tgoop.com/marroodiinayaas/8552
Last Update:
🚩 #ኢትዮጵያ ወይም #ኢምፓዬሯ..⁉️
📌ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ምን ያልተፈጸም ፤ ምንስ ያልተደረገ ግፍ አለ ?
📌እጅግ በጣም ሚያስደነግጠው እንዲሁም ፍጹም ከሰውነት ተራ እየተወጣ መሆኑን የሚያሳየው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ልክ ጀግንነት ፣ በጎ ተግባር፣ ፍቅርን ለትውልድ የሚያስተላልፉ ይመስል ግፍና ጭካኔያቸውን በቪድዮ ማስረጃ እራሳቸው ቀርጸው ለትውልድ እያስቀመጡ መሆናቸው ነው።
በእርግጥም እንዲህ እየቀረጹ ማስቀመጣቸው ህዝቡን ለሚፈልጉት ዓላማ ለማነሳሳትና እርስ በርስ ለማባላት፣ ህዝቡን ወደ ግጭት ለማስገባት ሊሆን ይችላል።
በጥላቻ የሚፈጽሙት የግፍ ተግባራቸው አላረካ ብሏቸው ፣ " እዩልን ምን ያህል አውሬ እንደሆንን " የሚለውን ለማሳየትም ይሆናል።
🚨በሀገራችን ፦ 🗣
♨️ሰው ከነህይወቱ ሲቃጠል
♨️ በድንጋይ ተወግሮ ሲገደል
♨️በጅምላ በጥይት ተደብድቦ ወደ ገደል ሲከተት
♨️ አስክሬን ሲጎተት
♨️ አስክሬን አደባባይ ላይ ሲጣል
♨️ ተዘቅዝቆ ሲሰቀል
♨️በስለት ተቀልቶ ሲገደል
♨️ የጥይት በረዶ ሲዘንብበት ... ኧረ ብዙ ብዙ በቪድዮ ተቀርጾ አይተናል።
ይኸው ዛሬ የሰው ልጅ ልክ እንደ ዶሮ " በስመአብ " ተብሎ ሲታረድ በቁማችን አየን።
ይህ ጭካኔ በማስረጃ በቪድዮ ተቀርጾ የወጣ ነው ለመሆኑ ስንት በቪድዮ ያልተቀረጸ ፣ በየአካባቢው የተፈጸመ ግፍ ይኖር ይሆን ?
እነዚህ ግፍ ፈጻሚ ሰዎች ሰይጣናዊ ስራቸውን በቪድዮ ቀርጸው ማስቀረታቸው በቤተሰብ ፣ በህዝብ ላይ የማይረሳ ቂም፣ ቁርሾና ቁስል ለማኖር ይመስላል።
የትም ይሁን ማንኛውም የግፍ ድርጊት ሲፈጸም ግን የሚቀድመው ድርጊቱን ከልብ አዝኖ ማውገዝ ነው። ፍትህ ተጠያቂነት እንዲሰፍን መጠየቅ ፤ ለፍትህ መታገል ነው።
ልክ ሰው በሞተ ቁጥር ያለ አንዳች ሀዘን እና መከፋት ወደ ፖለቲካ ንትርክ መግባትና የሰው ደም ፈሶ እንዲቀር ለማድረግ መሯሯጥ የግፍ ግፍ ነው።
ከዚህ ቀደም ብዙ ታዝበናል።
ሰው በግፍ ይገደላል ከዛም ሰዎች በየማህበራዊ ሚዲያ ይመጡና " የኔ ወገን ሰው አይገድልም፤ ፍጹም ነው ፣ ፃድቅ ነው ፣ እንዲህ እንዲያደርግ ተፈጥሮው አይፈቅድለትም " እያሉ ድርጊቱ ያራክሱታል።
ሌላው ወገን ይመጣና በሞተው ንጹህ ሰው ደም ፖለቲካ ይሰራል። በጅምላ ጥላቻውን ይተፋል። በዚህ መንገድ የስንት ሰው ደም ፈሶ ቀረ ?
ላለፉት ዓመታት ሰው በግፍ ይገደላል ከዛ የቀናት የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ ሆኖ ያልፋል፤ ይረሳል። ከዛ ሌላ ግፍ ሌላ ግድያ ይፈጸማል።
አንዳንዱ እውነት ከልቡ አዝኖ ፤ አንዳንዱ ደግሞ የይስሙላ ያዘነ ይመስል ሸፋፍኖ በማህበራዊ ሚዲያው ይጽፋል ፤ ይለፍፋል። ከሰዓታት በኃላ ሁሉም ረስቶት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ ህይወቱ ይመለሳል። ማህበራዊ ሚዲያ ሲገባ ትዝ ሲለው ለቀናት ስሜቱን ይፅፍ ይሆናል።
እስከ ህይወት ፍጻሜ ድረስ በሀዘን የሚቃጠሉትና ልጃቸውን የማይረሱት እናት አባት፣ ወንድም ፣ እህት ቤተሰብ፣ ዘመዶች ናቸው።
በተለይ እናት እና አባት ሲያለቅሱ ነው የሚኖሩት።
ይህ አዙሪት መቆም አለበት። ደመ በፈሰሰ ቁጥር ቁርሾ ቂም እየተወለደ እንጂ ፍቅር አንድነት አይመጣም።
ልጆቹን የተነጠቀ ቤተሰብና አካባቢ እንደሌላው የማህበራዊ ሚዲያ አርበኛ የአንድ ቀን ሀዘን አድርጎ አያልፈውም። የተፈጸመበትን ግፍና በደል መቼም አይረሳውም ! ቂም በውስጡ ያድራል። ይህ በሀገር ህዝብ ትስስር ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ከባድ ነው።
ከምንም በላይ ለተጎዱ ወገኖች ፍትህ በማስፈን ፣ ሌላ የአንድ ሰው ደም እንዳይፈስ በማድረግ አዙሪቱን ማቆም ካልተቻለ የከፋ ነገር መምጣቱ አይቀርም።
እዚህች ምድር ላይ ነገ ሳይሆን ዛሬ የሰው ልጅ ደም መፍሰስ እንዲቆም ማድረግ ይገባል።
ፍትህ ሊሰፍን ፤ ተጠያቂነት ሊረጋገጥ ይገባል።
ታጣቂም ሆነ አልሆነ ፤ የአካባቢው ፣ የክልሉ የመንግሥት አካል ሆነ አልሆነ ሁሉም በየድርሻው በየደረጃው ሊጠየቅ ይገባል።
እጅግ በጣም አስገራሚው ነገር በምንም አይነት መንገድና ሁኔታ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ስራው ሊሆን የሚገባው እና ችግርም ሲፈጠር ለህዝብ የማሳወቅ ኃላፊነት ያለበት መንግሥት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ከማህበራዊ ሚዲያው ጩኸት በኃላ ለመናገር ሲወጣ መታየቱ ነው።
ለመሆኑ የሚፈጸመውን የሚሰማው ከህዝብ ጋር በሚዲያ ነው ? ነዋሪው በሚዲያ ባይጮህ ላያወግዝ ነው ?
ቆይ ልክ እንደማንኛውም ሌላ አካል " አወገዝኩ " ብቻ ነው የሚባለው ወይስ ስለተፈጸመ ግፍ በዝርዝር አጣርቶ ለህዝብ ወጥቶ መረጃ መስጠት ነው የሚገባው ? የመንግሥት ስራ ድርሻው ምንድነው ? ለስንቱ ፍትህ ለተነፈገ እያነባ ላለ ወገን ፍትህ ሰጠ ? ተጠያቂነትን አሰፈነ ? በደል የደረሰባቸውን ካሰ ? ዳግም ደም እንዳይፈስ ተከላከል ? እኚህ ሁሉ ጥያቄዎች መልስ ይሻሉ።
ህዝብ በሀገሩ የሚሆነውን ሁሉ ያያል ፣ ይታዘባል፣ ይገመግማል ፣ ነጥብም ይይዛል።
በምንም አይነት ሁኔታ የሰው ደም አይፈስስ ፤ ደም ሲፈስ ቂምና ቁርሾ እንጂ ፍቅርና አንድነት አይወለድም።
- Finfinne Times
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!💎
____
📌www.tgoop.com/Fastsinfo99
📌www.tgoop.com/Fastmereja5
🌴 🌴 🌴
BY OROMIA TIMES™°°°!!
Share with your friend now:
tgoop.com/marroodiinayaas/8552