Telegram Web
መንፈሳዊ ህይወት pinned «https://www.tgoop.com/Ortodoxe21 ሁላችንም እንሳተፍ»
መንፈሳዊ ህይወት
በደብረ ታቦር ተራራው የምን ምሳሌ ነው
📚 ክፍል 1
ደብረ ታቦር ተራራ የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ እንዴት ትሆናለች ቢባል ተራራ ሲወጡት ያደክማል ያልባል ጉልበት ይዝላል ግን ከወጡ በኃላ ድካምን አስረስቶ ንፅህ አየር ይሰጣል የሚከናወነውን ሚስጥር ገሀድ አርግቶ ያሳያል መንግስተ ሰማያትም እንዲሁ ነው ሰው ለሆንን እኛ በዚህች ምድር ሳለን መጾም መጸለይ መቅረብ ማስቀደስ ማህሌት መቆም ኪዳን ማድረስ ወንጌል መማር መዝሙር ማጥናት ኮርስ መከታተል ያቅተናል እንዝላለን እንደክማለን በመጨረሻ ግን የፀናንበትን ዋጋ እናገኝለን እና ደብረ ታቦር በመንግስተ ሰማያት የተመሰለችበት ምሳሌው ይህ ነው ተራራ መውጣት እንደሚያደክም መንግስተ ሰማያትም መግባት በብዙ መከራ እና ፈተና ችግር መሆኑን ሲነግረን ነው።

ይቀጥላል.......
ለወዳጆ ሼር ያድርጉ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት
በደብረ ታቦር ተራራው የምን ምሳሌ ነው
📚ክፍል 2
ደብረ ታቦር እንዴት በቤተክርስቲያን ትመሰላለች ቢሉ ቤተክርስቲያን ሁለት ካህናት ሶስት ዲያቆን በመሆን ወደ እግዚአብሔር ቅዳሴ ምስጋና ፀሎት ይደርሳል ቅዳሴ የሚለው ይጠቀልልናል እና ደብረ ታቦር ላይ ሙሴ እና ኤልያስ በካህናት ሶስቱ ሀዋርያት በዲያቆናት ይመሰላሉ ታቦር በቤተክርስቲያን ጌታችን የቤተክርስቲያን ራስ በመሆን በደብረ ታቦር ላይ የጌታችን ልብሱ ወደ አስደናቂ ነጸብራቅ እንደተለወጠ በቅዳሴ ሰአት ልክ ፍሬ ቅዳሴ ሲገባ ስንዴው ወደ ጌታ ቅዱስ ስጋ ወይኑ ወደ ጌታ ቅዱስ ደም ይለወጣል ይህ የዛ ምሳሌ ነው ሙሴና ኤልያስ ከጌታ ጋር ሲነጋገሩ እንደነበር አይንተ እግዚአብሔር አባቶች ካህናት እግዚአብሔር አይን አርግታቸው እንደሚያይባችው እግዚአብሔር አፍ አርግታቸው እንደሚናገርባቸው ምሳሌ ነው.....በአጠቃላይ ታቦር ተራራ የቤተክርስትያን ምሳሌ ነች


ይቀጥላል...
ለወዳጆ ሼር ያድርጉ
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxd21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት
📚በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ለምን ተገኙ??? ሁላችሁም በ comment ላይ ተሳተፉ 👇👇👇 መልሱን አየዋለሁ
📜በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ለምን ተገኙ?
ስለ ብዙ ምክንያት ነው እኛ ግን 4 እናያለን የመጀመሪያ ጌታችን
ማቴዎስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።
¹⁴ እነርሱም፦ አንዳንዱ መጥምቁ ዮሐንስ፥ ሌሎችም ኤልያስ፥ ሌሎችም ኤርምያስ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ አሉት።

1.ሐዋርያትን በጠየቀ ጊዜ ሰዎች አንዳንዶቹ ከነብያት አንድ እንደሆነ ሌሎቹም ኤልያስ ነው.. ይሉ ስለነበረ እሱ ሙሴ እንዳልሆነ ኤልያስም እንዳይደለ እንደውም እርሱ የነብያት አምላክ ፈጣሪ ለዓለም ነፍሱን ቤዛ ሊሰጥ እንደመጣ ሲያጠይቅ በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ተገኝተዋል


ይቀጥላል.....

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
መንፈሳዊ ህይወት
📚በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ለምን ተገኙ??? ሁላችሁም በ comment ላይ ተሳተፉ 👇👇👇 መልሱን አየዋለሁ
2. አንድም ሙሴን ከመቃብር ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን መጥራቱ እኔ የሕያዋን እና የሙታን ፈጣሪ እኔ ነኝ ሲል በደብረ ታቦር ሙሴና ኤልያስ ተገኝተዋል
መንፈሳዊ ህይወት
📚በደብረ ታቦር ላይ ሙሴና ኤልያስ ለምን ተገኙ??? ሁላችሁም በ comment ላይ ተሳተፉ 👇👇👇 መልሱን አየዋለሁ
3.አንድም ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር መገኝታቸው ሙሴ በምድር ላይ እጅግ ትሁት ሰው ነበረ
“ሙሴም በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ እጅግ ትሑት ሰው ነበረ።”
— ዘኍልቁ 12፥3
ኤልያስ ደግሞ እጅግ ቀናተኛ ነበረ ለአምልኮተ እግዚአብሔር የሚቀና
“በገለዓድ ቴስቢ የነበረው ቴስብያዊው ኤልያስ አክዓብን፦ በፊቱ የቆምሁት የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ጠልና ዝናብ አይሆንም አለው።”
— 1ኛ ነገሥት 17፥1
ሰማይን የሚለጉም እሳትን የሚያወርድ ነውና ኤልያስን በደብረ ታቦር ጠራው ይህ ሚስጥሩ ምንድነው ቢሉ
የእኛ አገልግሎት እንደ ሙሴ በትህትና እና እንደ ኤልያስ በመንፈሳዊ ቅናት ከሆነ እግዚአብሔር አገልግሎታችንን እንደሚቀበል ከፍ ወዳለው ክብር እንደሚያሸጋግረን ሲያስተምረን ሲነግረን ነው።

4.አንድም ሙሴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሕግ ተሰቶታል ኤልያስ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ ጠብቃል በዛም ኃይለኝ ማቅ የለበሰ አመድ የነሰነሰ ሰማይን የመዝጋት የመክፈት እሳት የማውረድ በእሳት ሰረገላ የማረግ ስልጣን አጊንታል እና ጌታችን በደብረ ታቦር ሙሴና ኤልያስ መጥራቱ ሕግን እንደ ሙሴ ተቀብለን እንደ ኤልያስ በቅንነት መተግበር እንዳለብን ሲነግረን ነው።

5.አንድም በደብረ ታቦር ላይ ከብሉይ ሙሴና ኤልያስ ከሐዲስ 3ቱ ሀዋርያት መገኝታቸው ጌታችን የብሉይ እና የሐዲስ ጌታ አምላክ እኔ ነኝ ሲለን ነው
6.አንድም ከብሉይ ነብያትን ከሐዲስ ሐዋርያትን ያስገኝበት ነብያት ስለ እኔ የተናገሩልኝ ሐዋርያት ስለእኔ የሚመሰክሩልኝ አልፋ እና ኦሜጋ እኔ ነኝ ሲል ነው
7.አንድም ሙሴና ኤልያስ በደብረ ታቦር መገኝታቸው ሁለቱም ሊያዩት ይመኙ ስለነበረ በኃለኛው ዘመን ታየኝለህ ብሎ ለሙሴ ቃል ስለገባለት ኤልያስም ብዙ ጊዜ ሊያየው ይመኝ ስለነበረ በብሉይ ለምን አላዩትም ቢሉ እግዚአብሔር በብርሀነ መለኮቱ አይቶ መቆም የሚችል ፍጥረት ስለሌ በኃለኝው ዘመን ሰው ሆኖ ታያቸው።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

#join #share
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
😁አራት ብዮ ሳላውቀው 7 ገባሁ መልካም ንባብ
ከሁሉም ይልቅ ኃጥእ ስሆን ከሁሉ ይልቅ ጻድቅ እንደ ሆንኹ አስቤ በንጽሕናሽ እመካለሁ፡፡
ጠላት ቢነሳበብኝ አንቺ ስላለሽኝ ምን እሆናለሁ
"እናቴ ኪዳነምህረት"❤️

እንኳን አደረሳችሁ ኦርቶዶክሳውያን🙏🏿❤️
#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
🌹"ነገ ነሐሴ 16 እኮ ነው እንኳን ለእናታችን ለእመቤታች ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገቷ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።🙏🌷

በዓሉ የሰላም የፍቅር የጤና ያሰባችሁት የልባችሁ መሻት የሚፈጸምበት በልዕልና ከፍ የምትሉበት እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቴ ነው 😊🙏

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
እናት አለኝ የምታስብ እንባ
አያታለሁ ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት ኪዳነ ምህረት
አንባ መጠጊያ ናት
✥ ------------- ✥
ሔዋን ሰታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቁቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደኔ መተሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል
✥ ------------- ✥
ለዘለዓለም ንጽህት በመሆኗ
ከእኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሃዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ
✥ ------------- ✥
ከጥፋቱ ውሃ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ
በሕይወት አለሁ ጥልቁን ተሻግሬ
✥ ------------- ✥
በእናትነት ሕይወቴን ጎብኝታው
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታው
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬን በልጅሽ ጣፈጠ
✥ ------------- ✥
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር

#join
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
ኪዳነምሕረት ልዩ ነሽ ለእኔ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኪዳነ_ምህረት_ልዩ_ነሽ_ለኔ

ኪዳነ ምህረት ልዩ ነሽ ለኔ
ሳዝን ስጨነቅ አትራቂኝ ከጎኔ
የችግሬ ደራሽ እመ እግዚአብሔር
ቃል ኪዳንሽ ይርዳኝ ካንቺ ጋር ልኑር(፪)
#አዝ
የአዳም ተስፋው ነሽ የሴት ቸርነቱ
ኪዳነምህረት ነሽ የኖህ ምልክቱ
አዳም ደጅ የጠናሽ ሲገባ ንስሀ
ኖህም ድኖብሻል ከጥፋቱ ውሃ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንቺ ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናየን ሁሉ
#አዝ
የሰሎሞን አክሊል የዳዊት ዝማሬ
ድንግል መሆንሽን ትመስክር ከንፈሬ
ለተጠማው ውሻ የሚራራው ልብሽ
ለኔም እራርቶልኝ አስታርቂኝ ከልጅሽ
#አዝ
የአብርሃም ድንኳን ነሽ የሙሴ ፅላቱ
ማርያም አንች ነሽ የፈጣሪ እናቱ
የእስራኤል መሰላል የሴም እጣ ክፍሉ
እመብርሃን ስሚኝ ልመናዬን ሁሉ
💚 @linkortodoxe21 💚
💛 @linkortodoxe21 💛
❤️ @linkortodoxe21 ❤️
ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና።

ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና።

አቤቱ፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን፥ በአንተ እንደ ታመንን። (መዝሙር 33፥20-22)

@linkortodoxe21
🌹❖ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው🌹

✥##ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን✥አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም” ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

✥ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ሰጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ይህ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
የነቢያትን ትንቢት የፈጸመ፤የክርስቶስን ልደት ለድንግል ያበሰረ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሠለስቱ ደቂቅን ከእቶን እሳት ያዳነቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ወደ ዮሴፍና ወደ ኒቆዲሞስ የተላከ

✥ቅዱስ ገብርኤል ነው✥
ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ከእቶን እሳት ያዳናቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ

✥ይህ ገብርኤል ነው✥
የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ

✥ገብርኤል ነው✥
የአሸናፊና የኃይል መልአክ

✥ገብርኤል ነው✥
ነበልባላዊ ዖፈ ሰማይ

ገብርኤል ነው
አማላጅ ነው ፈጥኖ ደራሽ

"የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን"
❖አሜን❖🙏🙏🙏

👉 @linkortodoxe21
አዲሱ አመት ባርክልን

አሮጊ አመት አልፎ አዲሱ ዘመን መጣ
ምድረ በዳው ሁሉ አበባን እንዲያወጣ
ጭጋጉ ዝናብ ዘመኑን ጨርሶ
ርዕሰ አውዳመት መጣ ተመልሶ/2/


በአድይ አበባ ምድሩ ተንቆጥቁጦ
ጨለማው በብርሃን ደምቆ ተለውጦ በወርሃ መስከረም ቅዱስ ዮሐንስ
እንደ ምን ደስ ይላል ጌታ ሲወደስ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርክልን/4/ አዲሱ አመት ባርክልን
አውዳመቱን ባርክልን /2/


/አዝ====


የጠራውን ሰማይ እንድናይፈቀደ አዲስ
ቀን ሊሰጠን እግዚአብሔር ወለደ
በዳዩን ሰውነት ጥለን እንድንመጣ
ለአዲስ ማንነት አዲስ አመት መጣ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል/4/ .............

/አዝ =====


በችቦ ብርሃን ስንሰንቅ ተስፋ ችግርና
ስደት ከኢትዮጵያ እንዲጠፋ እንዲሰማን
አምላክ ምህረት እንዲመጣ ከወቀልና
ግፍ ከቁጣም እንድንወጣ

አበባ አየሽ ሆይ /4/ ................

/አዝ =====

በዙፋኑ ያለ በዘመን የሚኖር አመትን ሊሰጠን ስለ ድንግል ብሎ ልክ እንደ ዘመኑ ልባችን ይለወጥ በቀኙ እንድንቆም ለፍርድ ሲቀመጥ

አበባ አየሽ ሆይ እንበል /4/
ኢዮሃ አበባ እንበል/4/መስከረም ጠባ
ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን /2/

/አዝ =====

በተሰጠሽ ኪዳን ባንቺ አማላጅነት
ለአስራት ሃገርሽ ይምጣላት ምህረት
የፍቅርን ሸማ ኢትዮጵያ ትልበስ
እርጋታን ያድላት የእግዚአብሔርመንፈስ

ባርኪልን /4/ አዲሱን አመት ባርኪልን
ድንግል ማርያም ባርኪልን


አርቲስት ዘማሪ ይገረም ደጀኔ /አስቴር /
ዘማሪ ዲ/ን ሄኖክ ሞገስ


╔​✞═══●◉❖◉●═════7
@linkortodoxe21
╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝

ዜማ ቅዱስ ያሬድ
#አምላክ_ሆይ_ባርክልን_በዓሉን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

ባርክልን ኧኸ በዓሉን
ለዛሬ ዓመት ኧኸ አድርሰን
ሠላም ፍቅር ኧኸ አድለን
በዕምነታችን ኧኸ አበርታን
በአንድነት ኧኸ አቁመን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

ጽኑ ሠላም ኧኸ ለሐገሪቱ
እንዲጦሩ ኧኸ አዛውንቱ
ወጣቱ እና ኧኸ ሕጻናቱ
ያለ ጊዜ ኧኸ እንዳይሞቱ
አንድም ሳይጎድል ኧኸ በመሃላችን
ለዓመት ያብቃን ኧኸ አምላካችን

አምላክ ሆይ ባርክልን በዓሉን /2/

አገልጋዩን ኧኸ ከመቅደሱ
እንዲኖሩ ኧኸ ሲያወድሱ
ታቦቱንም ኧኸ ከመንበሩ
አታናውጠው ኧኸ ከደብሩ
ወታደሩን ኧኸ በድንበሩ
ጠብቅልን ኧኸ በበረከት
ቸሩ ጌታ ኧኸ የፍቅር አባት

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/

ለባርኮ ኧኸ አውደ ዓመት
ንዒ ማርያም ኧኸ በምሕረት
ያዘነው ኧኸ እንዲጽናና
የተከዘው ኧኸ እንዲል ቀና
በሐገር ውስጥ ኧኸ ውጭም ላለው
በበረከት ኧኸ አትለይው

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/

የናቁሽም ኧኸ ጽዮን ብለው
ይሠግዳሉ ኧኸ ፊትሽ ወድቀው
ካኅናቱ ኧኸ በማሕሌቱ
በቅዳሴው ኧኸ በሠዓታቱ
ከልጅሽ ጋር ኧኸ ከዓለም ጌታ
ዘመሩልሽ ኧኸ በዕልልታ

ድንግል ሆይ ባርኪልን በዓሉን /2/
ባርኪልን ኧኸ /4/


ዘማሪት ፅጌሬዳ ጥላሁን ና
ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው


╔​✞═══●◉❖◉●═════✞╗
@linkortodoxe21

╚✞═══●◉❖◉●═════​✞╝
ሌሎች የእንቁጣጣሽ መዝሙሮችን ማግኘት ከፈለጉ ከላይ ያለውን forwarde በመንካት ወደ ቻናላችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን

​​🌺🌼አበባዮሽ🌺🌼

እሰይ /ደስ ደስ ይበለን/(፪)🌼
አዲሱ አመት መጣልን ደስ ደስ ይበለን

ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ጌቶች አሉ ብለን🌻
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
እሜቴ አሉ ብለን
ሆ ብለን መጣን ሆ ብለን(፪)
ዘመን መጣ ብለን
🌼🌼
አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ባልንጀሮቼ - - - ለምለም
ግቡ በተራ - - - ለምለም🌼
በእግዚአብሔር መቅደስ - - - ለምለም
በዚያች ተራራ - - - ለምለም
እንድታደንቁ - - - ለምለም
የአምላክን ሥራ - - - ለምለም
ህይወት ያገኛል - - - ለምለም
እርሱን የጠራ - - - ለምለም

🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼

አበባዮሽ - - - ለምለም (፪)
ክረምት አለፈ - - -ለምለም
ጨለማው ጠፋ- - - ለምለም
የመስቀሉ ቃል - - -ለምለም
ሆነልን ደስታ - - -ለምለም
እናገልግለው - - - ለምለም
ቤቱ ገብተን - - - ለምለም
ትንሽ ትልቁ - - - ለምለም
ተሰልፈን - - - ለምለም🌾

🌺አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌼

አበባዮሽ - - -ለምለም(፪)
ያንን ኩነኔ - - - ለምለም
ዘመነ ፍዳ - - - ለምለም
የሞቱ በራፍ - - - ለምለም
ያ ምድረበዳ - - - ለምለም
ልክ አንደ ክረምት - - - ለምለም
ሄደ ተገፎ - - - ለምለም
ፀሐይ ወጣልን - - - ለምለም
ጨለማው አልፎ - - - ለምለም🌼

🌸አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌺

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው መስከረም - - - ለምለም
ይኸው ፀሐይ - - - ለምለም
ንጉሡ ወርዶ - - - ለምለም
ከላይ ሰማይ - - -ለምለም🌼
አውደ ዓመት ሆነ - - - ለምለም
ደስታ ሰላም - - - ለምለም
ፍቅር ሲገለጥ - - - ለምለም
በአርያም🌿 - - - ለምለም

💐አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪)🌻

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ይኸው አበባ - - - ለምለም
ለምለም ቄጤማ🌾 - - - ለምለም
አዲሱ ዘመን - - - ለምለም
አምጥቷልና - - - ለምለም
በሩን ክፈቱ - - - ለምለም
መኳንንቶቹ - - - ለምለም
የክብር ንጉሥ - - - ለምለም
ይግባ ቤታችሁ - - - ለምለም

🌹አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ(፪) 🌼

አበባዮሽ - - - ለምለም(፪)
ቤታችሁ ይሙላ - - - ለምለም
ሰላም ደስታ - - - ለምለም🌼
ሰጥቷችሁ እርሱ - - - ለምለም
የሁሉ ጌታ - - - ለምለም
ከዘመን ዘመን - - - ለምለም
ያሸጋግራችሁ - - - ለምለም🌺
የሽበትን ዘር - - - ለምለም
ይሸልማችሁ - - - ለምለም

🌼አበባ አበባ ፈካ ዘመን ሲተካ🌼

ይሸታል ዶሮ የእማምዬ ጓሮ
ይሸታል ጠጅ ጠጅ የአባብዬ ደጅ🌼

አብዬ ኧኸ አባብዬ
ደግሞም እማምዬ
መጣሁ ለሰላምታ🌺
ከቤት አሉ ብዬ
እንኳን ለአዲሱ ዓመት
አደረሰዎት ብዬ💐
🌼
ከብረው ይቆዩን ከብረው
የክብርን ወንጌል ሰምተው🌼
የበጉን ሥጋ በልተው
የአምላክን ፊቱን አይተው
ከብረው ይቆዩን ከብረው🌸

መዝሙር
🌺በዘማሪያን🌼
ወርቅነሽ ተፈራና ፅጌሬዳ ጥላሁን

<< በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ
ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል >>
መዝ ፷፭፥፲፩🌼

@linkortodoxe21
2025/01/04 00:14:47
Back to Top
HTML Embed Code: