Forwarded from ኢትዮጵያ ታበጽዕ እደዊሃ ሐበ እግዚአብሔር
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
ከኤርቱ ሞጆ ፍኖተ ሰላም ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን
አስቀድመን ለመላው ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን ይህ ታላቅ በዓል በሀገራችን በታላቅ ድምቀትና ክብር እንደሚከበር ይታወቃል።
በዚህም በ2017 ዓ.ም ደብራችን የኤሩቱ ሞጆ ፍ/ሰላም ቅ/ክርስቶስ ሠምራና ቅ/አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን የአሁኑ የጥምቀት በዓል ተረኛ አዘጋጅ ነው። ቤተክርስቲያናችን ደግሞ በሸገር ሲቲ መልሶ ማልማት ምክንያት ሕዝቡ ከአካባቢው በመነሳቱ መንፈሳዊውም ሆነ ማኅበራዊ አገልግሎቱን ለማስቀጠል በጣም ችግር ውስጥ ስለሆነች በአሁን ሰዓት ገቢዋም በጣም አስተኛ ስለሆነ ለበዓሉ የሚያስፈልግ ለአገልግሎቱ፣ ለመንገድ ጽዳት፣ ለውሃ አቅርቦት የሚሆን ምንም ነገር የለንም ስለዚህም እናንት የእግዚአብሔር ልጆች ቤተክርስቲያናችን በዓሉን ከዋዜማው ጀምሮ በአግባቡና በድምቀት አክብራ ታሳልፍ ዘንድ የቻላችሁትን አድርጋችሁ በረከትን ታገኙ ዘንድ ቤተክርስቲያናችን ስም እንጠይቃለን፤
በዚህ በተቸገርንበት ወቅት በቀሩት ጥቂት ቀናት የምትችሉ ቤተክርስቲያኗ ድረስ በመገኘት በመጎብኘት ማገዝ የምትችሉ ሲሆን ሁላችሁም ባላችሁበትም ከታች ባለው አካውንት የአቅማችሁን እንድታግዙን እየተማጸንን በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
የደብሩ አካውንት
1000189712336
ለማንኛውም መረጃ እና ጥያቄ በዚህ ስልክ ቁጥር ያነጋግሩን፤👇
0911058924
ገቢ የምታደርጉትን ገንዘብ ደረሰኙን ፎቶ አንስተው ከላይ ባለው ስልክ ቁጥር በቴሌግራም/ በኢሞ እንዲልኩልን እየጠየቅን ለምታደርጉልን ድጋፍ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልን እያልን ቤተክርስቲያኗ በጸሎት እንደምታስባችሁ እናሳስባለን።
share ለ20 ለ20 ሰው

"አቤቱ አንተን ደስ ከማያሰኝ ሐሳብ እንለይ ዘንድ መለየቱን ስጠን....አቤቱ የእውቀት ዓይኖችን ስጠን፤ ዘውትር አንተን ያዩ ዘንድ ፤ጆሮቻችንም ያንተን ብቻ ቃል ይሰሙ ዘንድ።"
ቅዳሴ እግዚእ
ቅዳሴ እግዚእ
Telegram
መዓዛ ሃይማኖት በጎ አድራጎትና ጉዞ ማህበር
"ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡"
"በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘውድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ"
መጽሐፈ ሰዓታት
የፌስቡክ ፔጃችን www.fb.me/meazhaimanot ይቀላቀሉን

"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡
ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡
ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

እናመሰግናለን You Tube ላይ 1160 subscribe ስለገባን
አሁንም subscribe አድርጉ 🏃♂️5000
👇👇👇
https://m.youtube.com/channel/UCKGh-U7U7pnvFUIEGXPOnNw
ቻሌንጁን ተቀላቀሉ

YouTube
መዓዛ ሃይማኖት
ዉድስት አንቲ በአፈ ነብያት ወስብሕት በሐዋርያት አክሊለ በረከቱ ለያዕቆብ ወትምክህተ ቤቱ ለእስራኤል፡፡
በነቢያት በሐዋርያት አንደበት የተመሰገንሽ የያዕቆብ የበረከቱ ዘዉድ የእስራኤል ወገን መመኪያ አንቺ ነሽ
https://www.tgoop.com/meazahaymanot

የጥር ፲፯ የጥያቄ እና መልስ ውጤት
1. ኢትበሉኬ ለጌሠም:እስመ ጌሠምሰ = 12
2. ሰ/ሸዋNewflawor =10
3. Elisye12lij = 5
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን በቤቱ ያቆይልን
1. ኢትበሉኬ ለጌሠም:እስመ ጌሠምሰ = 12
2. ሰ/ሸዋNewflawor =10
3. Elisye12lij = 5
ቃለ ሕይወትን ያሰማልን በቤቱ ያቆይልን
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አሜን"። ❤
❤ #ጥር ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጃንደረባ_በ34 ዓ.ም #ሐዋርያው_ቅዱስ_ፊሊጶስ_ላተጠመቀ ለመጀመሪያው ለአፍሪካ ሐዋርያ ለሆነ ለሐዋርያች #ለቅዱስ_አቤላክ (ባኮስ) ከሞት ለተሰወረበት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
✝ ✝ ✝
❤ #የመጀመሪያው_የአፍሪካ_ሐዋርያ_ቅዱስ_አቤላክ (ባኮስ)፡- ይኽም ጃንደረባ በመጀመሪያ የኢትዮጵያ ንግሥት የሆነችው የህንደኬ የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊና አዛዥ የነበረ ነው፡፡ ከአባቱ እብነ መላክ ከእናቱ ስሂነ ሕይወት ታኅሣሥ29 ቀን ተወለደ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ ለበዓለ ፋሲካ በቤተ መቅደስ ይሰግዱ እንደነበረው ሁሉ ይኽም ጃንደረባ ከ4ሺህ ማይልስ በላይ ተጉዞ ኢየሩሳሌምን ተሳልሞ በመለስ ላይ ነበረ፡፡
❤ ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ የነቢዩ ኢሳይያስን መጽሐፍ በተለይም ስለ ጌታችን መከራ መስቀል በዝርዝር የሚናገረውን ክፍል 53ኛውን ምዕራፍ ያነብ ነበር ነገር ግን ጃንደረባው ስለማን እንደሚናገር አልገባውም ነበር፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር በአካባቢው ወንጌልን ይሰብክ የነበረውን ሐዋርያውን ቅዱስ ፊሊጶስን ላከለት፡፡ እርሱም ጃንደረባው ያነበው የነበረውን መጽሐፍ ተረጎመለት፣ የከበረች ወንጌልን ሰበከለት፣ በመጨረሻም አጠመቀው፡፡ ሐዋርያው ባጠመቀውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በጃንደረባው ላይ ወረደ፡፡ ሐዋ 8፡26-40፡፡
❤ ይህን ለእኛ ለኢትዮጵያውን እጅግ የሚያኮራን ታሪካችን ነው፡፡ ዛሬ በእጃችን ላይ በመገኘው መጽሐፍ ውስጥ ባይኖርም በቆዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥራዞች ላይ ግን ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ጃንደረባውን ባጠመቀውም ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያው ጃንደረባ ላይ እንደወረደ ተጽፏል፡፡ (v 39.cord.alexand. in bible reg. angl-aliqu plures codd.mss)
ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ጃንደረባውን ያጠመቀበት ወንዝ "ቤተ ሳሮን" በተባለችውና እስከዛሬም ድረስ ከኢየሩሳሌም20 ማይልስ ርቀት በምትገኘው መንደር በኬብሮን መካከል ባለው ኮረብታ ሥር የሚመነጭ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ጸሐፊ የሆነው ሊቁ ቅዱስ ጀሮም ጃንደረባውን "የኢትዮጵያውያን ሐዋርያ" በማለት ይጠራዋል፡፡ በሰፊው ለኢትዮጵያውያን ወንጌልን የሰበከ እርሱ ነውና፡፡
❤ ጌታችን የመረጣቸው የከበሩ ሐዋርያት እንኳን ወንጌልን በዓለም ለመስበክ ገና ከኢየሩሳሌም ባልወጡበት ወቅት በ34ዓ.ም ነው። ቅድስት አገራችን ኢትዮጵያ በክርስቶስ አምና ወንጌልን የተቀበለችው፡፡ በምድሪቱም ላይ ወንጌል መነገር የጀመረው ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ሐዋርያው ባኮስ (አቤላክ) ከኢየሩሳሌም ወንጌልን ተምሮና ተጠምቆ ወደ አክሱም እንደተመለሰ በመጀመሪያ ያጠመቀ ንግሥቲቷ ሕንደኬን ነው፡፡ ከእርሷም በኋላ መኳንንቱና መሳፍንቱ ሁሉ አምነው በባኮ እጅ ተጠመቁ ይኸውም በ34 ዓ.ም ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ባኮስ እስከ ኑብያ ድረስ ሄዶ ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቋል፡፡ በዚህም ጊዜ ወንጌላዊው ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በባኮስ እየተሰጠ የነበረውን የወንጌል ብርሃን የበለጠ እንዲበራ አድርጓል፡፡ ከጃንደረባውም ጋር ሆነው በብዙ ቦታዎች አብረው ወንጌልን ሰብከው አምልኮተ ጣዖትን አጥፍተዋል፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ባኮስ ወደ የመን በመሄድ በዚያም ክርስትናን በማስተማር ብዙዎችን አሳምኖ ካጠመቀ በኋላ ወደ ፐርሺያ ከዚያም ወደ ሕንድ፡ በመሄድ ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ፈጽሟል፡፡ በመጨረሻም ጥንት ታፕሮባና (taprobana)፡ ዛሬ ሲሎን በምትባለው ደሴት ወንጌልን በማስተማር ላይ እያለ በሰማዕትነት እንዳረፈ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ (lives of the most eminent fathers of the church, page 87) በሌላም በኩል ሐዋርያው ባኮስ (አቤላክ) ከመጠመቁ በፊት 35ዓመት ከተጠመቀ በኋላ ደግሞ 41 ዓመት ኖሮ በኢየሩሳሌምም 3ዓመት ተቀምጦ ወንጌልን ዞሮ ካስተማረ በኋላ በመጨረሻ በ79 ዓመቱ ጥር 18 ቀን በሰሜን ተራራዎች ላይ ቅዱስ ያሬድ በተሰወረበት ቦታ እንደተሰወረ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋ ጽፈዋል፡፡ ምንጭ፦መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳት በዓላት።

መልካም 2⃣3⃣4⃣5⃣7⃣8⃣9⃣🔟 እነዚህ ያልተመረጡ ቁጥሮች ናቸው መንፈሳዊ ጥያቄዎች መሳተፍ የምትፈልጉ @meazahaymanot1 ይግቡ
መንፈሳዊ ጥያቄዎች 26 people answered
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና አስተምህሮ በጠበቀ መልኩ ቃለ እግዚአብሔርን ለምዕመናን ማዳረስ
🖊 12 questions · ⏱ 2 min · 🔀 all
External sharing link:
www.tgoop.com/QuizBot?start=67pBRLhh

Quiz Directory
መንፈሳዊ ጥያቄዎች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና አስተምህሮ በጠበቀ መልኩ ቃለ እግዚአብሔርን ለምዕመናን ማዳረስ / 12 questions
ጥር 21 የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት
“ ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ”
ጥር 21 በዓለ አስተርእዮ (የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት)
እንኳን ለዚህች ታላቅ በዓሏ አደረሰን፡፡
ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡
ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
... የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ“አስተርእዮ ማርያም” ተብሏል፡፡ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡ ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ (ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ) ነገረቻቸው፡፡ ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን፡፡ ሁላችንም ባለንበት ይህ ታላቅ በዓሏን እያሰብን ጸልየን የበረከቷ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን፡፡ መልካም በዓል !!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!
የነገረ ቅዱሳን ክፍል ፩ ጥያቄ
፩. ነገረ ቅዱሳን ማለት ምን ማለት ነው?
፪.የቅዱሳን ማለት ምን ማለት ነው?
፫. ቅዱሳን እግዚአብሔር የክብሩ መገለጫዎችን ዘርዝሩ?
እውነት ውይም ወሸት
፩. ነገረ ቅዱሳን ነገረ እግዚአብሔር ማለት ይቻላል?
፪. ነገረ ቅዱሳን ማለት ትምህርተ ተዋህዶ ማለት ነው?
፫. ቅዱሳን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫዎች ናቸው?
መልሱን ➡️ @wengelyohannes አድርሱን
የነገረ ቅዱሳን ክፍል ፩ ጥያቄ
፩. ነገረ ቅዱሳን ማለት ምን ማለት ነው?
፪.የቅዱሳን ማለት ምን ማለት ነው?
፫. ቅዱሳን እግዚአብሔር የክብሩ መገለጫዎችን ዘርዝሩ?
እውነት ውይም ወሸት
፩. ነገረ ቅዱሳን ነገረ እግዚአብሔር ማለት ይቻላል?
፪. ነገረ ቅዱሳን ማለት ትምህርተ ተዋህዶ ማለት ነው?
፫. ቅዱሳን የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫዎች ናቸው?
መልሱን ➡️ @wengelyohannes አድርሱን
"ልጆቼ! የሚያሳፍር ነገር፣ የስንፍና ንግግር ወይም ዋዛ ፈዛዛ የማይገቡ ናቸውና በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድ ከቶ አይሰሙ፡፡ እስኪ ንገሩኝ! የዋዛ ፈዛዛ ንግግር ጥቅሙ ምንድን ነው? እስኪ ንገሩኝ፤ አንድ ጫማ ሰፊ፣ ጫማ እየሰፋ በአንድ ጊዜ ሌላ ሥራ መሥራት ይችላልን? አይችልም፡፡ ከዋዛ ፈዛዛ የሚያሳፍር ንግግር ይወለዳል፡፡ የአሁኑ ጊዜ ደግሞ ለእኛ ለክርስቲያኖች ዋዛ ፈዛዛ የምንናገርበት ሳይኾን የንስሐችን ጊዜ ነው፡፡ እስኪ አሁንም ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! አንድ ቦክስ የሚጫወት ሰው ውድድሩን ችላ ብሎ ዋዛ ፈዛዛን ይናገራልን? እንዲህ የሚያደርግ ከኾነስ በተጋጣሚው በቀላሉ የሚሸነፍ አይደለምን? ታዲያ ባለጋራችን ዲያብሎስ‘ኮ የሚውጠውን ፈልጐ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙርያችን ቁሟል፡፡ ጥርሱን እያንቀጫቀጨብን ነው፡፡ እኛን የሚጥልበት ወጥመድ በማዘጋጀት ላይ ነው፡፡ የደኅንነታችን መንገድ ላይ እሳት እየተነፈሰ ነው፡፡ ታዲያ ዲያብሎስ እንዲህ እኛን ለመጣል ሲተጋ እኛ ዋዛ ፈዛዛን፣ የሚያሳፍር ነገርን፣ የስንፍናንም ንግግር ስንናገር ቁጭ ልንል ይገባናልን?
የምወዳችሁ ልጆቼ! ጊዜው የምንተኛበት ጊዜ አይደለም፡፡ የተጋድሎ ጊዜ ነው እንጂ፡፡ ቅዱሳን ጊዜያቸውን እንደ ምን እንደሚያሳልፉት ማወቅ ትፈልጋላችሁን? እስኪ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስን አብረን እንስማው፤ እንዲህ ያለውን፡- “ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ”፤ … “በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችኋለሁ…”፡፡ … “የሚደክም ማን ነው፤ እኔ አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፤ እኔም አልናደድምን?”፤ “… በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን”፡፡ ታዲያ እነ ቅዱስ ጳውሎስ ጊዜያቸውን እንዲህ ካሳለፉ፣ ኃጥአን የምንኾን እኛ ጊዜያችንን በሳቅና ስላቅ ልናጠፋ ይገባናልን? በክርስቶስ ፍቅር የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በንግግሬ አትማረሩ፡፡
ጊዜው የተጋድሎ ጊዜ ነው፤ ታዲያ ስለ ምንድን ነው የዘፋኞችን መሣርያ አንሥተን ከዓለም ጋር የምንዘፍነው? በጦር ግንባር ያለ ወታደር ከጠላት ሊመጣ የሚችለውን ጥቃት ለመከላከል ከመዘጋጀት ይልቅ ጊዜውን በዋዛ ፈዛዛ ያጠፋልን? አያጠፋም፡፡ ታዲያ እኛም‘ኮ የክርስቶስ በጎ ወታደሮች ነን፡፡ ..."

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡