tgoop.com/mez_tewahedo/2589
Last Update:
እንደ ግል መረዳት አቅሜ አኬ ያለውንም ይሄንንም ፅሁፍ እቀበላለሁ። እንዴት ብትለኝ አኬ እመቤታችን የወደቀውን የአዳምን ስጋ ስለያዘች ሞተች ማለቱ ኃጢአት አለባት ኃጢአት ስላደረገች ነው ማለቱ አይደለም ወይም የውርስ ኃጢአት ኖሮባት ነው እያለ አይደለም። የያዘችው ስጋ ግን የአዳም ስጋ ስለሆነ ክርስቶሳዊ ለመሆን በሞት መታደስ አለበት ነው ሞቷ ግን ቅጣት/punishment/ አይደለም ወይም ኃጢአት አይደለም ወይም ኃጢአት አለባትም አያስብልም። ስለዚህ የአኬን ሀሳብ አብዛኞቹ አላገኙትም።
በአንፃሩ ከላይ በፅሁፉ ላይ እንዳለው እመቤታችን የያዘችው ስጋ ሞት የተፈረደበትን ስጋ ሳይሆን አዳም ከመውደቁ በፊት የነበረውን ንጹህ ስጋ ነው የሚለው አገላለፅ በተመሳሳይ እመቤታችን ኃጢአትን አልሰራችም ለማለት የተጠቀሙት አገላለፅ ነው ብዬ አምናለሁ። ምክንያቱም አዳም ከመውደቁ በፊት ከኃጢአት ንጹህ ስለነበር ልክ እንዲሁ እመቤታችንም ንፁህ ናት ለማለት ብቻ የተጠቀሙት አድርጌ እተረጉመዋለው።
ሁለተኛውን ሀሳብ ሙሉ ለሙሉ እንደወረደ የምንቀበለው ከሆነ ግን እመቤታችን መሞት አልነበረባትም ወደ ሚል መደምደሚያ ይወስደናል ምክንያቱም አዳም ከመውደቁ በፊት ሞት ስለማያውቀው ማለት ነው ።
ስለዚህ እንደ እኔ አኬ አልተሳሳተም። ሁለተኛው ሀሳብ ደግሞ ንጽህናዋን ለመግለፅ የገባ አገላለፅ አድርጌ እወስደዋለው።
ምክንያቱም ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእርሷም መድኃኒቷ ስለሆነ።በደረቁ ግን እሷ የያዘችው ስጋ አዳም ከመውደቁ በፊት የነበረውን ንጹህ ስጋ ነው ካልን ያ ስጋ መድሃኒት የሚፈልግ ስጋ አልነበረም። የሚሞትም አልነበረም። ስለዚህ መድሃኒት አያስፈልጋትም ኃይለ አርያማዊት ናት ልንል ነው ። ይህ ደግሞ ስህተት ነው ።
BY የሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ መዝሙሮች
Share with your friend now:
tgoop.com/mez_tewahedo/2589