tgoop.com/markonalfikru/546
Last Update:
እስከ መቼ?
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
በዱሩ በዋሻው ጤዛ እየላሱ
ድንጋይ ተንተርሰው ጥሬ እየቀመሱ
መከራ መስቀሉን ከፊታቸው ስለው
ስለ አንቺ ተጥለው
እንደ መጻተኛ በሰው ዘንድ ተቆጥረው
ፂማቸው ተነጭተው ቁልቁሊት ተሰቅለው
በሰይፍ እና በእሳት እጅግ ተፈትነው
ቆዳቸው ተገፎ
ጥርሳቸው ረግፎ
ዝንቱ ውእቱ ፍሬ ሃይማኖት
ብለው መቀበሉን መልእክት
አርቀው በማየት ብራናውን ፍቀው
በደም የከተቡሽ ተዋህዶ አንቺን ነው
ቢያነፈንፉ ጉባኤ ካለባት
ታሪክሽን ቢያጠፉ ግራኝ እና ጉድት
ያደረሱት ጥፋት የታሪክ ጠባሳ
በልጆችሽ ልብ ውስጥ ቢልም አልረሳ
ማነው የጨከነ ቆርጦ የተነሳ
እንባሽን ሊያብስ ሀዘንሽን ሊያስረሳ
ብራናውን ዳምጠው
ቀለሙን በጥብጠው
ለኛ ያቆዩልን ተጨንቀው ተጠብበው
ይህን ሁሉ ድካም ትውልድ ካልገባው
በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱ
ምን ጥቅም ይሰጣል ... መባል ለትውልዱ
እምነትን ከምግባር ባንድ ካላስኬዱ
አንተ ግን
ቀና ቢሉ ላፍታ በደም የከተቧት
ሰለ እርሷ መስክረው ያለፉ ሰማዕታት
አደራ በሊታ እጅግ አሳፋሪ
ሆነህ ሲያገኙህ ወጭቱን ሰባሪ
ዋ
ምን ትመልስ ይሆን ከፊታቸው ቆመህ
የአባትህን ርስት አደራውን በልተህ
ልጄ! ባክህ አስተውል
የወላድ መካን አትሁን ደጁም አይዘጋ
ፍጠን አሁኑኑ አትሮንሱንም ዘርጋ
አንተ የናቡቴ ልጅ ክፈልላት ዋጋ
ናቡቴን አስበው ያን የተገፋው ሰው
በኤልዛቤል ክፋት ደሙ የፈሰሰው
ለርስቱ ነበረ ሞትን የቀመሰው
በተፈለፈለው ዋሻ ስር
ስለሷ ያነቡ በፍቅር
ቅዱሳን ናቸው ምስክር
ሀጢያት አይብቀል በቤቷ
እንዳይበላሽ ውበቷ
@markonalfikru
@markonalfikru
@markonalfikru
BY 📜መንፈሳዊ ግጥሞች📜MENFESAWI GITMOCH
Share with your friend now:
tgoop.com/markonalfikru/546