MEZGEBEHAYMANOT Telegram 6626
መዝገበ ሃይማኖት:
ጥያቄ:-ከደረሱኝጥያቄዎች መካከል ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ ሲጠመቅ ሐዋርያት ታቦት ተሸክመው ወጥተው ነበር? በጥምቀት ጊዜ ታቦት ተሸክሞ ይሄድ የነበረ ነቢይ ወይም ሐዋርያ ካለ ስሙን ብትነግሩን?በጥምቀት ጊዜ ታቦት ይዛችሁ ውጡ ተብሎስ ታዟል?ትርጉሙ አልገባኝም

አዘጋጅ በለጠ ከበደ (የጣፈጡልጅ)

መልስ:-ቅድስትቤተክርስቲያን በጥምቀት ጊዜ ታቦት ይዛ የምትወጣው ጌታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ  ሲሄድ ታቦት የያዙ ነቢይ  ወይም ሐዋርያ ስላለ ሳይሆ ጌታች እራሱ ታቦት ስለሚመስል ነው ።የጥያቄ አገባብ በእራሱ ችግር ያለበት ቢሆንም ። ለዚህ ከቀደምት ሐዋርያዊ ሰንሰለት Apostolic Succession አስተምህሮና የፃፉትን ታቦት በሐዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ወስጥ ስላለው አገልግሎት እንመለስበታለን። አሁን አይን መገለጫ የምትሆን ጥያቄ ላይ በጥቂቱ እናተኩር ።

ታቦት የጌታችን የክብሩ መገለጫ ማደሪያው ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ የሚፈተትበት ሰለሆነ ሰለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው ክቡር ደሙ የሚፈተትበት የጌታችን  ምሳሌ የሆነው ታቦት ከቅድስት ቤተክርስቲያን ተነስቶ ወደ ባሕረ ጥምቀት ጌታችን አምላካችን ጥምቀትን ለመመስረት ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስን ባሕረ ለመጠመቅ መሄዱ ያመለክታል

እስቲ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳን መሠረት አድረገን እንመልከት

✥ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታቦት ይመሰላል!

የቀደመችውታቦት ከማይነቅዝና ከማይለወጥ እንጨት የተሠራች ናት ፤ ጌታም (ከዚህበታች በሰፊው እንደምንመለከተው)በኃጢአት ከማትለወጥ  ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍስዋ ነፍስን ነሥቶ በመወለዱ ‹‹ከማይነቅዝ ዕንጨት የተሠራ ታቦት›› ተብሏል፡፡ አንድም ታቦቱ እንደማይነቅዝና እንደማይለወጥ ጌታም ያለመለወጥ (ውላጤሳይኖርበት)፤ ያለመለየት (ፍልጠትሳይኖርበት)በመለኮቱ ንጹሕ እንደሆነ ሰው የሆነ ነውና ‹የማይነቅዝ› ተብሏል፡፡

‹‹ታቦት ማለት መርከብ ማለት ነው› በሚለው አገባብም ደግሞ ጌታችን ታቦት ተብሏል፡፡ ደራሲው ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ታቦተ ሕይወቱ ለኖኅ ፤ ኅብአኒ እግዚኦ በውሳጤከ ስፉሕ ፤ ማየ ኲነኔ አመ ዘንመ አይኅ›› / ‹‹የኖኅ የሕይወት መርከቡ ኢየሱስ ክርስቶስ የኲነኔ ጥፋት ውኃ ዝናም በዘነመ ጊዜ በሰፊው ውስጥህ ሸሽገኝ!››ሲል ተናግሯል፡፡ (መልክአኢየሱስ) 

ጌታችን በኖኅ መርከብ መመሰሉ በመርከቢቱ ውስጥ ያልተገኘ ይሞት እንደነበር በወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ አምላክነት ያላመነም ሞተ ነፍስን ይሞታልና ፣ ወደ መርከቢቱ የገባ እንደዳነ ጌታም ‹‹በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል›› ብሏል፡፡ (ዮሐ.10.9) 
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ‹‹ታቦት በወርቅ ልቡጥ እምኲለሄ ዘግቡር እም ዕፅ ዘኢይነቅዝ ይትመሰል ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ ዘኮነ ሰብአ ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ መለኮት ንጹሕ ዘአልቦ ሙስና፡፡›› ‹‹ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸ በውስጥና በውጭ በወርቅ የተለበጠ ታቦት ያለመለየትና ያለመለወጥ ሰው የሆነ አብን ቃል ይመስልልናል፡፡›› ብሏል፡፡ (ውዳ.ማር.ዘሰንበ.ክር.)

በሃይማኖተአበውም ‹‹ወእም ድኅረ ኮነ ሰብአ ተሰምየ ብእሴ ወመሲሐ ወኢየሱስሃ ወታቦተ ወዐራቄ ወበኲረ ለዘሰከቡ ወበኲረ ለዘይትነሣእ እሙታን ወርእሰ ሥጋሃ ለቤተ ክርስቲያን ወካልኣን አስማት ዘከመዝ ይታለዉ ›› ‹‹ሰው ከሆነ በኋላ ብእሲ ፣ መሲሕ ፣ ኢየሱስ ፣ ታቦት፣ አስታራቂ ፣ ለሙታን በኲር ፣ ከሙታን ወገን ለሚነሡትም በኲር፣ የምእመናን ገዥ ፣ ፈጣሪ ተባለ እንዲህ ያሉ ሌሎች ስሞችም ይነገሩለታል ፤ በብሉይ በሐዲስ ሰው ከመሆኑ በፊትና ሰው ከሆነ በኋላ የተነገሩ ስሞች ሁሉ የርሱ ገንዘቦች ናቸው እርሱ መቼም መች አንድ ነው፡፡›› ተብሎ ጌታ ታቦት እንደሚባል ተጽፏል፡፡ (ሃይማኖተአበው ዘቄርሎስ '1.8)

tgoop.com/mezgebehaymanot/6626
Create:
Last Update:

BY መዝገበ ሃይማኖት

Share with your friend now:
tgoop.com/mezgebehaymanot/6626

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The best encrypted messaging apps As the broader market downturn continues, yelling online has become the crypto trader’s latest coping mechanism after the rise of Goblintown Ethereum NFTs at the end of May and beginning of June, where holders made incoherent groaning sounds and role-played as urine-loving goblin creatures in late-night Twitter Spaces. How to Create a Private or Public Channel on Telegram? fire bomb molotov November 18 Dylan Hollingsworth yau ma tei “Hey degen, are you stressed? Just let it all out,” he wrote, along with a link to join the group.
from us

Telegram መዝገበ ሃይማኖት
FROM American