tgoop.com/love_history9/2432
Last Update:
ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 5
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
የምገዛቸውንም ሆነ የምለብሳቸውን ልብሶች የሚመርጥልኝ የፀጉር ስታይሌን የሚመርጥልኝ እሱ ሆኗል የማክ አባት ጭራሽ ባሌ መሆኑን እረስቼዋለሁ አንድ ቀን አምሽተን ከውጪ እንደገባን ከመኪና ሳንወርድ ሄዋኔ ብሎ ጠራኝ ወዬ ማክ አልኩት በፍቅር እያየሁት ነይማ የሆነ ነገር አለ ፀጉርሽ ላይ አለኝ ወደኔ እየተጠጋ ወደሱ ስቀርብ ድንገት ሳመኝ በደስታ ልሞት ምንም አልቀረኝም ጉንጮቼ ቀሉ ሲያልበኝ ይታወቀኛል ክፍሌ ገብቼ በደስታ አልጋዬ ላይ ዘለልኩኝ ወንድ ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ነው እሱም ብቻ ሳይሆን እኔ የምወደው ቀን ከሌሊት የማስበው ማክ እኮ ነው የሳመኝ!!! በደስታ የምሆነውን አጣው ልብሴን ቀይሬ ለመተኛት ብሞክር አልቻልኩም የማስበው ማክንና የማክን የመጀመሪያ ኪስ ብቻ ነበር ድንገት መደወልና ድምፁን መስማት ፈለኩ ልደውል ስል ደውዬ የምለው ነገር ግራ ገባኝ ስልኬን ይዤው ለብዙ ደቂቃዎች ማሠብ ጀመርኩ በመሀል ስልኬ ጠራ ማክ ነበር ሴኮንድ አላባከንኩኝም ማክ አልኩት ወዬ አልተኛሽም እንዴ አለኝ እንቅልፍ እንቢ አለኝ አልኩት ለምን ምን እያሰብሽ አለኝ አንተን አልኩት ድንገት ከአፌ ያመለጠ ቃል ነበር ስለኔ ምን አለኝ አፍሬ ዝም አልኩት እኔም ስላንቺ እያሰብኩ ነበር
የዛን ቀን ለረጅም ሰአታት አወራን ሌሊቱ አላልቅ ብሎኝ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ማክን እያሰብኩ ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ አሸለበኝ ጠዋት የአዙ ድምፅ ነበር ያነቃኝ ሄዋንዬ ዛሬ ተኝተሽ ልትውይ ነው እንዴ አለችኝ መጋረጃውን እየከፈተች በይ ተነሽ አለችኝ የለበስኩትን እየገለጠች በግድ አይኔን ገልጬ እንዴት አደርሽ አዙ አልኳት ለመነሳት እየተንጠራራው እግዛሄር ይመስገን ጎሽ ተነሽ! ጋሽዬ ለቁርስ እየጠበቁሽ ነው አለች ልነሳ የነበረው እንደዛ ስትለኝ ተመልሼ ተኛሁ በግድ አስነሳችኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሄድኩ ትላንት የሆነውን እየፈነደኩ ነገርኳት
አንቺ ልጅ እኔ አላማረኝም አለች የመከፋት ፊት እየተነበበባት እኔ ንግግሯን ከምንም ሳልቆጥር አዙ ደግሞ ዝም ብለሽ ታካብጂያለሽ አልኳት የምለብሰውን እየመረጥኩ አዙ ይሄ ያምራል ወይስ ይሄ አልኳት በሁለት እጆቼ የያዝኩትን ልብስ እያማራጥኳት ኤዲያ እኔ ምኑም አላማረኝም አንዱን ልበሽና ይልቅ ተከተይኝ አታስጠብቂያቸው ብላኝ ጥላኝ ወጣች እኔ እየዘፈንኩና በደስታ እንደ ህፃን እየፈነደኩ ወደታች ስወርድ የማክ አባት ፊት ተቀያይሯል ምነው ደና አይደለህም እንዴ አሞሀል አልኩት መልስ የለም ዛሬ ከቤት እንዳትወጪ አለኝ ማስጠንቀቂያ በሚመስል ድምፅ እንዴ ለምን አልኩት ግራ እየተጋባው ባልሽ መሆኔን ላስታውስሽ አለኝ ቀና ብሎ ያልተለመደ ፊት እያሳየኝ በዚህ መሀል ነበር ማክ እንደምን አደራቹ እያለ የወረደው የማክ አባት ምንም ሳይመልስ ከተቀመጠበት ተነስቶ ያልኩሽን እንዳትረሺ መልካም ቀን ብሎኝ ወጣ
ማክ ግራ በመጋባት እያየኝ ምን ሆኖ ነው ተጣለቹ አለኝ ያለኝን ነገርኩት ማታ ስስምሽ አይቶ ይሆን እንዴ አለኝ ባባቱ ሁኔታ ግራ እንደተጋባ እ ይሆናል አሁን ምን እናድርግ አልኩት ትንሽ እስከሚረጋጋ በቃ አንወጣም ነገሮችን እናስተካክላለን አይዞሽ አለኝ ተነስቶ በድጋሚ እየሳመኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱ እስኪረጋጋ ከቤት ባንወጣም ግን አንድ ላይ ሆነ የምናሳልፈው ሁለታችንም በፍቅር ከንፈናል አባቱ ሲመጣ ፊት ለፊቱ እንደበፊቱ እናወራለን ግን በቃ ቤቱን በአንድ እግሩ ስናቆመው ነው የምንውለው የቤቱም ሰራተኞች በእኛ ሳይድ ነበሩና ማንም ለማን ምንም አይናገርም ነበር እኛ በድብቅ ፍቅራችንን እያጣጣምን ነው ከማክ ጋር ከመሳሳም ውጪ ምንም አናደርግም ሲውል ሲያድር በድብቅ አንድ ቀን እኔ ጋር ሌላ ቀን እሱ ጋር ነው የምናድረው እስከምንጋባ ምንም ላናደርግ ወስነናል በቃ በጣም የሚያስቀና ፍቅር ውስጥ ገብተናል ማክ ወደ አውስትራሊያ ላለመመለስ ከተመለሰም አብረን እንደሆነ ወስኗል
አንድ ቀን እሁድ የማክ አባት እንደሚፈልገኝ በአዙ በኩል ልኮብኝ ስሄድ በረንዳ ላይ አኩርፎ ተቀምጧል ሄዋን አለኝ የሆነ ቁጣ ባዘለ ድምፅ አቤት አልኩት ምን ሊለኝ ነው በሚል ፍራቻ እንደተጋባን ዝግጁ አይደለሁም ምናምን በሚል ተራ ምክንያት እስካሁን ለብቻሽ እየተኛሽ ነው እኔም ስለምወድሽና ስሜትሽን ላለመጋፋት ታግሼሻለሁ አሁን ግን የሚበቃ ይመስለኛል የማሰቢያ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ ካልሆነ ግን ወደ ነበርሽበት ህይወት ትመለሻለሽ አለኝ ዛቻ ባዘለ ድምፅ ንግግሩ አናዶኝ ልሄድ ስል አልጨረስኩም አለ ቆጣ ብሎ ከልጄ ጋር ያለውን ነገር የማላውቀው እንዳይመስልሽ ከዚህ ቤት ብወጣ እሱ አለልኝ ብለሽ ከሆነ እንዳታስቢ ሁሉን ነገር አሰቤበታለው ደግሞ ማክቤል ለአንቺ የሚሆን ልጅ አይደለም አባትሽን በማታገኚው ነገር ላይ ተማምነሽ እንዳታሳዝኚው የአባትሽ ከባድ ሚስጥር በእጄ ላይ ነው አለ አንቺ አይሆንም የምትይ ከሆነ ባባትሽ ፈርደሽ ነው አለኝ.....
@love_history9
✎ ክፍል ስድስት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
join @love_history9
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
BY Love_history
Share with your friend now:
tgoop.com/love_history9/2432