Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
2578 - Telegram Web
Telegram Web
አስተርዮ ማርያም ❤️‍🩹

"ጊዜ እረፍታ ለማርያም ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና ወረደ ወልድ እም ዲበ ልዕልና ጠሊሳነ ንግሥ ሶቤሃ ከደና”

ሶልያና ባረፈች ጊዜ ክብር የክብርም ክብር የተገባው ወልድ ልጇ ክርስቶስ ከልዕልናው በልዕልና ወረደ እናቱን በጠሊሳነ ንግሥ በዚያን ጊዜ  ሸፈናት።
                   ቅዱስ ያሬድ
          
እንኳን አደረሳችሁ ❤️‍🩹
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡

የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡ እነርሱ ቤተ እስራኤላውያን ነቢዩ እንደተናገረው "ከእንግዲህ አይሹትም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለውም አይጠሩትም" ለእኛ ለአዲስ ኪዳን ልጆች ግን የተሠጠን የሥጋ ወደሙ ቃልኪዳን ነውና ዘላለማዊ ነው::

የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡

ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.

It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡

‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡

ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 10 2009 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ::
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ

ስርዓተ ተክሊል እና ስርዓተ ቁርባን ልዩነትና አንድነት
የማኀበረ ቅዱሳን አንድ እርምጃ

📞ሃሎ: መምህር
ይጠይቁን ምላሽ ያግኙ - የስልክ መስመር

ማኅበረ ቅዱሳን ማንኛውንም ሀይማኖታዊ ጥያቄ ሲኖራችሁ ባዘጋጀናቸው የስልክ መስመር በ +251 111 55 3232 ደውለው ማንኛውንም ጥያቄ መጠየቅ እና መልስ ማግኘት እንደሚችሉ ማህበሩ አሳውቋል

አገልግሎቱም የሚሰጠው በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ነው ( በሌሎች ቋንቋዎችንም እንደሚቀጥል ይታመናል)

በአማርኛና በAfaan Oromo
ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስና አርብ
ስንጨልፍ ፡- ከቃኘው የምሕረት በር /የትንቢተ ዮናስ ማብራሪያ

ከተጣልሁበት ሰማኝ!

‹‹ተጣልሁ፣ እርሱም ከተጣልሁበት ከጥልቁ ሰማኝ፣ ሞት በሲኦል መካከል አሳለፈኝ፣ አንተ ግን ጠበቅኸኝ፡፡ ባሕር ከበበኝ አንተም ያለ መቅዘፊያ ጠበቅኸኝ (ከለልኸኝ)፡፡ አንተ በጥልቁ ቆለፍኽብኝ፣ ወደ ባሕሩም ጣልኸኝ፡፡ወደ ባሕሩ ጥልቅ ወረድሁ፣ እሞት ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ሞት ሰለቀጠኝ፣ አንተ ግን በአፉ ውስጥ ሕያው አድርገህ አኖርኸኝ፡፡ ምንም እንኳን ውኃው ቢሸፍነኝም፣ እታፈን ዘንድ ግን አልተውኸኝም፡፡ ዳሩ ግን መደነቅ ያዘኝ! ህየንተ ሞት ሕይወት ከፍ ከፍ አደረገኝ! ተስፋዬ ሙሉ ለሙሉ ሲሟጠጥ አንተ መለስኸኝ፡፡ ስለዚህ ከጥልቁ ባሕር አንደበቴ በብዙ አመሰገነህ፣ ከባሕሩ ጠልልም በደስታ ለገናናው ስምህ ዘመርኩልህ፡፡ ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም ባለው ታላቅ ቤተ መቅደስ በታቦቱ ተውኩህ (ከአንተ ተለይቼ ወጣሁ)፣ ነገር ግን በመሬት ሥር በጥልቁ ለእኔ መንገድን ስታዘጋጅልኝ አገኘሁህ፡፡ አንተ ከውኆች በላይና በታች፣ በእርሱ ውስጥና ከርሱ ወዲያም በምልዓት አለህ፡፡ አድባራት፣ ቀላያት፣ አቅጣጫዎች ኹሉም ያለማቋረጥ ያለመታከት ያመሰግኑሃል፡፡›› (የምሕረት በር፣ ገጽ 261፣ ዮና.3፡3- ነገሬን ሰማኝ)
--
እኛንም ይስማን!
2025/03/04 12:52:36
Back to Top
HTML Embed Code: