tgoop.com/mahitot_zetewahido/212
Last Update:
#ሃይማኖት_ምንድነው_?
#ሃይማኖት፦ የሚለው ቃል "ሃይመነ" ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመን ፣ መታመን ፣ አማኝነት፣ አመኔታ ማለት ነው /ሮሜ 10:9/ #ሃይማኖት ፦ ፍጡርና ፈጣሪ የሚገናኙበት ረቂቅ መንገድ ነው /ኤር 6:16/ #ሃይማኖት ፦ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች በመገለጡ የተሰጠ አምላካዊ ስጦታ ነው / ይሁዳ 1:3/ #ሃይማኖት፦ ተስፋ ለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው /ዕብ 11:1/ #ሃይማኖት ፦ ማመን፣መታመን፣ ተስፋ ማድረግ ፣ አለመጠራጠር ፣ እውነትን መናገር ፣ ያዩትንና የሰሙትን ያመኑትን በማያምኑት ፊት መመስከር ነው /ሮሜ 8:2/ #ሃይማኖት ፦ አንዲት ናት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለው ግንኙነት አንድ ነውና /ኤፌ 4:5/ #ሃይማኖት ፦ ምንጩና ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው ስለዚህ የሰው ልጆች ከእውቀት ማነስ ፣ ከፍርሀትና ከድንጋጤ ያመጡት አይደለም /ይሁዳ 1:3/ የክርስትና ሃይማኖት እግዚአብሔር ወልድ ሁለት ልደታት እንዳሉት ማመን ነው #1ኛ.ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ መወለዱ /መዝ 109:3/ #2ኛ.ድኀረ ዓለም ያለ አባት ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ፣ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ #በተዋህዶ መወለዱን ማመን /ማቴ 1:25/ እግዚአብሔር ወደ ሰው ያደረገው የማዳን ጉዞ (ፍኖተ እግዚአብሔር) ሃይማኖት ይባላል /ዘፍ 3:1 ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መማር ይገባል እንዳሉ 318 ሊቃውንት ፤ #ሃይማኖት መሰረት ናት ምግባር ግድግዳና ጣሪያ ናቸውና እንዳለ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅፅሩ መሰረቱ ያልፀና ቤት ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ አያድንም የቀና ሃይማኖት የሌለው ምግባርም ከፀብአ አጋንንት ከስጋዊ ጠላት ከገሃነመ እሳት አያድንም በጎ ምግባር የሌው ሃይማኖት ነፍስ የተለየው በድን ማለት ነው /ያዕ 2:22/ #ሃይማኖት ለትሑታን ዕውቀትን ስለምትገልጥ ፣ ከዕውቀትም በላይ ስለሆነች በመጽሐፍ ቅዱስ ጥበብ ተብላ ተጠርታለች /ምሳ9:17/ #ሃይማኖት እባቡን ለመርገጥ ፣ ጊንጡን ለመጨበጥ ፣ መርዝን ለመጨለጥ ፣ ዲያቢሎስን ድል ለመንሳት፣አጋንንትን ለመግዛት፣ ተራራን ለማፍለስ ኃይልና ስልጣን ትሰጣለች ። /ማር 16:16/ በአጠቃላይ ሃይማኖት የነገረ መለኮትን ትምህርት ፡ የአምልኮን ሥርዓት ፣ ከእምነትም የተነሳ የአማኒውን ተጋድሎ ያጠቃልላል።
Comment @yitbarek1921
💚 @mahitot_zetewahido 💚
💛 @mahitot_zetewahido 💛
❤ ️@mahitot_zetewahido ❤️
BY ማኅቶት ዘተዋህዶ
Share with your friend now:
tgoop.com/mahitot_zetewahido/212