MIHRET_DEBEBE Telegram 205
ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም!
(እ.ብ.ይ.)

ማንም ሰው ከእውቀት ጋር አልተወለደም፡፡ ሰው ሲወለድ እውቀት የሚያመነጭበትን አዕምሮ ይዞ ነው የተወለደው እንጂ ጥበበኛ ሆኖ አልተወለደም፡፡ ጥበብ ከማሰብ ብዛት፣ ከምርምር፣ ከጥናት፣ ከንባብ የሚገኝ ነው፡፡ ዕውቀት በቅን አስተሳሰብ፣ በበጎ ሕሊና፣ በአዕምሮ ድካም፣ በማሰብ ሂደት፣ የተለያዩ ሃሳቦችን በማስተናገድ የሚመጣ ነው፡፡ እናቱ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሁሉን ያወቀ የሰው ልጅ የለም፡፡ ሁሉም ዕውቀትና ጥበብ፤ ክሂልና ልዩ ሃሳብ የተገኘው በመማር፣ በልምምድና በትጋት ነው፡፡
የሰው ልጅ ሲወለድ ማሰቢያ ማሽን ተገጥሞለት ነው የተወለደው፡፡ ይሄ ማሽን የማይታክት፣ የማይደክም፣ የማይሰለች፣ በቀንም ሆነ በሌት ዕረፍት የሌለው፣ መቼም ከስራው የማይዛነፍ ነው፡፡ ሰው ጤንነት ጎድሎት ቢያብድ እንኳን አዕምሮ የእብድ ሃሳብ ከማመላለስና ከመከወን አያርፍም፡፡ አዕምሮ የረባም ሆነ ያልረባን ሃሳብን እንደግብዓት ተጠቅሞ ውጤቱን የሚሰጥ ልዩ ማሽን ነው፡፡ ጥሩ ውጤት ለማግኘት ግን ጥሩ ግብዓት መስጠት ግድ ይላል፡፡ የስንዴ እህል ወፍጮ ቤት ወስዶ የጤፍ ዱቄት መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ የሰጠነውን አሳምሮ የሚሰጥ ነው ውዱ ሐብታችን (Give and take ነው ጨዋታው)፡፡ ያልሰጠነውን አይሰራም፤ የሰጠነው እንክርዳዱንም ቢሆን እህል አድርጎ አያወጣም፡፡

የአዕምሮ ጥሬ እቃ ሃሳብ ነው፡፡ ቁልፉ ደግሞ ማሰብ ነው፡፡ ማሰብና ሃሳብ ደግሞ በአሳቢው ይወሰናል፡፡ የአዕምሮ ቁልፉ ያለው በአዕምሮው ባለቤት በግለሰቡ እጅ ላይ ነው፡፡ ይሄ ቁልፍ ነው ሰውን በሞራል፣ በስብዕና፣ በምግባር ከፍም ዝቅም የሚያደርገው፡፡ ግለሰባዊ የሃሳብ ልዩነት የመጣው የአዕምሮ ምርቱ የተለያየ በመሆኑ ነው፡፡ የተለያየ አዕምሮ እንደአስተሳሰቡና እንደሃሳቡ ይለያያል፡፡ የሃሳብ ልዩነቱ እንዳጠቃቀማችን ይወሰናል፡፡ አዕምሮውን በርግዶ የመክፈትም ሆነ ጠርቅሞ የመዝጋት ፈቃዱ ያለው እያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ነው፡፡ አዕምሮ እንዲያስብ ማሳሰብ ያለበት ግለሰቡ ነው፡፡ ጥልቅ አሳቢ ሰው የአዕምሮውን ቁልፍ ለመጠቀም የሚፍጨረጨር ነውና፡፡

አዕምሯዊ ብልጽግና የሃብት ሁሉ ቁንጮ ነው፡፡ በሃሳብ ሳይሰለጥኑ፣ በማሰብ ሳይዘምኑ፣ በቅን አስተሳሰብ ከፍ ሳይሉ ውስጣዊ ብልጽግና አይገኝም፡፡ መርማሪ ሕሊና፣ አመዛዛኝ ልቦና፣ የነቃ አዕምሮ ባለቤት መሆን የሚቻለው በሃሳብ መበልፀግ ሲቻል ነው፡፡ በማሰብ የጠለቀ፣ በሃሳብ የረቀቀ፣ በበጎ ስራ የከበረ አዕምሮ የበለፀገ ነው፡፡ በማሰቡ ሃይል፣ በሃሳቡ ጥልቀት የሚመካ ደግሞ በሃሳብ ይበለፅጋል፡፡ በዚህ ዘመን የሚያስፈልገን የበለፀገ አዕምሮ እንጂ ስሙ ብልፅግና የሆነ ፓርቲ አይደለም፡፡ ፓርቲ የሰዎች ስብስብ ነው፡፡ አባላቱ ሳይበለፅጉ የፓርቲያቸው ስም ብልጽግና ቢሆን ስምና ግብር ለየቅል ይሆናል፡፡ ስሙ ይቆየን፤ ግብሩ ይቅደመን!

አዕምሮ የሌሎች ሐብቶች ሁሉ ምንጭ ቢሆንም ሰው ሐብት ፍለጋ ከአዕምሮው ኮብልሎ የውጪውን ዓለም ነው የሚያማትረው፡፡ ራሱን የዘነጋ መቼም ቢሆን ከአዕምሮው ጋር ተስማምቶ መኖር አይችልም፡፡ ከራሳችን ጋር መጣላት የምንጀምረው የራሳችንን ሐብት ዘንግተን ሌላ ሐብት ፍለጋ መባከን ስንጀምር ነው፡፡ ያሰብነው ዓለማዊ ሐብት በእጅ ቢገባ እንኳን ያለአዕምሮ አይደላደልም፡፡ በማሰብ ያልተዘጋጀ አዕምሮ እንግዳ ነገር ሲገጥመው መልስ ለመስጠት ደመነፍሱን ይጠቀማል፤ ስሜቱን ያስቀድማል፡፡ ሰው አይደለም ለቁሳዊ ሐብቱ ቀርቶ ለመንፈሳዊ ሐብቱ ጭምር አዕምሮውን መጠቀሙ ግድ ይለዋል፡፡ የደስታና ሐዘን፣ የእርካታና ርሃብ መሰረቱ አዕምሮ ነውና፡፡ ሰላምም ሆነ ጦርነት በዓለማችን ላይ የሚከሰተው አዕምሮን ከማሰራት እና ካለማሰራት ነው፡፡ ነገር ግን የተሰጠን ሐብት ድንቅ ቢሆንም አብዛኞቻችን የሚደነቁ ስራዎችን ያልሰራነው አዕምሯችንን ባለመበልጸጉ ነው፡፡

አዎ በዚህ ዘመን ድንቁን አዕምሮ በበቂና በብቃት የሚጠቀምበት ሰው እምብዛም ነው፡፡ ጥቂት ሰዎች በተለያየ ዘመን ተነስተው አዕምሯቸውን በሙላት ተጠቅመዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከራሳቸው አልፈው የአለምን አካሄድ የሚቀይር ችግር ፈቺ ሃሳቦችንና ቴክኖሎጂዎችን ፈጥረው ወደመጡበት ተመልሰዋል፡፡ አዕምሮን በሙላት መጠቀም ከራስ አልፎ ለዓለምም ያስተርፋል፡፡ አይደለም ለሰፊው ዓለም ቀርቶ ለአንድ ሰው እንኳን መትረፍ ደስታው ምን ያህል እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ከሁሉ ከሁሉ የአዕምሮ መክሊትህን በሙላት ተጠቀም፡፡ አምላክ የሰጠህ ተጠቅመህ እንድታተርፍበት እንጂ ቀብረህ እንድታባክነው አይደለም፡፡ አውቀህ ባትወለድም በንባብ፣ በምርምርና በማሰብ ሃይል እውቀትና ጥበብን በእጅህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ ያገኘኸውን አዕምሯዊ ሀብት ደግሞ ለዓለም አስቀርተህ ወደማይቀረው መሄድ ትችላለህ፡፡ አዕምሮህን በሙላት መጠቀም ስትጀምር ከመምሰል ዓለም ወጥተህ በመሆን ውቅያኖስ ውስጥ ትዋኛለህ፡፡ መሆን እንጂ መምሰልና ማስመሰል የሌለበት ህይወት የምትጎናፀፈው አዕምሮህ ሲበለፅግ ብቻ ነው፡፡ ከፓርቲህ በፊት አዕምሮህን አበልፅግ፡፡ ያልበለፀገ አዕምሮ የበለፀገ ማንነትም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲን አያስገኝም፡፡

‹‹በማሰብ ያልሰለጠነ፣
በሃሳብ ያልዘመነ፣
በሕሊና ያላደገ፣
በቅንነት ያልበለፀገ፣
መክሊቱን ቀበረ፣
አዕምሮውን ከሰረ፡፡››

ቸር የአዕምሮ ብልጽግና!
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️

tgoop.com/mihret_debebe/205
Create:
Last Update:

BY ዶ/ር ምህረት ደበበ

Share with your friend now:
tgoop.com/mihret_debebe/205

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

The Standard Channel Telegram Channels requirements & features End-to-end encryption is an important feature in messaging, as it's the first step in protecting users from surveillance. Each account can create up to 10 public channels Public channels are public to the internet, regardless of whether or not they are subscribed. A public channel is displayed in search results and has a short address (link).
from us

Telegram ዶ/ር ምህረት ደበበ
FROM American