tgoop.com/mafear/8327
Create:
Last Update:
Last Update:
"ሐብት ስጠን ብለን አንለምንም ምክንያቱም ጤና ያለው ሰው ሐብት ማግኘት ይችላልና፤ ከብዙ ገንዘብ በላይ ብዙ ዘመድ አዝማድ እንዲኖረን እንሻለን። ከእንሰሶች የምንለየው ዝምድናን ስለምናከብር ነው። አንድ እንሰሳ ጀርባውን ሲበላው ለማከክ ከዛፍ ጋር ያፋትጋል፤ እኛ ግን ወገን ስላለን እንዲያክልን እንጠራዋለን፣ ያክልናልም።" (141)
፧
"አንድ ሰው ዘመድ አዝማዱን ለድግስ ሲጠራ ሊያበላቸው አስቦ አይደለም፤ ምግብማ ሁሉም ከቤታቸው አላቸው። ከመጫወቻ ሜዳችን ላይ በጨረቃ ብርሐን ስንሰባሰብ ምክንያታችን የጨረቃዋ ብርሐን አይደለም፤ ሁሉም ሰው ግቢው ውስጥ ቁጭ ብሎ ብርሐኗን ማስተዋል ይችላል። የምንሰባሰበው ዝምንድናችን እንዲጠነክር ነው።" (142)
•
"Things fall Apart" Chinua Achebe፣ ሰለሞን ዳኜ ቸኮል "ለየቅል" ብሎ እንደመለሰው
@Noahtoaels_idea
BY Ex's Vs crush

Share with your friend now:
tgoop.com/mafear/8327