tgoop.com/love_history9/2439
Last Update:
ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨·...............:¨·.❣
♥️ ክፍል 8
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
የማክ አባት ለማክ ወደ አውስትራሊያ መቼ ልትመለስ አሰብክ አለው ማክ አባቱ ቶሎ ሊገላገለው መፈለጉን ቢረዳም እንዴ አባዬ ሰለቸውህ እንዴ አለው በቀልድ መልክ አይ ነገሩን ነው ለእህቶችህ የምትወስደውን ነገሮች እንድናዘጋጅልህ ነው አለው ለመሄድ እየተነሳ ሽፈራው እንደወጣ ካረጋገጥን በኃላ እኔና ማክ ልክ ከተገናኘን የቆየን ይመስል ተናንቀን ተሳሳምን ማክ ይሄ የድብቅ ህይወት ማብቃት አለበት አልኩት ልክ ነሽ የኔ ፍቅር እኔም እያሰብኩበት ነው አለኝ
ግን እንዴት እንደሆነ ለሁለታችንም ግራ ገብቶናል ማክ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ ለምን አንወጣም አልኩት አዎ እንደውም ልወስድሽ ያሰብኩበት ቦታ አለ ዛሬ አለኝ
የት አልኩት እንደህፃን እየተቁነጠነጥኩ
እሱማ ሰርፕራይዝ ነው ባይሆን ተነሽ ልበሽና እንውጣ አለኝ ጊዜ አላባከንኩም እየፈነደኩ ወደ ላይ ስወጣ ማክ በግርምት ቆሞ ያየኛል ልብሴን ለመልበስ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበር ለባብሼ ከመቅፅበት ወጣው አቤት ፍጥነት ይሄኔ ሰርፕራይዝ ባይሆን ባመትሽም አትወጪም ነበር አለኝ ከእቅፉ እያስገባኝ
ታዲያ ሁሌ ቶሎ እንድወጣ ለምን ሰርፕራይዝ አታዘጋጅም? አልኩት እየሣምኩት እኔና ማክ ብቻችንን ስንሆን አለምን እንረሳለን በቃ ምንም ትዝ አይለንም አሁን እንኳን እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ እያለፍን እንኳን በኛ ፍቅር መካከል ምንም የተቀየረ ነገር የለም
እንደውም ፍቅራችን በጣም እያማረበት ነው አንዳችን ካላንዳችን መኖር እስከማንችል እስከሚመስለን ድረስ ፍቅር ጨምረናል ልክ ማክ ያለኝ ቦታ ልንደርስ ስንል አይኔን እንድጨፍን ነገረኝ
ማክዬ ቸኮልኩ አልኩት ደርሰናል ብሎ መኪናውን ሲያቆም ተሰማኝ አይኔን እንደጨፈንኩ በማክ መሪነት ወደሚገርመው የማክ ሰርፕራይዝ አመራን አይኔን ማመን ነበር ያቃተኝ እኔ አላምንም ብዬ ማክ ላይ ተጠምጥሜ የደስታ እንባ አነባሁ ማክ ወደገዛው አስደናቂና ውብ ቤት ስንገባ እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልዕልት የሚል በሰፋፊው ተፅፏል ቤቱ በሚያማምሩ የቤት እቃዎችና አበባዎች አሸብርቋል፡፡
ደስታዬ ወደር አጣ የምናገረው ጠፋብኝ ማክ ላይ ተጠመጠምኩበት እንደኔ የታደለች ሴት አለም ላይ የለችም እኮ አልኩት እየሳምኩት እኔም እድለኛ ነኝ አባቴ አንቺን ስላመጣልኝ አለኝ ወዲያው ደስታዬ ጠፋ የረሳሁትን ነገር አስታወሰኝ
ማክ የፊታችን ገፅታ መቀያየር አይቶ አትዘኝ የኔ ማር የምታዝኚበት ቀን አብቅቷል አለኝ እንዴ ማክ አልኩት ሽሽሽ....አለኝ ወዳንገቱ ስር እያስገባኝ
በቃ አብቅቷል አለኝ ያባትና የልጅ ፍልሚያ ተጀመረ የዛን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ውጭ አደርን፡፡ ሽፈራው ደጋግሞ ቢደውልም አላነሳንም ማክ ሁሉንም ነገር ተዘጋጅቶበት ነበር እኔ ሳላውቅ ከአዙ ጋር ተመካክረው ጠቃሚ የምላቸውን ነገሮችና ልብሶች በሻንጣ አዘጋጅተዋል
እሱም እንደዛው በሁኔታው መገረሜን እስካሁን አላቆምኩም ሁሌም የማክ መልካምነት ይገርመኛል ቤታችን የመጀመሪያዋን ለሊት አሳለፍን የነፃነት ትንፋሽ እየተነፈስኩ አደርኩ ከማክ ውጪ የነበርኩዋቸው አስቀያሚ ትርጉም አልባ ጊዜቶች ሳስታውስ ይበልጥ ነፃነት ታወቀኝ ማክን እንደተኛ ይበልጥ እቅፍ አደረኩት ማክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ አትተኛም እንዴ የኔ ውድ አለኝ ደረቱን ተደግፌ አሸለበኝ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችንን አስቆጥረናል ከቤት ከወጣን ሽፈራውና አባቴ እያፈላለጉን እንደሆነ አዙ ነግራናለች ማክ አባቱን ማናገር እንዳለበትና ነገሮችን በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማይችሉ ነግሮኝ ከቤት ወጣ፡፡ ማክ አባቱን አናግሮ እስከሚመጣ በጭንቀት ሞትኩ በተደጋጋሚ ስደውልለት አያነሳም ሲጨንቀኝ አዙ ጋር ስደውል ማክና አባቱ ለረጅም ሰዓት ሲጨቃጨቁ ቆይተው በመጨረሻም ተጣልተው እንደተለያዩ እና ከቤት ከወጣም እንዳልቆየ ነገረኝ......
✎ ክፍል ዘጠኝ ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
••●◉Join us share
┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
🥀@love_history9🥀
🥀@love_history9🥀
🥀@love_history9🥀
┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━
BY Love_history
Share with your friend now:
tgoop.com/love_history9/2439