Telegram Web
''እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡
ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''

(ቅዱስ ኤፍሬም)

እኛስ እውነተኛ ጿሚ መባል ይገባን ይሆን?
ድንግል ሆይ

ልጅሽ የጎሰቆለውን ብላቴና እንደተቀበለ እኔንም ደግሞ ይቀበለኝ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ልጅሽ ቸር ይቅር ባይ ርኅሩኅ ነውና፡፡ (ሉቃስ ፲፭፣ ፲፬-፲፮)

የተራበ ሆድ ለምግብ እንዲቸኩል ክርስቶስ ደግሞ ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡

ይህንንም ማለቴ ለጥምቀት ልጆች በፍጹም ንስሐ በተቃጠለም የእግዚአብሔር ፍቅር ለተመለሱት ነው ላልተመለሱት ግን ይቅርታ የላቸውም፡፡

ድንግል ሆይ

የልጅሽ የሥጋው መታረጃ የደሙ መቅጃ ወደሚሆን መጋረጃ ውስጥ ያስገባኝ ዘንድ እታመናለሁ

ድንግል ሆይ

የምስሢር ጠረጴዛ ወደተዘጋጀበት በላዩም የመለኮት ማዕድ የሚሆን የሰማይ እንጀራ በተሠራበት ስፍራ ያስቀምጠኝ ዘንድ እታመናለሁ በጌታችን፡፡

የምሥጢሩ ጽዋዕ ከመለኮት ትስብእት ጎን የመነጨው አምላካዊ ወይን ወደተመላበት ያስቀምጠኝ ዘንድ እታመናለሁ፡፡

ድንግል ሆይ

ነፍስና ሥጋን ባንድነት የሚፈውሰውን ቅዱስ ምሥጢር ያሳትፈኝ ዘንድ እታመናለሁ ድንግል ሆይ መለኮታዊውን ቁርባን ሥጋው ደሙን ለመቀበል እንዲያበቃኝ ደጅ እጸናለሁ፡፡

በተቀበልሁትም ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ ለነፍሴና ለሥጋዬ መድኃኒት ይሁነኝ እንጂ

ድንግል ሆይ

እድል ፈንታዬ ጽዋ ተርታዬም የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ ዕንቋችሁንም በዕሪያዎች ፊት አታኑሩ ከተባለባቸው ጋር አይሁን

ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ ሞት አያገኘውም ቢሞትም ይድናል ለዘለዓለምም ይኖራል ተብሎ ከተነገረላቸው ጋራ እንዲሆን ደጅ እጸናለሁ፡፡ (ማቴ ፯፣ ፮)


የእመብርሃን በረከት አይለየን ❣️
ጸሎት ሰውን ወደ እግዚአብሔር መንግስት የምታደርስ ቀጭኗ ጎዳና ናት፡፡ ከኃጢአት በመራቅ የሚቀርብ ጸሎት ፍጹም የሆነ ሥራን ይሰራል፡፡ ከባልንጀራህ ጋር በጠብ እየኖርክ በእግዚአብሔር ስም ለጸሎት የምትቆም ከሆነ እርሱን እንደመሳደብ ይቆጠርብሃል፡፡ ህሊናህም ከጸሎትህ አንዳች ፍሬ እንደማታገኝ ያስታውቅሃል፡፡ በጸሎት ተመስጠህ ልብህን ወደ እግዚአብሔር አንሳ፡፡

አጠገብህ ስሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠኸው ቁጥር ነው፡፡ ጥላቻ በልቦናህ ነግሶ ከሆነ የዳቢሎስ እርዳታ እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡

የተንኮል ቃልን አትናገር፤ ለባልንጀራህ ጉድጓድ አትቆፍር፤ ወደ አመንዝራም ሴት አትመልከት የፊቷም ደምግባት አያጥምድህ፡፡ በእርሷ መረብ እንዳትጠመድ ከአንደበቷ ከሚፈልቁት ጣፋጭ ቃሎች ተከልከል፡፡ ከእርሷ ፈጽሞ ሽሽ፡፡

በሰዎች ውድቀት አትደሰት፡፡ በደለኛ እንዳትሆን ጠላትህ ክፉ ሲደርስበት አይተህ ደስ አይበልህ፡፡ ጠላትህ በኃጢአት ተሰነካክሎ ብታይ ስለ እርሱ እዘንለት አልቅስለት፡፡ እጆችህን ለሥራ አትጋቸው፤ ከንቱ ንግግር አትውደድ ለነፍስና ለሥጋ ብሩህነት በሥራ መጠመድን ውደድ፡፡
ፍቅርን የምትወድ ሁን

“በፍቅር ተመላለሱ” (ኤፌ. 512)

ይህ የሁሉም ነገር መሠረት ነው! ፍቅር ባለበት ቦታ ቁጣ፣ ጩኸት፣ ስድብ የለም፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ተወግደዋል፡፡ ጳውሎስ አሳዳጅ ሳለ በእግዚአብሔር ፍቅር ድኗል፡፡ አንተስ ስለምን የእግዚአብሔር ልጅ ሆንክ? ምክንያቱም ይቅር ስለተባልክ ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ዋጋው የማይተመን ስጦታ ተቀብለህ፣ እንዴት ለሌሎች አላካፍልም ትላለህ?

ይህን አስብ! ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወንጀሎች ተሸክመህ በእስር ቤት ተጣልክ፤ እናም አንድ ስው ከዚህ አውጥቶ ቤተ መንግሥት አስገባህ። ወይም ሌላ ምሳሌ ለመጠቀም፣ በጠና ታምመህ ለሞት ተቃርበህ ነበርና አንድ ሰው በመድኃኒት አዳነህ። ያን ሰው ከማንም በላይ ከፍ አድርገህ አትመለከተውም? የመድኃኒቱን ስም ስትሰማ እንኳ ደስ አይልህም? ከሥጋ ስቃይ ያዳነንን ከፍ አድርገን የምንወደው ከሆነ፣ ነፍሳችንን የሚያድኑትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ምን ያህል እንወዳቸው ይሆን?

ፍቅርን የምትወድ ሁን፤ የዳንከው የእግዚአብሔር ልጅ ባደረገልህ ፍቅር ነውና! ሌላውን የማዳን፣ የመርዳት እድል ካለህስ ይህን ተመሳሳይ መድኃኒት አትሰጠውምን? “ለሰዎች ኃጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤" እንደተባለው (ማቴ. 6፥14) በዚህ መንገድ አንዳችን የሌላኛችን አበርቺ፣ የሌላኛችን አመስጋኝ መሆናችን የተከበረ እና የለጋስ ልብ ምልክት ይሆንልናል።

ጳውሎስ በመቀጠል “ክርስቶስ ደግሞ እንደ ወደዳችሁ" ይለናል፡፡ እኛ ይቅር ማለት ያቃተን ወዳጆቻችንን ነው፡፡ ክርስቶስ ግን ጠላቶቹን ይቅር ብሏል፡፡ ከጌታችን የተቀበልነው ስጦታ ምንኛ ይበልጣል! ክርስቶስ እንደወደደን መውደድ ከፈለግን ለጠላቶቻችን እንኳን መልካም ማድረግ አለብን፡፡

ጳውሎስ “ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።" በማለት አክሎ ተናግሯል፡፡

ተመልከት… ስለሌሎች መከራ መቀበል ለጠላቶችም ቢሆን ጥሩ መዓዛ ያለው መባ ሲሆን፣ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው፡፡ ለሌሎች ብትሞት በእውነት መስዋእት ትሆናለህ፡፡ እግዚአብሔርን መምሰል ማለት ይህ ነው፡፡ እስከ መሥዋዕት መውደድ፣ በነጻ ይቅር ማለት፤ ክርስቶስ እንደ ተመላለሰ በፍቅር መመላለስ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 'ለነፍስህ ቤት ስራላት' ገጽ 44-45 በፍሉይ ዓለም የተተረጎመ)
የእውነተኛ ምጽዋት መለኪያ

የምጽዋት ብዛት የሚመዘነው በሚሰጠው ገንዘብ ቁጥር መጠን ሳይኾን ስጦታውን በሚሰጥ የልብ ስፋት ነው፡፡ አንዲት ድኻ ሴት ያላትን ጥቂት እንጀራ ምንም ከሌላት ከሌላ ሴት ጋር ተካፍላ የምትበላ ከኾነ፥ ወርቅን በሙዳዬ ምጽዋት ከሚጨምር ባለጸጋ ሰው ይልቅ እጅግ ትበልጣለች፡፡ ነገር ግን ምንም እንኳን ይህ እውነት እንደ ኾነ ብዙ ክርስቲያኖች ቢያውቁም፥ ምስጋና የሚሰጡት ወርቅ ለሰጠው ነው፡፡

አንድ ባለጸጋ ጠቀም ያለ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ቢሰጥ እጅግ ያመሰግኑታል፤ ካለው የሀብት ብዛት የተነሣ ያንን በመስጠቱ ምንም ባይጎድልበትም እንኳ፥ በሰዎች ዘንድ እጅግ ቸር እንደ ኾነ ተደርጎ ይንቆለጳጰሳል፡፡ ድኻው ጥቂት ገንዘብ ቢሰጥ ግን ሰዎች ስለ እርሱ ምንም ትንፍሽ አይሉም፡፡ ምናልባት ያቺ የሰጣት ገንዘብ’ኮ በኋላ እርስዋን በማጣቱ ምክንያት ተርቦ እንዲያድር ልታደርገው የምትችል ትኾን ይኾናል፤ ነገር ግን ይህን በማድረጉ የሚያመሰግነው አንድ ሰውስ እንኳ አይገኝም፡፡ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም ሳይጎድልበት የሰጠው ባለጸጋውን አመስግኖ ያለውን ኹሉ የሰጠውን ድኻ ሳያመሰግኑ ከሚቀሩ ከእነ ጭራሹ ምስጋና ባይኖር ይሻል ነበር፡፡

ስለዚህ እውነተኛ ምጽዋት የሚባለው የባለጸጋውም ይኹን የድኻው በአግባቡና በሥርዓቱ ልናውቀው ይገባናል፡፡ ማመስገን የሚገባንም ከዚያ በኋላ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር የምስጋናችን ስጦታም ሰዎች ከልባቸው ከሚሰጡት ገንዘብ ብዛት አንጻር ሊኾን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"አምስቱ የንስሐ መንገዶች" መጽሐፍ
በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።

1 Have mercy upon me, O God, according to thy lovingkindness: according unto the multitude of thy tender mercies blot out my transgressions.

2 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ

2 Wash me throughly from mine iniquity, and cleanse me from my sin.

3 እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። 4 አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።

3 For I acknowledge my transgressions: and my sin is ever before me.
4 Against thee, thee only, have I sinned, and done this evil in thy sight: that thou mightest be justified when thou speakest, and be clear when thou judgest.

5 እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።

5 Behold, I was shapen in iniquity; and in sin did my mother conceive me.

6 እነሆ፥ እውነትን ወደድህ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።

6 Behold, thou desirest truth in the inward parts: and in the hidden part thou shalt make me to know wisdom.

7 በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።

7 Purge me with hyssop, and I shall be clean: wash me, and I shall be whiter than snow.

8 ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥ የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።

8 Make me to hear joy and gladness; that the bones which thou hast broken may rejoice.

9 ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።

9 Hide thy face from my sins, and blot out all mine iniquities.

10 አቤቱ፥ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፥ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ።

10 Create in me a clean heart, O God; and renew a right spirit within me.

11 ከፊትህ አትጣለኝ፥ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ።

11 Cast me not away from thy presence; and take not thy holy spirit from me.

12 የማዳንህን ደስታ ስጠኝ፥ በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።

12 Restore unto me the joy of thy salvation; and uphold me with thy free spirit.

13 ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።

13 Then will I teach transgressors thy ways; and sinners shall be converted unto thee.

14 የመድኃኒቴ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ከደም አድነኝ፥ አንደበቴም በአንተ ጽድቅ ትደሰታለች።

14 Deliver me from bloodguiltiness, O God, thou God of my salvation: and my tongue shall sing aloud of thy righteousness.

15 አቤቱ፥ ከንፈሮቼን ክፈት፥ አፌም ምስጋናህን ያወራል።

15 O Lord, open thou my lips; and my mouth shall shew forth thy praise.

16 መሥዋዕትን ብትወድድስ በሰጠሁህ ነበር የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም።

16 For thou desirest not sacrifice; else would I give it: thou delightest not in burnt offering.

17 የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም።

17 The sacrifices of God are a broken spirit: a broken and a contrite heart, O God, thou wilt not despise.

18 አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ።

18 Do good in thy good pleasure unto Zion: build thou the walls of Jerusalem.

19 የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ።

19 Then shalt thou be pleased with the sacrifices of righteousness, with burnt offering and whole burnt offering: then shall they offer bullocks upon thine altar
ሥራህን ሥራ

ሌሎች ሰዎችን ከማያድን ክርስቲያን በላይ የከፋ ምንም የለም፡፡ አንተ ሰው! ድኻ ነኝ የምትለኝ ለምንድን ነው? ኹለት ዲናር የጣለችዋ ሴት ትፋረድባሃለች፡፡ ከምናምንቴ ቤተሰብ እንደ ተወለድክ የምትነግረኝስ ለምንድን ነው? ሐዋርያትም ምናምንቴዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ታላላቅ መኾን ተችሏቸዋል፡፡ አለመማርህን ሰበብ አድርገህ አትንገረኝ፤ ሐዋርያትም ያልተማሩ ነበሩና፡፡

ባሪያ ብትኾንም እንኳ፣ ስደተኛ ብትኾንም እንኳ ሥራህን መሥራት ይቻልሃል፤ ሌሎችን መርዳት ይቻልሃል፤ ሰዎችን ማዳን ይቻልሃል፥ አናሲሞስም እንደ አንተ ዓይነት ሰው ነበርና (ፊልሞ.1፥10-11)፡፡ ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ምን ወዳለ ማዕረግ ከፍ እንዳደረገውና ምን ብሎ እንደ ጠራው አድምጥ፡- “በእስራቴ ስለ ወለድሁት፡፡”

ወዳጄ ሆይ! እኔ እንኳን ሕመምተኛ ነኝ ብለህ አትንገረኝ፤ ጢሞቴዎስም እንደ አንተ ዘወትር ይታመም ነበር፡፡

ፍሬ የማያፈሩ ዛፎች እንደ ምን ብርቱዎችና ተወዳጆች፣ ግዙፋንና ሐመልማላውያን እንደዚሁም ረጃጅም እንደ ኾኑ አላየህምን? የፍራፍሬ ቦታ ቢኖረን ግን ፍሬ የሚያፈሩት ሮማንንና ወይራን እንተክላለን እንጂ እነዚህ ፍሬ የማይሰጡንን ዛፎች አንተክልም፡፡ ምክንያቱም እንዲሁ ለዓይን ማረፊያ ለማየት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ጥቅም የላቸውምና፡፡

የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚመለከቱ፣ ሌሎች ሰዎችንም የማይረዱ ክርስቲያኖችም እንደ እነዚህ ዛፎች ናቸው፡፡ እንዲያውም ከእነዚህ ዛፎችም የባሱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የሚቆረጡት ለእሳተ ገሃነም ነው፡፡ ዛፎቹ ግን ቢያንስ ቢያንስ ጠረጴዛም ወንበርም ለመሥራት ይጠቅማሉ፡፡ ለቤት መሥሪያ ይጠቅማሉ፡፡ አጥር ቅጥር ኾነው ያገለግላሉ፡፡

እነዚያ አምስቱ ደናግል እንደዚህ ነበሩ (ማቴ.25፥1)፡፡ ርግጥ ነው ንጽህናቸውን የጠበቁ ነበሩ፡፡ ለሚያያቸው ኹሉ ግሩም የኾነ ጠባይ የነበራቸው ነበሩ፡፡ ሥርዓት ያላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ኹሉ ግን ምንም አልጠቀማቸውም፡፡ ወደ እሳተ ገሃነም ከመጣ’ል አልታደጋቸውም፤ ዘይት የተባለው ምጽዋት አልነበራቸው’ማ! ክርስቶስን በነዳያን አማካኝነት የማይመግቡትም ዕጣ ፈንታቸው ጽዋ ተርታቸው ይኸው ነው የሰነፎቹ ደናግል ዕጣ!

አንተ ሰው ልብ ብለህ አስተውል! እነዚህ ደናግል በግል ኃጢአታቸው አልተነቀፉም፡፡ በዝሙት ወይም በሐሰት ምስክርነት አልተወቀሱም፡፡ በፍጹም! ይልቁንም የተነቀፉትና የተወቀሱት ሌሎች ሰዎችን ባለመጥቀማቸው ነው፡፡

እንደዚህ ከኾነ ታዲያ ሰዎች ክርስቲያን ተብለው ሊጠሩ የሚችሉት በምን መመዘኛ ነው? እኮ በምን መስፈርት? አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ! በሊጥ ውስጥ የተጨመረ እርሾ ሊጡን እንዲቦካ ካላደረገው እንዲሁ እርሾ ተብሎ መጠራት ብቻውን ምን ይረባዋል? ዳግመኛም ወደ እርሱ የቀረቡትን ሰዎች መዓዛው ካልሸተታቸውና ቤቱን ካላወደው በቀር ከርቤ በከርቤነቱ ምን በቁዔት አለው?

ሌሎች ሰዎችን መርዳት አይቻለኝም ብለህ አትንገረኝ፡፡ እንዲያውም ልንገርህ፤ አንተም ስማኝ፡- አንተ በእውነት ክርስቲያን ከኾንክ ሌሎች ሰዎችን አለመርዳት የማይቻል ነው፡፡ ዕጣን መዓዛ እንዲኖረው፣ እርሾም ሊጥን እንዲያቦካ ተፈጥሮው እንደ ኾነ ኹሉ፥ አንድ ክርስቲያንም በስም ክርስቲያን ከመባል አልፎ በእውነት ያለ ሐሰት ክርስቲያን ከኾነ ሌሎች ሰዎችን መርዳት መቻሉ፣ ሌሎችን የሚጠቅም ሥራ መሥራቱ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

ስለዚህ አይኾንልኝም፤ አይቻለኝም በማለት እግዚአብሔርን አታማርር፡፡ ፀሐይ ብርሃኗን በእኔ ላይ ማብራት አይቻላትም ካልክ ፀሐይን እየሰደብካት ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ክርስቲያንም ሌሎች ሰዎችን ሊጠቅማቸው አይችልም የምትል ከኾነ እግዚአብሔርን እየሰደብክ [ሎቱ ስብሐትና] ሐሰተኛም እያደረግኸው ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ክርስቲያን ሌሎች ሰዎችን ካለመርዳትና ካለመጥቀም ይልቅ ፀሐይ ሙቀትና ብርሃን ባትሰጥ ይቀላል፡፡ እንደዚህ ከሚኾን ብርሃን ወደ ጨለማ መቀየር ይቀላል፡፡

እናስ? እና’ማ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡ የማይቻለው መርዳት አለመቻል ነውና፡፡ አይኾንልኝም እያልክ በከንቱ እግዚአብሔርን አታማርር፡፡

ሕይወታችንን በአግባቡና በሥርዓቱ የምንመራ ከኾነ እነዚህን ነገሮች ኹሉ በቀላሉ ማድረግ ይቻለናል፤ እነዚህ ነገሮች ሊደረጉ ግድ ነው፡፡ በመቅረዝ ላይ የተቀመጠ ሻማ ብርሃኑን መደበቅ እንደማይቻለው ኹሉ ክርስቲያንም የእውነት ክርስቲያን ከኾነ ብርሃኑም መሸሸግ አይቻለውም፡፡ ስለዚህ እውነተኞች ክርስቲያኖች ከኾንን ሌሎች ሰዎችን መርዳት መጥቀምም ችላ አንበል፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - የክርስቲያን መከራና ሌሎች ገጽ 72-75)
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው....

ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡

"ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡

አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡

(ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ)
Forwarded from ማኅቶት Wave
#ደብረ_ዘይት
(የዐቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት)

የዐቢይ ጾም የአምስተኛው ሳምንት ደብረ ዘይት ይባላል፡፡ ጌታ በደብረ ዘይት የዳግም ምጽአቱን ነገር ማስተማሩ ይነገርበታል፡፡ ደብረዘይት የስሙ ትርጓሜ የዘይት ተራራ ማለት ነው ስያሜ የተሰጠው በቦታው ብዙ ወይራ ተክል ይበቅልበት ስለ ነበር ነው፡፡
እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው ንገረን ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድን ነው?›› አሉት (ማቴ. 24፥3፣  ዘካ. 14፥5 ፤ ሐዋ. 1፥11 ፤ 1ኛ ተሰ. 4፥16 ፤ ራዕ. 22፥7)

#አመጣጡስ_እንዴት_ነው?

ጌታ ይህንን ዓለም ለማሳለፍ ለሁሉም እንደ ሥራው ለመክፈል በግርማ መለኮቱ በክበብ ትስብዕቱ ይመጣል፡፡ ጊዜው ዘመነ ዮሐንስ ወርሃ መጋቢት ዕለት እሑድ መንፈቀ ሌሊት እንደሆነ ሊቃውንት ተናግረዋል፡፡ ምነው የሚያውቀው የለም ይባል የለምን? ቢሉ እውነት ነው የሚያውቀው የለም ብዙ የዮሐንስ ዘመን፤ ብዙ የመጋቢት ወር፤ ብዙ የእሑድ ዕለት አለና ለይቶ የሚያውቅ የለም፡፡ ሞት ለማን አይቀርምና ሁሉም ይሞታል፡፡ ዘፍ. 3፥19 በዕለተ ምጽአት ቅዱስ ገብርኤል ስምንቱን ነፋሳተ መዓት ከየመዛግብታቸው ያወጣቸዋል፡፡ ዛፏን ነቅለው ደንጊያውን ፈንቅለው ምድርን እንደ ብራና ይዳምጧታል፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መለኸት ይነፋል፡፡ 1ኛ መቃ. 9፥8 ቅዱስ እግዚአብሔር ዘያነቅሖሙ ለሙታን ሲል በዱር በገደል በባሕር በየብስ በመቃብር ውስጥ ያሉት በአውሬ ሆድ ውስጥ ያሉ ሁሉ ይሰበሰባሉ፡፡ በሁለተኛው ነጋሪት ሲመታ አጥንትና ሥጋ አንድ ሆነው ፍጹም በድን ይሆናሉ፡፡ ሦስተኛው ነጋሪቱን መቶ (ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ህያው ዘኢይመውት) ንቃሕ መዋቲ ዘትነውም ባለ ጊዜ መቃብር ክፈቱልኝ መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ደጉ ደጉነቱን ክፉውም ክፋቱን ይዞ ይነሳል፡፡    

ወንዱ የ30 ዓመት ሴቲቱ የ15 ዓመት ሆነው ጻድቃን ብርሃን ለብሰው ብርሃን ተጎናጽፈው ከፀሐይ 7 እጅ አብርተው ማቴ.13፥43 ኃጥአን ጨለማ ለብሰው ፍጹም ዲያቢሎስን መስለው ይነሳሉ፡፡ ጻድቃን ስለሠሩት መልካም ሥራ ኑ የአባቴ ቡሩካን ብሎ መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸዋል፡፡ ኃጥአንን ስለ ክፉ ሥራቸው (ከኔ ሂዱ) ገሃነም ይሰዳቸዋል፡፡ ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኃጥአን ግን ያዝናሉ፤ ዋይ ዋይ ይላሉ፤ ደረት ይደቃሉ እንባቸው ያፈሳሉ፡፡ የማይጠቅም ለቅሶ የማይጠቅም ሐዘን ሰቅለው የገደሉትም አይሁድ ክብሩን አይተው ላይጠቀሙ ይጸጸታሉ፡፡    

#ምልክቱስ_ምንድን_ነው? ብለው ጌታን ሲጠይቁ ‹‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፡- ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ፤ ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳል፤ ረሃብም ቸነፈርም መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሉአችሁማል፤ ስለ ስሜም በአሕዛብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡ በዳግም ምጽአቱ ጊዜ ከቅዱሳኑና ከሰማዕታቱ ጋር ለመቆም ያብቃን፡፡

#የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር_ከጾመ_ድጓ
እንዘ ይነብር እግዚእነ ውስተ ደብረ ዘይት ወይቤሎሙ ለአርዳኢሁ ዑቁኬ ኢያስሕቱክሙ ወንበሩ ድልዋኒክሙ ብዙኃን ይመጽኡ በስምየ እንዘ ይብሉ አነ ውእቱ ክርስቶስ ወዘአዝለፈ ትዕግሥቶ ውእቱ ይድኅን ወአመ ምጽአቱሰ....
(ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ለደቀ መዛሙርቱ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ ተዘጋጅታችሁም ኑሩ፤ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እስከ መጨረሻው የጸና እርሱ ይድናል፡፡....)

#የዕለቱ_ምንባባት
1ኛ ተሰሎንቄ 4÷13-ፍጻ፡-
ወንድሞቻችን ሆይ÷ ስለ ሞቱ ሰዎች÷ ተስፋ እንደሌላቸው ሰዎች እንዳታዝኑ ልታውቁ እንወዳለን፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞቶ እንደ ተነሣ ካመንን እንዲሁ እግዚአብሔር ሙታንን በኢየሱስ ያስነሣቸዋል ከእርሱም ጋር ያመጣቸዋል፡፡.....

2ኛ ጴጥ.3÷7-14፡-
አሁንም ሰማይና ምድር በዚያ ቃል ለእሳት ተዘጋጅተዋል፤ ኃጥኣን ሰዎች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀንም ተጠብቀዋል፡፡ነገር ግን ወንድሞቻችን ሆይ÷ ይህን አትርሱ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ አንዲት ቀን እንደ አንድ ሺህ ዓመት÷ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን ነውና፡፡.....

ሐዋ. 24÷1-21፡-
በአምስተኛውም ቀን ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ ከመምህራኑና ጠርጠሉስ ከሚባል አንድ ጠበቃ ጋር ወረደ፤ ጳውሎስንም በአገረ ገዢው ዘንድ ከሰሱት፡፡..... (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ምስባክ
መዝ. 49÷2
እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ፡፡
ትርጉም፦
እግዚአብሔር በግልጥ ይመጣል፡፡
አምላካችንም ዝም እይልም፤
እሳት በፊቱ ይነድዳል በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ፡፡

#የዕለቱ_ወንጌል
ማቴ. 24÷1-25፡-
ጌታችን ኢየሱስም ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው የቤተ መቅደሱን የሕንጻ አሠራር አሳዩት፡፡ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው÷ “ይህን ሁሉ ታያላችሁን? እውነት እላችኋለሁ፤ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም፡፡.....” (ተጨማሪ ያንብቡ)

#የዕለቱ_ቅዳሴ፦ ቅዳሴ አትናቴዎስ

ምንጭ፡-
(የማቴዎስ ወንጌል 24፥1 ትርጓሜ፣ መዝገበ ታሪክ ቁጥር 2፣ ግጻዌ)
ተግሣፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም

ሕይወትህን በአግባቡ መምራት ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ትሕትናን ተለማመድ፤ ያለ ትሕትና ተገቢውን ሕይወት መምራት አይቻልም፡፡ ሥራህን ሁሉ በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጀምር፡፡ ያን ጊዜ ፍሬዎችህ ወደ መንግሥተ ሰማያት ይደርሳሉ።

ሰው ከትሕትና ከራቀ ከትክክለኛው መንገድ ርቋል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የተወ ሰውን ርኵስ መንፈስ እንደ ሳውል ያስጨንቀዋል። የጠላት ወጥመድ በማር የተቀባ ነው፡፡ በማር ጣዕም የሚማረክ ሰው ሐዘንን ሁሉ በያዘ ወጥመድ ይያዛል። ትሕትናን ውደዱ፤ ያን ጊዜ ከሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አትወድቁም፡፡ በትሕትና ክንፍ በበረራችሁ ቁጥር ሁል ጊዜ ከጠላት ወጥመድ በላይ ትሆናላችሁ።

ግልፍተኝነት እንደ በሰበሰ ረጅም ዛፍ ነው፤ ቅርጫፎቹ ሁሉ በቀላሉ የሚሰበሩ ናቸው᎓᎓ አንድ ሰው በወጣባቸው ጊዜ ከወጣበት ከፍታ ወዲያውኑ ይወድቃል፡፡ በመልካም ሐሳብ ልቡናው የበራ ሰው ግን ምስጉን ነው፤ ክብሩም ታላቅና ዘላለማዊ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን ለመቆጣጠር እንጣር ያን ጊዜ ኃጢአታችንን እንረዳለን፡፡ ያን ጊዜም ሁል ጊዜ ራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን፤ እንደ እባብ በእብሪት መወጠርን እና ራሳችንን ከፍ ከፍ ከማድረግ እንቆጠባለን፡፡ እንግዲህ ራሳችንን ዝቅ ዝቅ ማድረግን እንውደድ፤ በንጹሕ ልቡና ሆነን ምናልባት የተሰጠንን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኃጢአት ከማቆሸሽ እንታደግ ይሆናል።

መልካም ጸሎት በሳግ እና በዕንባ የታጀበ ነው፤ በተለይ ደግሞ በምሥጢር የሚፈስ ዕንባ፣ በልቡናው ከፍታ ሆኖ የሚጸልይ ጌታውን በፊቱ ያያል። እኛ የምንኖረውና የምንሔደው በእርሱ ፈቃድ ነውና። ልቡናችሁ ከጠነከረ በጌታችን ፊት አልቅሱ እርሱ የዕውቀትን ብርሃን ይገልጥላችኋል፤ ወደ እርሱ የሚወስዳችሁ አዲስ ልብንም ይሰጣችኋል።

ንስሓ የገቡና ምሕረት የለመኑ ሰዎች ዕዳቸው ተሰረዘላቸው፤ ነገር ግን ለሠራኸው በደል ምሕረት ስትለምን ወንጀልን እና በደልን፤ በወንድምህም ላይ ቂም መያዝን መተው ይገባሃል። ፍቅር ሳይኖርህ ወደ እግዚአብሔር የምታደርገው ልመና ከተዘጋው በር ውጭ ይቀራል፡፡ የጸሎትን በር የሚከፍት ፍቅር ብቻ ነው፡፡

ወንድምህን ብታስቀይም እግዚአብሐርን ታሳዝናለህ፤ ካንተ ጋር ካለው ከወንድምህ ጋር ሰላምን ከፈጠርህ ግን በሰማይ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር ትታረቃለህ፡፡ ወንድምህን በፍቅር ብትቀበለው፣ በደሉንም ይቅር ካልከው እግዚአብሔርን ተቀበልክ፡፡

ስለዚህ በተናደዱ ሰዎች በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ታረቅ፤ እንግዲህ የተበሳጩትን በማስደሰት እግዚአብሔርን አስደስተው፣ በታሰሩት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን ጎብኘው፣ በተራቡት ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አብላው፤ በታረዙ ሰዎች በኩል እግዚአብሔርን አልብሰው፣ መንገደኛን በመቀበል እግዚአብሔርን በአልጋህ ላይ አስተኛው፤ እግሮቹንም እጠበው፣ በማዕድህም አስቀምጠው፣ እንጀራህንም ከእርሱ ጋር ተካፈል፤ ጽዋህንም ስጠው᎓᎓ እርሱ ታላቅ ፍቅሩን አሳይቶሃልና፤ እርሱ ስለ አንተ ብሎ ትበላው ዘንድ ሥጋውን ቆርሶልሃል፣ ትጠጣው ዘንድም ደሙን አፍስሷል።
    
እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም

እንደ ኃጢአት አዋራጅ የለም፡፡ ኃጢአትን የሚያደርግ ሰው በሐፍረት ካባ ብቻ የሚከናነብ አይደለም፤ አስቀድሞ ከነበረው ማስተዋልና ማገናዘብም ይዋረዳል እንጂ፡፡ ይህንንም ለመረዳት የአዳም የቀድሞ ክብሩን ማሰብ እንቸችላለን፡፡

ዳግመኛም ኃጢአትን ከሠራ በኋላ ያገኘውን ውርደት እንመልከተው፡፡ “በሰርክ ጊዜ ጌታ በገነት ውስጥ ድምፀ ሰናኮ ብእሲ እያሰማ ወደነርሱ ሲመጣ በሰሙ ጊዜ አዳምና ሔዋን ከእግዚአብሔር ፊት በገነት ዕንጨት መካከል ተሰወሩ” (ዘፍ.3፥8)፡፡ በዚህስ አዳም እንደ ምን ባለ ውርደት እንደ ተያዘ ታስተውላላችሁን? ምሉእ በኩለሄ ከኾነው፣ ፍጥረታትን ካለ መኖር ወደ መኖር ካመጣው፤ የተሰወረውን ኹሉ ከሚያውቀው፤ የሰውን ልቡና የፈጠረና በኀልዮ የሠሩትን ዐውቆ ከሚፈርደው (መዝ.33፥15)፤ ልብ ያሰበውን ኩላሊት ያጤሰውን መርምሮ ከሚያውቀው (መዝ.7፥9)፤ ልቡናችን ያሰበውን ከሚያውቀው (መዝ.44፥21) ከእግዚአብሔር ሊሸሸግ መውደዱ ከማወቅ ወደ ድንቁርና ከክብር ወደ ኃሣር እንደ ኼደ ያመለክታል፡፡

እኛም ኃጢአት ስንሠራ እንደዚህ ነው፡፡ መሸሸግ ባንችል እንኳን መሰወርን እንሻለን፡፡ ይህን ማድረጋችንም በኃጢአታችን ምክንያት ክብራችን እንደ ምን እንዳጣን፤ ሐፍረታችንን መሸፈንም እንደ ምን እንዳቃተን ያስረዳል፡፡ ነገር ግን ኃጢአትን የሠራ ሰው እንኳንስ በረኻ በኾነች በዚህች ምድር በገነት መካከልም መደበቅ አይችልም፡፡

("የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች" በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 81 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)
"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

#ቅዱስ_ፓሲዮስ
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ማኅቶት Wave
❤️የተወለዱበትን ወር በመምረጥ የሚደርሶትን መንፈሳዊ ቻናል በመቀላቀል ዕውቀቶችን ያግኙ
                   መልካም ዕድል!!!

https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk
https://www.tgoop.com/addlist/hVsJ5h6oKyk1NDRk
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures) via @dooxbot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእናንተው ደጋፍ የተጀመረው እዚህ ደርሷል አሁንም ድጋፋችሁ አይለየን 🙏🙏🙏
የቤተክርስቲያኑ የባንክ አካውንት
💰 👉 1000265718063 👈
ገላን ቅዱስ ሚካኤል

ሁላችንም 100 ብር ብናስገባ ብዙ ነገር መሸፈን እንችላለን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው እና ጥበቃው አይለየን 🙏🙏🙏

ለበለጠ መረጃ የደብሩ ስልክ

+251950008283

የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ
የአቅማችሁን ሼር በማድረግ ማገዝ ለሚችሉ እናድርስ

T.me/Elohe_picture
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱
ቻናሉ ላይ ምን እንዲጨመር ትፈልጋላችሁ???

ከዚህ ውጭ ካለ ኮሜንት ላይ ይፃፉልን ከፍተኛ ብልጫ ያለውን 1 / 2 ጭማሪ እናደርጋለን መልካም ዕለተ ሰንበት ።☦️ ማኅበራችንን መቀላቀል ለምትፈልጉ @Elohe_picture_robot ልታገኙን ትችላላችሁ
Anonymous Poll
34%
መዝሙር/ የመዝሙር ግጥሞች
28%
የእለቱ ማኅሌት እና ምስባክ
45%
ኮርስ
30%
ዕለታቱን የጠበቁ ግጥሞች
18%
የጉዞ አገልግሎት
41%
የአብነት ትምህርት ከቁጥር - አቋቋም
25%
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን ዜናዎች
46%
ኦርቶዶክሳዊ መጻህፍት በPDF
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ለማመን የሚከብዱ ታሪኮች አሉበት፡፡ እባብ ከሰው ጋር ሲነጋገር ፣ አህያ ጌታዋን ስትመክር ፣ ኤልያስ ዝናብን እንደ ቧንቧ ውኃ ሲከፍትና ሲዘጋ ፣ ቁራ አስተናጋጅ ሲሆን ፣ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ሲሳፈር ፣ ዮናስ በአሳ አንበሪ ሆድ ውስጥ ሲጸልይ ፣ የኤልሳዕ አጥንት ሙት ሲያስነሳ ፣ የኤልያስ ልብስ ባሕር ሲከፍል ፣ የሙሴ በትር እባብ ሲሆን ፣ ጌታ በምራቁ ዓይን ሲፈጥር ፣ የአራት ቀን ሬሳ በስም ተጠርቶ ሲወጣ ፣ የጴጥሮስ ጥላ ሲፈውስ ፣ የጳውሎስ ጨርቅ ሙት ሲያስነሣ ተጽፎ ታገኛለህ፡፡ ይሄንን ሁሉ እግዚአብሔር ሁሉን ማድረግ ይችላል ብለህ በእምነት ካልተቀበልከው በስተቀር እንዴት ታደርገዋለህ?

ሔዋን ከእባብ ጋር ተነጋገረች የሚለውን አምነህ አቡነ አረጋዊ በእባብ ተራራ ወጡ ሲባል ከቀለድህ ፣ ኤልያስን ቁራ መገበው ሲባል ተቀብለህ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቁራውን መገቡት ሲባል ከዘበትህ ፣ ዳንኤል ከአንበሶች ጋር አደረ ሲባል አምነህ አቡዬ አንበሶች ጋር ነበሩ ሲባል ካጣጣልክ መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ያለቀበት ቀን ለአንተ የዓለም ፍጻሜ መስሎሃል ማለት ነው::

አንድ አባት 'ዮናስን አሣ አንበሪ ዋጠው የሚለውን ታሪክ እንዴት ማመን ይቻላል?' ተብለው ሲጠየቁ 'የምናወራው ስለ እግዚአብሔር ከሆነ እንኳንስ ዓሣ አንበሪው ዮናስን ዋጠው ተብሎ ይቅርና ዮናስ ዓሣ አንበሪውን ዋጠው ቢባልም አምናለሁ' ብለዋል፡፡ 'አይ ይኼ እኮ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈ ነው' ካልከኝ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ ሲጠናቀቅ ሥራ አቁሞአል ማለት ነው? 'እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ' ሲል አብረን አልሰማነውም? (ማቴ. 28፡19)
2025/03/31 08:25:45
Back to Top
HTML Embed Code: