቆታል ልቡ በርቶ ዘለለ ስሙን ጠርቶ

ዘማሪ
ገብረ-ዮሀንስ ገብረ-ጻድቅ

════◉❖◉═══◉❖◉═════
●❖
https://www.tgoop.com/linkortodoxe21
https://www.tgoop.com/linkortodoxe21
👍1
✞ ኦ ቅዱስ ሚካኤል

ሚካኤል በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ቆሟል
ለተጨነቀች ነፍስ ምህረት ይለምናል
ጨለማው እንዲሸሽ እንዲሆን ብርሃን
ኦ ቅዱስ ሚካኤል ሰዓለነ እንበል (2)

እረቂቁመላዕክ መብረቅ ተጎናጽፏል
ለሰማይ ሰራዊት አለቃቸው ሆኗል
የምክሩ አበጋዝ ስሙ የተፈራ
እሱ ነው ሚካኤል ለሕዝቡ የሚራራ (2)

አዝ__________________

እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልፅበት
ፀሎት የሚያሳርግ የሚያሰጥ ምህረት
ስለ ትህትናው ከአምላክ የተሾመው
ቅሩበ እግዚአብሔር ቅዱስ ሚካኤል ነው (2)

አዝ__________________

እርህሩነው እና የነፍሳችን ወዳጅ
ለፍጥረቱ ሁሉ የታመነ አማላጅ
ከቅጥረ ፀሎቱ ነፍሳችን ትጠጋ
ተግቶ እንዲጠብቀን ሲመሽም ሲነጋ (2)

አዝ__________________

የነፀብራቅ ዝናር ሚካኤል ታጠቀ
በቅድመ እግዚአብሔር ሕዝቡን አስታረቀ
በእሳታዊው አክናፍ ከክፉ ጋረደ
ልጆቹን ሊባርክ ሚካኤል ወረደ (2)


ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች #share እናድርግ !
#join_share
@linkortodoxe21
-
እንኳን አደረሳችሁ!!!

🌻🌻እኔስ ምን ልተውልህ?🌻🌻

🌻🌻 ጴጥሮስ መረቡን ተወልህ: ማቴዎስም ቀረጡን በርተሎሜዎስም ግብርናውን ሌላውም ሽመናውን ተዉልህ እኔስ ምን ልተውልህ? ምን ልጣልልህ?

🌻🌻 ኒቆዲሞስ ትዕቢቱን ሳምራዊቷም እንስራዋን ዘኬዎስም ዛፉን ማርያም ዘናይን ዝሙቷን ተዉልህ እኔ ባሪያህ ምን እተውልህ ይሆን? ከኔ የሚጣልና የሚወድቅ ሀጢአት እጅግ ብዙ ነው ቤቴ የከረፋ በደለኛ ልጅህ ምን እጥልልህ ይሆን?

🌻🌻ሰኞ ያጣኸኝ በለስ ፤ አርብ የቀረሁ ሐዋርያ፤ የሸጥኩህ ይሁዳ፤ መቅደስህ ሲቃጠል ዝም ያልኩ ጲላጦስ ፤ አላቅህም ያልኩ ጴጥሮስ፤ ቁስሌ ሳይደርቅ የረገጥኩህ መጻጉዕ እኔ ነኝ!

🌻🌻ጌታዬ ሆይ ቅጠል ብቻ የሆንኩ ፍሬ አልባ ሆንኩብህ! በሞትህ ቀን ያጣኸኝ ሐዋርያ እኔው ነኝ ፤ ቤ/ክ መከራ ሲደርስባት ዘብ ያልቆምኩላት እኔ ነኝ! ሰኞ ፍሬ ያጣህብኝ ምግባር አልባው ደንዳናው ልጅህ እኔ ነኝ

🌻🌻 ቤቴ እንደሆን ከጣሪያው የማያስገባህ ላንተ የማይገባ አደፍ ቤት ለዘመናት የተዘጋ ቤት ድር እንደሚበዛው ልቤም አንተን አጥቶ ሀጢአት ደርቶበታል ...እናም ሁሉን ክፋት ጥዬ ልከተልህ በዕውቀት ሳይሆን በሕይወት ልከተልህ ስለ አንተ ሳይሆን አንተን ልወቅህ ልቅረብህና ሰው አርገኝ ......ብቻ ካንተ ያለያዩኝን ስንፍናን፤ ተንኮልን፤ክፋትን፤ግዜ ማባከንን፤ወገንተኝነትን፤አለመከባበርን ፤አለመተሳሰብን፤ ትርፍ የሌለውን ከንቱ ተግባርን ልጣልና ልከተልህ።

🌻🌻 ስንት ጊዜ ልትፈልገኝ መጣህ? መቼ በቀንህ ተገኘሁ? ስትቀርበኝ የራቅኩ ስትፈልገኝ የጠፋሁ ሽፍታ እኔ ነኝ! በጾሙ ወራት በሕማሙ ሳምንት ማን ነኝ? በእኔ ውስጥ አንተን መስክሬ ይሆን? የታጣሁ ፍሬ ልጅህ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ

🌻🌻 ከቤ/ክንህ መከራ ሳልሳተፍ ከሀገሬ ቁስል ሳልጋራ ለነፍሴ ሳልተጋ ዓመታት ተቆጠሩ ዘንድሮም ከቁጥር ደረስኩ እስከ አሁን የታገስከኝ ይቺን ዓመት ተወኝ፡፡


© ጥላዬ ግብሩ
የ2015 ዋዜማ
@ ሐረር

@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
2025/07/13 15:50:49
Back to Top
HTML Embed Code: