tgoop.com/livescoreET/4757
Last Update:
ጣልያን ወይስ ስፔን ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ?
👉 ዛሬ ማታ ከምሽቱ 4 ሰአት በትልቁ ስታድየም ዌንብለይ ሁለቱም የአውሮፓ የእግርኳስ ሀያለን ሀገሮች ይገናኛሉ። ምርጥ ብቃት እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ጣልያኖች ወይስ እየተሻሻሉ የመጡት ስፔኖች ወደ ዩሮ 2020 የፍፃሜ ጨዋታ ያልፋሉ?
የእርስ በእርስ ግንኙነት
👉 በታሪካቸው ስፔን እና ጣልያን 37 ግዜ መገናኘት የቻሉት ሲሆን ጣልያን 11 ጨዋታዎች ሲያሸንፉ በተመሳሳይ ስፔን 11 ግዜ ጣልያንን መርታት ችለዋል። በተቀሩት 15 ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል።
👉 ካለፉት አምስት ጨዋታዎች የእርስ በእርስ ግንኘነት ስፔን ሁለት ግዜ በማሸነፍ የበላይነት ስይዙ ጣልያን አንድ ግዜ ብቻ ነው ማሸነፍ የቻሉት። በተቀሩት ሁለት ጨዋታዎች አቻ መለያየት ችለው ነበር።
👉 ካለፉት አምስት ጨዋታዎች ጎል በማስቆጠር አሁንም የበላይነት ያላቸው ስፐይኖች ሲሆኑ 6 ጎል ማስቆጠር ችለዋል ጣልያን 4 ጎል ማስቆጠር ችለዋል።
👉 ወቅታዊ አቋም ስንመለከት ጣልያን የተሻለ ጥንካሬ እና የተሻለ የማሸነፍ ስነልቦና ያላቸው ሲሆኑ እስከአሁን በዩሮ አቻም ሽንፈትም አልቀመሱም። በስፔን በኩል ምንም እንኳን በመጀመሪያ 2 የምድብ ጨዋታዎች አቻ ቢለያዩም ከዚያ በኋላ ግን እየተሻሻሉ መምጣት ችለዋል።
ታድያ ዛሬ ምሽትስ ወደ ፍፃሜው ጨዋታ ማን ያልፋል?
@livescoreET
BY LIVE SCORE🤌
Share with your friend now:
tgoop.com/livescoreET/4757