tgoop.com/markonalfikru/10
Last Update:
📜 መንፈሳዊ ግጥም📜
🛑 እውነት አለቀሰች🛑
▱▱▱▱▱▱▱▱
ልብ ያለህ አስተውል፥ ጆሮ ያለህ ስማ
እግርህ እንዳይገባ፥ ከክህደት ከተማ።
የያዝከውን አጽና ፥ ልብህ አይጨነቅ
ለጥያቄህ መልስም ፥ ሊቃውንትን ጠይቅ።
ለእውነት የቆመ፥ ሃይማኖቱን የሚያውቅ
ንባብ ትርጓሜን ፥ ጠንቅቆ የሚዘልቅ
ተናገር ዩሐንስ ፥ አንተ ልሳነ ወርቅ።
ቄርሎስን ጠይቀው ፥ የተዋህዶን ምስጢር
የክርስቶስ ነገር ፥ እንዴት እንደነበር።
ከብሉይ ከሐዲስ ፥ በማቀነባበር
እንዳመሰጠረው ፥ በብዙ ምስክር።
ነቢዩ ኢሳያስ ፥ ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ
መዝሙረኛው ዳዊት ፥ ሐዋርያው ሉቃስ
አባ ዝክረ ማርያም ፥ ወአባ ጴጥሮስ
የስነ ዘፍጥረት ሊቅ ፥ ኤጲፋኒዮስ
ዝም አትበል ተናገር ፥ ቅዱስ ሳዊሮስ
በሥጋው ማክበሩን ፥ አምላክ ክርስቶስ።
ጊዮርጊስ ተናገር ፥ አንተ የጥዋት ጮራ
ክርስቶስ መሲሕም ፥ ተብሎ እንደሚጠራ።
ወልድ ቅብዕ በማለት፥ ክህደት አስተማሩ
የሥግው ቃል ነገር ፥ መች ገባቸው ዳሩ
የተዋሕዶ ምስጢር ፥ ሳይገባቸው ቅሉ
ሃይማኖት ከምስጢር ፥ ይደባልቃሉ።
ክርስቶስ በሥጋ ፥ እንደሞተ ሲያውቁ
በሥጋስ መክበሩን፥ እንዴት አላወቁ
ሊቃውንት እያሉ ፥ ለምን አይጠይቁ
በተዋሕዶ ከበረ ፥ ብለው ሲናገሩ
ለዚህ ብሂላቸው ፥ የታል ምስክሩ።
ግብርን በማፋለስ....
አንድ ገጽ ካለው ፥ ከሰባልዮስ
አንድነትን ትቶ ....
ሁለት አካል ካለው ፥ ከእርጉም ንስጥሮስ
መንፈስ ቅዱስ፥ ሕጸፅ ካለው ከመቅዶንዮስ
ወልድ ፍጡር ካለው፥ ከእርጉም ከአርዮስ
የዚህ ክህደቱ ፥ በምንም አያንስ።
ፈላጊዋ ጠፍቶ፥ እውነት አለቀሰች
ግብራቸው ተቃርኖ፥ ሀሰት ጥላት ሄደች።
ዳሩ ግን ወገኔ ፥ ይህ ክህደት ነውና
ቀኑ ሳይመሽብህ ፥ መንገድህን አቅና
እውነትን ከፈለክ ፥ ታገኛለህና
እረፍት ስላላት ፥ የህይወት ጎዳና
የያዝከውን ይዘህ ፥ በሃይማኖት ጽና።
🙏ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
🙏 ወለወላዲቱ ድንግል 🙏
🙏ወለመስቀሉ ክቡር🙏
ይቆየን ○○○○○○○○
BY 📜መንፈሳዊ ግጥሞች📜MENFESAWI GITMOCH
Share with your friend now:
tgoop.com/markonalfikru/10