MEKBU Telegram 2975
ከዚህ ወዲያ ፍቅር!

በዕድሜ ማለዳ በአበባው የልጅነት ወቅት የሚታደሉት የለመለመ ዓለም ነው።ኣው! ለኔ የሩሔን ፍሰሃ የምቋደስበት ምድረገነቴ ነው።እድሉ ገጥሞት የቀረበ ያደገበት፣ወይም የተጠጋው ያውቀዋል።
የኻዲሞች መተናነስን ከሩቅ እያየን ስንገረም ያደግነበት ሐድራ።ትልቅ ሰዎች ታናናሾቻቸውን ሲካድሙ፣ወጣቶች ተቀምጠው አባቶች ቡና ሲቀዱ፣እሳት ሲያነዱ እያየን እንገረም ነበር።ኻዲሞች የሚለዩት ደግሞ ሻላቸውን ወገባቸው ላይ(ኣንዳንድ ቦታ ደግሞ ከትከሻቸው ላይ) ጠበቅ ኣርገው በማሰር ነው።ለካ ለኺድማው ታጥቂያለው ነው!።
እድሜ እውቅና ሳይገድበው ለታናሽ ማዘንን፣ታላቅን ማክበርን እዚህ በተግባር ይዳሰሳል።አባቶች ከነ ትጥቃቸው ወዲህ ወዲያ ሲሉ ይውላሉ።የኺድማ ተራቸው ሲደርስ ልባቸው በሐሴት የሚደልቅ መሆኑ እርምጃቸው፣ቅልጥፍናቸው፣
ከፊታቸው የሚነበብ ፈገግታ በጉልህ ያሳብቃል።

ልብን በአደብ አስተምሕሮና ማንነትን በዕመነት ቀርፆ፣ ኣስዉቦ ከሚያሰለጥን ስልጣኔ ኹሉ ቀዳሚ የማደርገው ሐድራን ነው።ምናልባትም ዛሬ ብዙዎች ላይ ከሚታየው የመልካም ስነ–ምግባር ነፀብራቅ ጀርባ የዚህኛው ዓለም ጠብታዎች ይኖራሉ።በወንድምነት ሰንሰለት የተጋመደ ሁሉ ሶፉን ደምድሞ
ይቀመጣል።ክብ መጅሊስ መሐል የተቀመጠች የእጣን ማጨሻ እቃ እንኳ በከበቧት አስሃቦች ነሻጣ የነሸጠች ትመስላለች።ሽቅብ የሚምዘገዘግ ጭሷን እያንቦገቦገች ቅጥሩን በመልካም መዓዛ ታውደዋለች።እዚህ ከተሰበሰበው ዙምራ ውስጥ አንድም የግል ፍላጎት ኣይንፀባረቅም።አንድም ሰው "እኔ"ብሎ ሚያብሰለስለው ሐጀት የለውም።
ሁሉም ሁሉንም ይረሳል።ግጣሙ ህብረት እኛነትን ገንብቶ፣እኔነትን ኣጥፍቷል።

ሩህ በኺያል ሲከንፍ ዛት ግራና ቀኝ ይወዘወዛል።ጃሊሶች ሁሉ ህብረት በኳለው ዜማ የሚቀኙት ሰላዋት ላይ ተጠምደዋል።ቀልባቸው ላይ የሚፈስስ ዘምዘም ይኖር ይመስል ፍካትን ተላብሰዋል።እዚህ መደማመጥ እንጂ ረብሻ አይታሰብም።ኢማሙ ቢቻ ወይም ኢማሙን ያስፈቀደ ሰው ብቻ! ለዚያውም ቀልብን የሚያርስ፣የሼኾችን ተርቲብ የጠበቀ ወግ ካለው ያወጋል።ሁሉም በጥሞና ያዳምጣል።

በየ ደውሩ ሶፉን ደምድሞ ከተቀመጠው ሐዲር ላይ የሚነበብ ፍቅር፣የቀልብ ሰላም አለ።የወንድምነት ጥምረቱ ባቀማመጥ ይጌጣል።እግሩን ኣጣጥፎ ከተቀመጠ ወንድም ኣጠገብ ጉልበቱ ከጉልበቱ ጋር የገጠመ ወንድም ከጎኑ አለ።በዚሁ ትስስር ሁሉም ኣንድ ይሆናል።በመሐል ደወሩን የሚመሩት ሼኽ እስካላዘዙ ድረስ ኸልዋው ላይ ፍፁም ሰላማዊ ፀጥታ ይሰፍናል።ምንም ኣይነት ኮሽታ ይጠፋል።ፀጥ ረጭ ያሉ ሓዲሮች ቀልባቸው ወደ ኻሊቅ የኮበለሉ ጅስሞች።
………

ልጅ ሆነን፣ በረንዳ ተቀምጠን ከሩቅ የምንቃኘው እኛ እንኳን ገብቶን ይሁን ሳይገባን ብቻ በንዝረት እንወዛወዝ ነበር።

ጥንፍ የጥንፍፍ ልጅ ባባቱም በናቱ፣
ውልውልም የለው መድሓኒትነቱ፣
እንዴት ናት ወላጁ እንዴት ናት እናቱ፣
የኑር ማኖሪያቱ የኑር ሱንዱቂቱ፣
ያለችው ሴቶቹን አትወልዱም እንደኔ።
አሏሁመሶሊ………ሲሉ ሰሊውን ያቀብላሉ።
ኣሺቁም በህበረት ይቀበላል።

ባንድነት የተዋበ፣ባብሮነት ጣምራ የተጌጠ የፍቅር ዜማ ይንቆረቆራል።ቅጥሩ ዳግም ይጀድዳል።
ሳር ቅጠሉም በመደድ ይገባል።ትዕይንቱ ልባችንን በፍቅር ይሞላዋል።ያኔ የተጋትነውን ፍቅር በሩሓችን አፀድ ላይ ነግሷል።እናም ከዚህ ወዲያ ፍቅር የታለ ያስብለናል!❤️

tgoop.com/mekbu/2975
Create:
Last Update:

BY Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ

Share with your friend now:
tgoop.com/mekbu/2975

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Find your optimal posting schedule and stick to it. The peak posting times include 8 am, 6 pm, and 8 pm on social media. Try to publish serious stuff in the morning and leave less demanding content later in the day. Informative The Standard Channel Just at this time, Bitcoin and the broader crypto market have dropped to new 2022 lows. The Bitcoin price has tanked 10 percent dropping to $20,000. On the other hand, the altcoin space is witnessing even more brutal correction. Bitcoin has dropped nearly 60 percent year-to-date and more than 70 percent since its all-time high in November 2021. Concise
from us

Telegram Al-inaya Ye Hadra Jemea (Butajira) አል-ዒናያ የሀድራ ጀመዓ ቡታጂራ
FROM American