Telegram Web
ማኀበራዊ ቀውስ ባለባቸው  አካባቢዎች ድጋፍ  እየተደረገ እንደሚገኝ በማኀበረ ቅዱሳን የሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት አስታወቀ ፡፡

የካቲት ፲፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኀበረ ቅዱሳን የሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት በኢትዮጵያ ከፍተኛ  ቀውስ ባለባቸው አካባቢዎች  ማኀበራዊ ድጋፎችን የመለገስ፣በጦርነት፣በድርቅና በረሀብ ለተጎዱ ሕጻናት ድጎማ የማድረግ፣ማኅበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን የማጠናከር እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶች እንየተሰጡ እንደሚገኙ በማኀበረ ቅዱሳን የሙያ፣ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ዲያቆን ንጉሴ ባለውጊዜ  ገልጸዋል።

በተቻለ አቅም ማኀበራዊ ቀውስ ባለባቸው በሀገሪቱ በርካታ የክልል ቦታዎች ለሚገኙ ተጎጂዎች የተለያዩ ድጋፎችን  ከአጋርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ተደራሽ እያደረጉ  እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

አክለውም የተረጂዎች ቁጥር መብዛት፣የጸጥታ ችግርና የግብዓቶች የዋጋ ንረት መጨመር ድጋፎቹን ተደራሽ ከማድረግ ረገድ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶች በመሆናቸው እነዚህንም ለማቃለል ድጋፉ በሚሰጥባቸው አካባቢዎች ግብዓቶቹ ከእዛው እንዲገዙ እና ጉዳዩን ለሚመከታቸው አካላት ማሳወቅ በመፍትሔነት መሰጠቱን ምክትል ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

በጦርነት ምክንያት ከፍተኛ የተፈናቃይ ቁጥር በሚገኙባቸው የተፈናቃይ ጣቢያዎች ሰብዓዊ ድጋፎች በተከታታይነት እየተደረጉና በቀጣይም እንደሚደረጉ ዲያቆን ንጉሴ ጠቁመዋል፡፡
በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት የሚገኙ ግብረ ሠናይ ድርጅቶች፣የፋይናንስ ተቋማት፣መንግሥት እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት በተዘጋጁ የገንዘብ ማሳባሰቢያ የባንክ ቁጥሮች ላይ ገቢ በማድረግና በሌሎች መንገዶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ዳይሬክተሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-

1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
“ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ የድርሻዬን እወጣለው”
ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በቀጥታ ስርጭት ተሰናድቶ እየጠበቅዎ ይገኛል።

ቤተ ክርስቲያንን እንድናውቅ እና እንድናገለግል ምክንያት የሆኑንን ግቢ ጉባኤያት ለመደገፍ በቀጥታ ሥርጭት ላይ እንሳተፍ።

የግቢ ጉባኤያት ምሩቃን ዓለም አቀፍ ኅብረት በሚለው ግሩፓችን
                *ነገ ማታ ከምሽቱ  ከ2፥00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት ይጠብቁን።

https://www.tgoop.com/gibigubayat_mirukan_hibret
26 የደረጃ አንድ የሰባኪያነ ወንጌል ሠልጣኞች መመረቃቸውን በማኅበረ ቅዱሳን የአርባምንጭ ማእከል ገለጸ

የካቲት ፲፫/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የአርባምንጭ ማእከል ከከምባ ወረዳ ማእከል ጋር በመተባበር በከምባና ጋርዳ ማርታ ወረዳዎች፣ ከተለያዩ አጥቢያዎችና የስብከት ወንጌል መስጫ ማእከላት ለተወጣጡ 26 የደረጃ አንድ የሰባኪያነ ወንጌል ሠልጣኞች የካቲት 12 ቀን /2017 ዓ.ም አስመርቋል ::

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማእከል ተወካይ፣ የከምባ ወረዳ ቤተክህነት ተወካይ እና የከምባ ወረዳ ማእከል ስራ አስፈጻሚዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ በሠልጣኞች አጠር ያለ ትምህርተ ወንጌል የተሰጠ ሲሆን  ከአርባምንጭ ማእከል ስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል በመ/ር መብራቱ “እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ለዘለዓለም አይጠማም” በሚል ርዕስ ት/ተ ወንጌል ተሰጥጧል።

የከምባ ወረዳ ማዕከል ሰብሳቢ አቶ ቸርነት ጫሬ የወረዳ ማእከሉን መልዕክት አስተላልፈው ሥልጠናው የአርባምንጭ ማእከል ከከምባ ወረዳ ማእከል ጋር በጋራ እንደተዘጋጀ  በመግለጽ አርባምንጭ ማእከልን አመስግነዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን አርባምንጭ ማእከል ጽ/ቤት ኃላፊ  ዲ/ን ችሮት አበራ በመልእክታቸው ማ/ቅ አርባምንጭ ማእከል በእግዚአብሔር ቸርነት ላለፉት 5 ወራት ከሚመለከታቸው የቤ/ን አካላት ጋር በመተባበር 8364 አዳዲሰ አማንያን ወደ ቅድስት ቤ/ክን እንዲቀላቀሉ አድርጓል በማለት በተጨማሪም ሌሎችም በርካታ መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎቶች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም  በእንደዚህ አይነት ሐዋርያዊ አገልግሎት በዛሬው ዕለት የተመረቁ ሰባኪያነ ወንጌል በሚሰማሩበት አከባቢ በቋንቋቸው  በማስተማር  ለቅድስት ቤ/ክ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ገልጸው ጠንክረው እንዲያገለግሉ መክረዋል።
በመጨረሻም የሶስቱ አአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪ ቀሲስ መስፍን መኩሪያ “ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው” የሚለውን የመዝሙረ ዳዊት ቃል አንስተው በሥልጠናው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ ሠልጣኞች ጠንክረው እንዲያገለግሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሠልጣኞችም የነበራቸውን ቆይታ በመግለጽ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል የገቡ ሲሆን በማኅበረ ቅዱሳን የአርባምንጭ ማእከል በታኅሳስ06/2017 ዓ.ም ከአጋር አካላት ቃል የተገባውን መጽሐፋ ቅዱስ ለሁሉም ሠልጣኞች በቀሲስ መስፍን መኩሪያ ተበርክቶላቸዋል።
የገቢ ማስገኛ ሕንጻዎች እና ለአብነት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶች እየተገነቡ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡

የካቲት ፲፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

የቤተ ክርስቲያን ዕድገትና መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች አገልግሎት ጉባኤ በማኀበረ ቅዱሳን ሥር ከሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች አንዱ ሲሆን የግንዛቤ መፍጠር ሥራና ለፕሮጀክቶች ግንባታ የሚውሉ ሀብት የማፈላለግ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

ዲያቆን ደረጄ ጋረደው የአገልግሎት ጉባኤው ዳይሬክተር እንደተናገሩት ለገቢ ማስገኛ የሚሆኑ ሕንጻዎችና የአብነት ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታዎች እየተገነቡ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክት ዝግጅትና ትግበራ ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር ማስተዋል አበበ በበኩላቸው በክፍላችን አዘጋጅነት በርካታ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ ናቸው ከነዚህም ውስጥ በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት የሚገኘው በ115 ሚሊየን ብር መነሻ ዋጋ የደብረ ሓዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም የG+4 ገቢ ማስገኛ ሕንጻ እየተገነባ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

አክለውም በማኅበረ ቅዱሳን የበደሌ የሥልጠናና ሁለገብ G+4 ሕንጻ በ170 ሚሊየን ብር የተጠና ዋጋ በሁለት ዙር በ1152 ካ.ሜ ላይ አርፎ እየተተገበረ ነው ያሉት ኢንጂነሯ በምሥራቅ ወለጋ ሀገረ ስብከት የተገነባው የአብነት ተማሪዎች የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

የግብዓቶች ዋጋ መናር፣የትራንስፖርት ወጪ መጨመርና የሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አለመረጋጋት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን ምክትል ኃላፊዋ አንስተው አማራጮችን በመጠቀም ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡
እየተሠሩ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ የሙያዊና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገ ሲሆን በዚህም ረገድ በውጭ ሀገራት የሚገኙ ማእከላት እንዲሁም በውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ምእመናን ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ በመሆኑ ምስጋናቸውን ዳይሬክተሩ አቅርበዋል፡፡
ዘወረደ
እንኳን አደረሳችሁ!

ዘወረደ ማለት "ከላይ የመጣ፣ የወረደ'' ማለት ነው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን "ዘወረደ እምላዕሉ አይሁድ ሰቀሉ ወሚመ ኢያእመሩ እግዚአ ኩሉ ዘየሐዩ፤ አዳምን ለማዳን ከሰማይ የወረደውን አምላክ አይሁድ ሰቀሉት፤ የሰማይ ሥልጣን ያለው የሁሉ ጌታ እንደሆነም ምንም አላወቁም" እያለች በሰንበት ዋዜማ ዜማውን መሐትው (መግቢያ) አድርጋ የሳምንቱን ዜማ በማስተጋባት የጌታችንን ከሰማይ መውረድ ታመሠጥርበታለች፤ ታመሰግንበታለች። (ጾመ ድጓ፥ ዘዘወረደ ዋዜማ)
ይህን ሳምንት በልዕልና በዘለዓለማዊ ቅድስና እና በማትመረመር ጥበብ ራሱን ሰውሮ የሚኖር አምላክ በገሃድ ለሰው ልጅ የተገለጠበትን፣ ዘለዓለማዊ አምላክ ሰውን ከተደበቀበት ለመፈለግ ብሎ ''ኦ አዳም አይቴ ሀሎከ- አዳም ሆይ ወዴት ነህ" እያለ በማያልቅ የፍቅር ድምፅ ፍለጋ ወደ ዱር (ወደ ዓለም) የገባበትን ሳምንት የምንዘክርበት ነው። አምላካችን እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ምን ያህል በበዛ ፍቅሩ እንደሚፈልገው፣ ከፍ ላለ ዓላማውም እንዳጨው ያሳየበት፣ ከሁሉም ደግሞ በሕሊና ሊታሰብ የማይችለውን የሰማይ አኗኗሩን ትቶ በሚታይ የአዳም ሥጋ የተገለጠበት፣ መጋረጃው እሳት፣ ዙፋኑ እሳት፣ ልብሱ እሳት የሆነው አምላክ በሚበሰብስ ሥጋ የተገለጠበት፣ በጨርቅ፣ ያንን የሚያስደነግጥ መለኮታዊ ክብሩን ስለ ሰው ልጅ መዳን ተጨንቆ በሕፃን አምሳል ተገልጦ በበረት የተገኘበትን ሳምንት እናስብበታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ የእግዚአብሔር ልጅ ለሰው ልጅ ድኅነት ሲል መወለዱን እንዲህ በማለት ይገልጠዋል፡፡ "ለዚሁ ዓላማ (ለሰው ልጅ ድኅነት) የማይበሰብስ፣ የማይሞት አካል ያለው የእግዚአብሔር ልጅ ወደዚህ ዓለም ገባ" (On the Incarnation: Saint Athanasius page 6)
ዘወረደ ከዚህ ትርጉም ባለፈ የአዳም ሳምንት ተብሎ ይጠራል። አዳምን ከጠፋበት ሊፈልግ፣ ከወደቀበት ሊያነሣ፣ ከገባበት ሊያወጣ የትንቢቱ ጊዜ በደረሰ ሰዓት ከብላቴናይቱ ድንግል ተወልዶ ተስፋ አዳም ተፈጽሞበታልና። “ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤" እንዲል ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ (ገላ.፬:፬)።
ሠለስቱ ምዕት በጸሎተ ሃይማኖት "ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ" (ጸሎተ ሃይማኖት) እንዲሉ በሥጋ የአዳምን ዘር ለማዳን ሰው ሆኖ ለአዳም የገባውን ኪዳን ፈጸመ። የሥጋ ዘመዳችንም ሆነ። (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ)
ሌላኛው ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባል ይታወቃል። ይህም በ፮፻፲፬ ዓ.ም የፋርስ ንጉሥ ኪርዮስ ኢየሩሳሌምን ወርሮ፣ አብያተ ክርስቲያናትን ዘርፎ እና መዝብሮ ክርስቲያኖችን ማርኮ ንግሥት ዕሌኒ ካሠራችው ቤተ መቅደስ የክርስቶስን መስቀል ዲያቆናትን አሸክሞ በምርኮ ወሰደ። ከምርኮ ያመለጡ ክርስቲያኖች ወደ ሮሙ ንጉሥ ከ፲፬ ዓመት በኋላ በ፮፻፳፰ ዓ.ም ለንጉሥ ሕርቃል ጩኹታቸውን ያሰማሉ፤ እርሱም በፋርሱ ንጉሥ በኪርዮስ ላይ ድል አግኝቶ መስቀሉን መለሰላቸው። በሕገ ቤተ ክርስቲያን ‹‹ሰው የገደለ ዘመኑን ሁሉ ይጹም›› የሚል በሐዋርያት ስለተደነገገ የንጉሡን ዕድሜ ተከፋፍለው አንድ ሳምንት ደርሶባቸው ስለ ንጉሡ ጾመወለታል፤ በዚህም የእርሱ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ይህ ሳምንት ጾመ ሕርቃል በመባል ይጠራል። እኛም ይህንን ዋቢ አድርገን እንጾማለን። (ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርኀ መጋቢት ፲)
ዘወረደ ከአርብዓው ዕለት የሚካተት ባይሆንም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ አድርጋ ከአርብዓው ዕለታት ጋር ደምራ እንድንጾም ሕግ ሠርታለታች። እኛም እንደ ፈቃድ ሳይሆን እንደ ትእዛዝ ተቀብለን እንጾማለን።

ቅዳሴ፡- ቅዳሴ እግዚእ

"ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ፡፡" ወንጌል (ዮሐ.፫፥፲-፩፬)
ምስባክ ዘነግህ:- (መዝ.፪፥፲፩) "ዘበእንቲአነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት፤ ተሰብአ ወተሰገወ እመንፈስ ቅዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል፤ ስለ እኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ"
ምስባክ ዘቅዳሴ:- (መዝ.፪፥፲፩) “ተቀነዩ ለእግዚአብሔር፤ ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ፤ አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር፤ ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ፤ በረዓድም ደስ ይበላችሁ፤ ጌታ እንዳይቆጣ ተግሣጹንም ተቀበሉ፡፡”
መልእክታት:-
ሠራኢ ዲያቆን ዕብ.፲፫፥፲፯
ንፍቅ ዲያቆን ያዕ. ፬፥፮- ፍጻሜው
ንፍቅ ካህን የሐዋ. ፳፭፥፲፫-ፍጻሜ

ስብሐት ለእግዚአብሔር፤ አሜን!
He Who Comes Down
The First Sabbath of “The Great Lent” according to our Holy Church’s teachings is known as “Zewerede” to mean “He Who Comes Down.” Saint Jared’s hymn for this holiday states about The Holy Son Coming from the heavens as He vowed to the first mankind Adam and for the salvation of all human race. (Book of Tsome Deguua)
This week is the commemoration of the Lord Who Came Down from His mysterious in highness and everlasting holiness and be revealed on this vain world, in search of man by His unconditional love.
Saint Athanasius said, “For this purpose, then, the incorporeal and incorruptible and immaterial Word of God entered our world. In one sense, indeed, He was not far from it before, for no part of creation had ever been without Him Who, while ever abiding in union with the Father, yet fills all things that are. But now He entered the world in a new way, stooping to our level in His love and Self-revealing to us. He saw the reasonable race, the race of men that, like Himself, expressed the Father's Mind, wasting out of existence, and death reigning over all in corruption. He saw that corruption held us all the closer, because it was the penalty for the Transgression; He saw, too, how unthinkable it would be for the law to be repealed before it was fulfilled. He saw how unseemly it was that the very things of which He Himself was the Artificer should be disappearing. He saw how the surpassing wickedness of men was mounting up against them; He saw also their universal liability to death. All this He saw and, pitying our race, moved with compassion for our limitation, unable to endure that death should have the mastery, rather than that His creatures should perish and the work of His Father for us men come to nought, He took to Himself a body, a human body even as our own. Nor did He will merely to become embodied or merely to appear; had that been so, He could have revealed His divine majesty in some other and better way. No, He took our body, and not only so, but He took it directly from a spotless, stainless virgin, without the agency of human father--a pure body, untainted by intercourse with man. He, the Mighty One, the Artificer of all, Himself prepared this body in the virgin as a temple for Himself, and took it for His very own, as the instrument through which He was known and in which He dwelt. Thus, taking a body like our own, because all our bodies were liable to the corruption of death, He surrendered His body to death instead of all, and offered it to the Father. This He did out of sheer love for us, so that in His death all might die, and the law of death thereby be abolished because, having fulfilled in His body that for which it was appointed, it was thereafter voided of its power for men. This He did that He might turn again to incorruption men who had turned back to corruption, and make them alive through death by the appropriation of His body and by the grace of His resurrection. Thus He would make death to disappear from them as utterly as straw from fire.” (On the Incarnation: Saint Athanasius page 6)
The first Sabbath “Zewerede” is also known as “Adam’s Week.” The Lord and Savior Jesus Christ Came Down and Be Born from the Virgin Saint Mary, to search for Adam, raise him from his failure; take him out from hell and for the fulfillment of the prophecy. The Apostle Paul said, “But when the fullness of the time had come, God sent forth His Son, born of a woman, born under the law.” (Galatians 4:4)
This week is also known as “Hercules’s fast.” The naming is related with the finding of the Holy Cross that the Lord was crucified on. The King regained back the cross from the theft committed by King of Persia, Cyrus. Then, the people pronounced it to the King demanding justice. The King brought back the Cross onwards a battle with the Persian King. But after his triumph on the war, he faced another trial. The rule of Church on killing stated that “a person who killed shall fast his entire life.” Therefore, the people fasted the fasting King Hercules’s was order to fast by distributing the age of the King amongst themselves. In the commemoration of him, the first week is known as “The Fast of Hercules” and all Christians fast it. (Book of Ethiopian Synaxarium Megabit 10)
Though Zewerede is not included amongst the forty days our Lord fasted, the Church made order and included it amongst The Great Lent. We then fast it as an order but not by owns will.
May God’s mercy be upon us throughout this fast; Amen!
የቅጥር ማስታወቂያ
2025/02/25 03:56:33
Back to Top
HTML Embed Code: