tgoop.com/menefesawinet/10866
Last Update:
“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።" (ራእይ 21፥5)
#ውድ_የተዋህዶ ልጆች_የቻናሎቼ_ተከታዮች
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወደዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ::
ቀን እና ሌሊትን
ሳምንታትን እና ወራትን
አመታትን እና አዝማናትን እያፈራረቀ በዕድሜያችን ላይ ዕድሜን ጨምሮ ለአዲሱ ዘመን ያደረሰን ከዘመናት በፊት የነበረ ዘመናትንም አሳልፎ የሚኖር ለህላዌው ዘመን የማይቆጠርለት ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለማይነገር ስጦታው እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
አዲሱ አመት ዘመን የምንቀይርበት ብቻ ሳይሆን እኛም ተቀይረን ለክብር የምንበቃበት ይሁንልን።
ብዙዎች ይቺን ቀን ለማየት ናፍቀው ያላዩ በሞት የተጠሩ አሉ።
ብዙዎች በህመም በየ ሆስፒታሉ በየፀበሉ ያሉ አሉ።
በመከራ በስቃይ በችግር ውስጥ ያሉ አሉ እኛን ግን እግዚአብሔር ነብዩ 'በቸርነትህ' አመታትን ታቀዳጃለህ'' (መዝ 65:11) ብሎ አንደተናገረው በስራችን ሳይሆን በቸርነቱ አዲሱን አመት ያሳየን ቸሩ አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።
ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያው መልእክቱ ምዕራፍ 4-3 ላይ
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።”
ብሎ ባለፈው ዘመን ከኖርንበት የኃጢአት መንገድ እንድንመለስ ያስተምረናል::
እኛም ከክፋት፣ከተንኳል፣ከመከፋፈል በጠቃላይ ከክፉ ተግባር ርቀን እግዚአብሔርን የምናስደስትበት ዘመን ያድርግልን።
ዲ/ን ተረፈ ተስፋዬ ነኝ።
@ty1921
@webzema @menefesawinet @kinexebebe @yedawit_begena @amantaakoo @yeberhanljoche @esxifanose
BY መንፈሳዊ ትምህርት ዘኦርቶዶክስ
Share with your friend now:
tgoop.com/menefesawinet/10866