tgoop.com/mihret_debebe/206
Last Update:
ሦስቱ ልጆች እና ጥቅል በትሮቹ፤
====================
በአንድ ወቅት አንድ አዛውንት ከሶስት ወንድ ልጆቹ ጋር በአንድ መንደር ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ሦስቱም ልጆች ታታሪ ሠራተኞች ነበሩ ፡፡ ነገር ግን ሁል ጊዜ እርስ በርሳቸው ይጣሉ ነበር፡፡ አዛውንቱ አባታቸው አንድ ሊያደርጋቸው ብዙ ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡ የመንደሩ ነዋሪዎች ልፋታቸውን እና ጥረታቸውን ቢያደንቁም በጸባቸው ላይ ይዘባበቱባቸው ነበር፡፡
በእንዲህ ያለ ሁኔታ ዓመታት አለፉ። እናም አዛውንቱ አባታቸው ሕመም ገጠመው፡፡ ልጆቹ አንድ ሆነው እንዲቀጥሉ በተደጋጋሚ ነግሯቸው የነበረ ቢሆንም ግን አልሰሙትም፡፡ ስለዚህ ልዩነቶቻቸውን ረስተው አንድነት እንዲኖራቸው ተግባራዊ ትምህርት ሊያስተምራቸው ወሰነ፡፡ እናም ልጆቹን ጠራቸው ፡፡ እንዲህም አላቸው፦ “አንድ ጥቅል እስር ዱላ እሰጣችኋለሁ እያንዳንዱን ዱላ ለይታችሁ ለሁለት ለሁለት ትሰብሩታላችሁ፡፡ ዱላውን በፍጥነት የሚሰብረው የበለጠ ሽልማት ያገኛል" ልጆቹም ተስማሙ፡፡ አዛውንቱም ለእያንዳንዳቸው የ10 ዱላ ጥቅል ሰጣቸው እና እያንዳንዱን ዱላ ወደ ሁለት እንዲከፍሉ ጠየቃቸው፡፡ ዱላዎቹን በደቂቃዎች ውስጥ ሰበሩ፡፡ ልጆቹ በድጋሜ ማን ቀድሞ እንደመጣ እንደገና በመካከላቸው መጨቃጨቅ ጀመሩ ፡፡
ሽማግሌው “ውድ ልጆቼ ጨዋታው አልተጠናቀቀም አሁን ለእያንዳንዳችሁ ሌላ ጥቅል ዱላ እሰጣችኋለሁ፣ ዱላዎቹን ለያይታችሁ ሳይሆን እንደ ጥቅል መስበር አለባችሁ” አላቸው፡፡
ልጆቹም ተስማምተው የዱላውን ጥቅል ለመስበር ሞከሩ፡፡ ምንም እንኳን የተቻላቸውን ሁሉ ቢሞክሩም ጥቅሉን መስበር አልቻሉም፡፡ የተሰጣቸውን ሥራም በአግባቡ መፈጸም አልቻሉም ፡፡ ሦስቱም ልጆች እንዳልቻሉ ለአባታቸው ሪፖርት አደረጉ፡፡
አዛውንቱ አባታቸውም: - “ውድ ልጆቼ ፣ አያችሁ! ዱላዎችን በነጠላ በቀላሉ ወደ ቁርጥራጭ መቀየር ትችላላችሁ፣ ግን ጥቅሉን መስበር አልቻላችሁም! ስለዚህ አንድ ሆነህ ከቀጠልክ ማንም ሰው ምንም ጉዳት ሊያደርስብህ አይችልም ፡፡ ከወንድሞቻችሁ ጋር ሁል ጊዜ ጠብ ትሆናላችሁ፣ ማንም ሰው በቀላሉ ሊያሸንፋችሁ ይችላል፡፡ አንድነት በመካከላችሁ እጠይቃለሁ፡፡
በመጨረሻም ሦስቱ ልጆች የአንድነትን ኃይል በመረዳት ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሁሉም አብረው እንደሚቆዩ ለአባታቸው ቃል ገቡ፡፡
አንድነት ጥንካሬ ነው
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
BY ዶ/ር ምህረት ደበበ
Share with your friend now:
tgoop.com/mihret_debebe/206