tgoop.com/markonalfikru/773
Last Update:
አንቺዬ
በጣቶችሽ እርሳስ የተሳሉ ሁሉ፤
ያመሰግኑሻል ብጽዒት እያሉ፤
እኮ .......ሁሉም በየግሉ፣
ሠዓሊያን በሥዕሉ ፣
ዜመኛው በዜማ፣
የቅኝቱን ጉልበት......
ከነፍሱ ሲያስማማ፣
ገጣሚያን በግጥሙ፣
ገድልሽን ሲነድፉ ብዕር እያደሙ፣
ቅናት ይሉት ስሜት ተጋባብኝ እና፣
ለቅኔ ለመዝሙር ቆምኩኝ ለምስጋና፤
እንኳን ለእናትዬ እንኳን ለማር--- ያሜ፣
መራራ አንደበቴን
ለቀየረችልኝ በጣፈጠ ቃና፥
እንኳንስ በብዕሬ፥
በእስትንፋሴ ዜማ፥
ሲያንስባት ነው እንጂ
ቆዳዬ ተገፎ ቢከትብ በደሜ፤
አስታውሰዋለሁ!.....
ነፍሴ ተጨንቃ መድረሻ ጠፍቷት፣
ስጋዬ ገልፍቶ ፥
....ድድር ኃጢያቴ ነፍሴን ሲያስጉዛት፣
እናቴ ድንግል ባልኩበት ማግስት፣
ከዕድፌ ነፃሁ፥
ዳግም ሰው ኾንኩኝ ፥
ስጋ ለበስኹ አግቸ ምህረት፣
ሳመሰግናት!.....
በመውደድ ዜማ ስቀኝ ከፊቷ ባትረካ ነፍሴ፣
እንደ ቅዱስ..... ኤፍሬም .....በጣመ ውዳሴ፣
እንደ ቅዱስ ያሬድ ዜማዬ ባይጥምም፣
ማርያምን! ....,ማርያምን......
ስለ እናትነትሽ ዝም ብዬ አላልፍም።
ማርያምን!......
ስምሽ ጣፋጭ ነው ከወይን የላቀ፣
አንቺን የተጠጋ፣አንቺን የያዘ ሰው
እንደምን ፀደቀ?!
አሁን እናትዬን ስሟን ስነሳሳው
ጠላት ይቃጠላል፣
ምድር አስጨንቃው
ሠማይ ልጥቀስ ይላል፣
እንኳን ማረር መክሰል
ቡን ቢል አልተውም
አንቺን ከማመስገን!...፣
መች ፍርኃት አውቅና
ሺህ ወጥመድ ቢጠመድ ፣
በአንቺ ታምኛለኹ አልቀርም ከመንገድ ፤
"ማርያም" ይላል ትውልድ ሁሉ፤
"አዛኝ" ይላል ተገፍቶ እንደ መውደቅ ብለው ቀና ያሉ፣
"አማላጅ" ይላል ከአምላኩ የታረቀ፣
ስራሽ ድንቅ ሆኖ በትውልዱ አንደበት ስምሽ [እ]ረቀቀ፤
እኔም ተነሳኹ፣
በድልብ ኃጢያት:-
የደነደነ ሽንፈት የጣለው ልቤን [እ]ረታኹ፣
ይኼው ተነሳኹ!.......
ለድንግልናሽ:-
ለንጽህናሽ፣
ለቅድስናሽ:-
ለፈጣን ምልጃሽ :-
ቅኝቴን ልቀኝ ላዜም ለፍቅርሽ፣
ከደጅሽ መጣኹ፤
ካንቺ እርቄ!....
አልቦ ህይወቴ እያስጨነቀኝ፣
እልፍኘ ኦና ኖኅ እየራቀኝ፣
የእምባዬ ግለት ፊቴን ሲፈጀኝ፣
የነፍሴ አምላክ" እነኋት " ብሎ እናቱን ሰጠኝ፤
¶ ሚስጥረ Yenatua Lij
BY 📜መንፈሳዊ ግጥሞች📜MENFESAWI GITMOCH
Share with your friend now:
tgoop.com/markonalfikru/773