tgoop.com/love_history9/2436
Last Update:
ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 6
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ አምላኬ ሆይ አንተ ትግስቱን ስጠኝ አልኩኝ በውስጤ ደስታዬ ላይ ውሀ ቸለሰበት ክፍሌን ዘግቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ምንድነው የማረገው አሁን ለማክ ልንገረው ወይስ ይቅር እያልኩ ሳስብ ማክ ደወለ ሄዋንዬ እስካሁን ተኝተሻል እንዴ አለኝ ገና መነሳቱ ነበር አይ ቆየው አልኩት ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ በስልክ አይሆንም ናና እናወራለን አልኩት ደቂቃ አልፈጀበትም ነበር አባቱ ያለውን ስነግረው በጣም ደነገጠ ምን ማድረግ እንዳለብን እያሰብን በቃ አይዞሽ አንቺ ብቻ አትከፊ መፍትሔ አናጣም አለኝ
ድንገት ለምን አባትሽ እና አባቴን የሚያስተሳስራቸውን ነገር አባትሽን አጠይቂውም ከዛ በምንችለው መንገድ ዶክሜንቱን መውሰድ ከዛ በኃላ ያለውን ነገር እንጋፈጣለን አለኝ አባቴ ለነገሮች ድብቅና ሀይለኛ እንደሆነ ባውቅም በማክ ሀሳብ ተስማማው ጥሩ በቃ ዛሬ ከአባቴ ጋር እናወራለን አልኩት ተነስቼ እንድተጣጠብና አባቴ ጋር አብረን እንደምንሄድ እሱ ውጪ እንደሚጠብቀኝ ተነጋግረን እሱም ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡
በተባባልነው መሠረት ወደ አባቴ ጋር ለመሄድ ስንወጣ የማክ አባት ወዴት ነው አለን ከላይ መኝታ ቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ
እንዴ አባዬ አለህ እንዴ አለው ወደ አባቱ እየተመለከተ አዎ አለው ወዴት ነው አለ ደግሞ እየጠየቀ ምን ትላንት ለሰው መስጠት የነበረብኝ እቃ ነበር ቦታውን ስላላወኩት አሁን ሄዋንን አሳይኝ ብያት እሺ ብላኝ እየሄድን ነው እንዳለህ አላወኩም ነበር አለው ጥሩ ቶሎ ተመለሱ አለው ፊቱ ሳይፈታ ዋናው መፍቀዱ ነው አልኩ ተመለሽ የሚለኝ መስሎኝ በጣም ፈርቼ ነበር ከግቢ እንደወጣን ተረጋጊ የኔ ቆንጆ ብሎ ሳመኝ
ማክ ፈራሁ አልኩት እጁን አጥብቄ ይዤ
አትፍሪ ምንም አይመጣም መቼም አንለያይም ካልሆነ እንጠፋለን አለኝ ለመቀለድ እየሞከረ እስኪ አትቀልድ ለራሴ ጨንቆኛል አልኩት አይዞሽ የኔ ቆንጆ ሁሉም ይስተካከላል አለኝ አባቴ ቤት ደረስን አናግረሻቸው ነይ አለኝ ማክ እሱም ጨንቆታል አባቴ ቁጭ ብሎ ስልኩ ላይ ካርታ ይጫወታል አባዬ አልኩት እንዴ ሄዋኔ ምን እግር ጣለሽ ለምን መጣሽ አለኝ ቀና ብሎ እየሳመኝ እንዴ እንደዚህ ይባላል እንዴ አልናፍቅህም አልኩት አይ እንዴት ሳትነግሪኝ ብዬ ነው አለኝ ምንም ሳይመስለው አባቴ ለኔ ግድ የለውም ሁሌ ይገርመኛል እናቴ ከሞተች በኃላ ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው ያደኩት
ፈልጌህ ነበር አባ አልኩት አሁንም ቀና ብሎ ሳያየኝ ምነው በሰላም አለኝ አዎ ምንድነው አቶ ሽፈራው አንተን የሚያስፈራራበት ሚስጥር ምንድነው አልኩት የሰማውን ማመን አልቻለም በጣም ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለና አንቺ እንዴት አወቅሽ ሊመታኝ በሚመስል ሁኔታ አፍጥጦ እንዴ አባ የዚህን ያህል ከባድ ሚስጥር ነው እንዴ ለኔ ለልጅህ የማይነገር ?? አልኩት ልጅ ያሳጣሽ ዝም በይ ብሎ ጮኸብኝ ሁኔታው በጣም ነበር የሚያስፈራው ምንም ሳልተነፍስ ጥጌን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ ነኝ አባቴ በንዴት ቤቱን እየዞረው ነው ድንገት ቆም ብሎ ቆይ አንቺ በመሀላችን ሚስጥር እንዳለ በምን አወቅሽ አለኝ ስሩ እስጊገተር እየጮኸ
እ ....ያው ሽፈራው ነው የነገረኝ አልኩት እየተንቀጠቀጥኩ እኮ እንዴት አለኝ አይኑን እንዳፈጠጠ እ ...አብረን መተኛት አለብን ነው የሚለው አልኩት ቃላቱን ለመጨረስ እየፈራው ያባቴ ንዴት ይባስ ጨመረ እና ለምን አተኝም ታዲያ ያገባሽ የቤቱ ጌጥ ሊያረግሽ ኖሯል አንቺን ቤቱ አስቀምጦ የሚቀልብበት ምንም እዳ የለውም ትሰሚኛለሽ ምንም ጊዜ ሳታባክኚ አሁኑኑ ሄደሽ ይቅርታ ጠይቀሽ የሚልሽን ካለምንም ድርድር ፈፅሚ አለኝ ቁርጥ ባለ ድምፅ ጌታዬ ሆይ መፍትሔ ፍለጋ መጥቼ ጭራሽ አጣብቂኝ ውስጥ ልግባ አልኩኝ ለራሴ፡፡ አሁን ማጉረምረሙን ትተሽ ዳይ ወደ ባልሽ ደሞ ከኔ ጋር እንዳወራንም ሆነ እንደመጣሽ እንዳትነግሪው አለኝ
ቦርሳዬን አንሴቼ ሳልሰናበተው እንኳን እየሮጥኩ ወጣሁ......
✎ ክፍል ሰባት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
🥀✨@love_history9✨🥀
🥀✨@love_history9✨🥀
🥀✨@love_history9✨
BY Love_history
Share with your friend now:
tgoop.com/love_history9/2436