tgoop.com/love_history9/2451
Last Update:
.
ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
" ምዕራፍ ሁለት🌺 "
♥️ ክፍል 18
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ
💔🥀የመጨረሻው ክፍል💔🥀
በረጅሙ ተንፍሶ ትንሽ ቆይቶ ያባትሽ ብትር እናትሽ ላይ አረፈ ...እንዴት እኔ ይሄንን አላምንም ብዬ ጮህኩ ሄዊ ተረጋጊ አለኝ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ ራሴን ማረጋጋት ፍፁም ተሳነኝ በር ዘግቼ ማልቀስ ሆነ ስራዬ አልበላም አልጠጣም አባቴን ሄጄ ብገለው ደስታዬ ነበር ግን የማክ ቁጥጥር አደለም ከቤት መውጣት ስልኬን እስከመቀማት ደርሶ ነበር ማክ ከስጦታ ጋር ጊዜዬን እንዳሳልፍና ነገሮችን እንድረሳ የማይጥረው ነገር አልነበረም ከቀን ወደቀን ትንሽ እየተሻለኝ ቢመጣም ግን የእናቴ አሟሟት መርሳት አልቻልኩም ትዝ ይለኛል እናቴ በጣም ሳቂታና ተጫዋች ነበረች ሁሌም እሷ ነበረች ከትምህርት ቤት የምታመጣኝ ጠዋት
ት/ት አድርሳኝ ባልተለመደ ሁኔታ በጣም አቅፋ ስማኝ ነበር፡፡ ታዲያ ወደቤት ስመለስ ብቻዬን ነበር ሰው ሁላ ቤታችን ተሰብስቧል እናቴን በዛ ትርምስ ውስጥ ስፈልግ ያየኝ ሁሉ ልጅ አይደለች ምኑን አውቃው እያሉ በሀዘኔታ ከንፈራቸውን ይመጡልኛል፡፡ እኔ በወቅቱ ምንም አልገባኝም ነበር እናቴ ላትመለስ አሸልባለች ባልሰራችው ሀፂያት ተቀጥታለች ከናቴ ድንገተኛ ሞት በኃላ አባቴ ይባስ ጨከነብኝ ለኔ ጭራሽ ግድ አልነበረውም አንዳንዴ እማዋ ቤት እንኩዋን ሳድር የት ገባች ብሎ አይፈልገኝም በራሴ ጥረትና በጎረቤት ፍርፋሪ ነው ያደኩት ይኸው በመጨረሻም ለወንጀሉ ተባባሪ ለሆነው ሰው ሸጦኝ እሱም አልበቃ ብሎት ሲያሳድደኝ ነበር የእናቴን ገዳይም ሆነ ተባባሪ ለህግ አሳልፌ ሳልሰጥ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ ለራሴ ቃል ገባሁ ማክን ጠርቼ እነዚህን መረጃዎች ከየት እንዳመጣና ተልኮልኝ የነበረው ፋይል የት እንደሆነ ጠየኩት ሄዊዬ ቃሌን ፈፅሚያለው እስክትረጋጊ ነበር የጠበኩሽ እንጂ ሁሉም በህግ ስር ከዋለ ሳምንት አልፏቸዋል አለኝ እንዴት ማክ አልኩት በአድናቆት እያየሁት በመጀመሪያ ነበር
አባትሽ እናትሽን እንደገደላት ያወኩት እንደውም ካስታወሽ መጀመሪያ አባቴን ላናግረው የሄድኩኝ ቀን አስታወሽ አለኝ አ....አዎ እንደውም ቆይተህብኝ ተጨንቄ አዙ ጋር የደወልኩት ሰዓት አልኩት ለመስማት እየጓጓው እክል እንደሚገጥምሽ ገመትኩ ከዛ ያለውን ነገር ሁሉ አንቺ እንዳትገቢበት እየተከላከልኩ አጣራሁ ለዛ ነበር ይሄን ክትትል እንዳቆም አባቴ አስደብድቦኝ የነበረው ከዛም እኔ የሆነ የተደበቀ ነገር እንዳለ ይበልጥ ስለጠረጠርኩ በክትትሌ ገፋሁበት እናም በመጨረሻም የናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽና በማግስቱ በማታውቂው ቁጥር ቴክስት እንደመጣልሽ የነገርሽኝ አስታወስኩ የሚስጥሩ መፍቻ ቁልፍ እሳቸው እንደሆኑ ተረዳው እናም ሆነ አለኝ እና ይሄን ሁላ ነገር የነገሩህ እሳቸው ናቸው አልኩት አሁንም ማልቀሴን ማቆም አልቻልኩም ....አዎ ያው በመጀመሪያ ተቸግረን ነበር በኃላ ግን በልጆቻቸው ስናስፈራራቸው አመኑ ሁሉንም ነገር ተናገሩ ታዲያ እናቴ እንዴት ሞተች አልኩት ያው እራሷን እንዳጠፋች ነበር ተደርጎ የተወራው ግን አንቺ ልጅ ስለነበርሽ ፊት ለፊትሽ አልተወራም ለዛ ነው ያላስታወሺው ለማንኛውም አሁን ዝግጁ ከሆንሽ ፖሊስ ጣቢያ ሄደሽ ቃል ትሰጫለሽ ብሎ አቅፎ ሳመኝ የናቴ ጉዳዮች ለፍርድ በመብቃታቸው ብደሰትም እናቴን ግን ለዘላለም አጥቻታለሁና መርሳት አልቻልኩም እንዴት ልረሳት እችላለሁ ለዛውም በግፍ ያለሀፂያትዋ የተቀጣችው እናቴን አሁን ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ ስጦታም እያደገች ነው ቤተሰቤ ደስ የሚል ፍቅር አለው ዛሬ የስጦታ ሶስተኛ አመት የልደት ቀን ነው የማክ ወንድምና እህቱ እዚሁ ናቸው፡፡ ወንድሙ ጠቅልሎ ከመጣ አመት ያልፈዋል ከሳምንት በኃላ በአባቱ ቤት ይሞሸራል ማክ በጣም ደስተኛ ሆኗል ዛሬ ደግሞ የምነግረው አስደሳች ዜና አለኝ ማክና ስጦታ የኔ የህይወቴ መጀመሪያ ስጦታዎቼ ናቸው፡፡ ማክ አልኩት ወዬ ሄዊዬ የኔ ፍቅር አለኝ በቅርቡ ሌላ የቤተሰብ አካል ቤተሰባችንን ይቀላቀላል እርጉዝ ነኝ አልኩት ማክ እራሱን መቆጣጠር አልቻለም በደስታ መጮህ ጀመረ ሚስቴ ሄዊ እርጉዝ ናት ብሎ ለታዳሚው ጮሆ ተናገረ እኔና ስጦታን አቅፎ የደስታ እንባ አነባ...
የመጀመሪያዬ ፍፃሚዬም ሆነ እስከለተሞቴ ላልለየው ፅኑ ቃል♥️ አለኝ፡፡
✎ ውድ የእውነተኛ ስሜት🌺 ቤተሰቦች ታሪኩን እንዴት አገኛችሁት መቼም የማይረሳ ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ እንደሰነቃቹ አልጠራጠርም በሌላ ድርሰት እስከምንገኛኝ ድረስ ባላችሁለት ሰላማችሁ ይብዛልን አስተያየታችሁን አድርሱኝ መልካም ጊዜ።🌺
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
✨#እውነተኛ_ስሜት✨
🥀@love_history9
BY Love_history
Share with your friend now:
tgoop.com/love_history9/2451