tgoop.com/mihret_debebe/207
Create:
Last Update:
Last Update:
በእንግሊዝ እድሜያቸው ከ18 እስከ 65 በሆኑ ሴቶች ላይ በተሰራው አንድ ጥናት ምንም አይነት ሚስጥር ቢሆን ከ10 ሴቶች አራቱ ሚስጥር መጠበቅ እንደማይችሉ ተመልክቷል፡፡ አርባ አምስት በመቶ (45%) የሚሆኑት በልባቸው የሚያስጨንቃቸውን ሚስጥር ለመገላገል ሲሉ የሚያወጡት ሲሆን ኋላ ላይ ግ ን እንደሚጸጽታቸው ተናግረዋል፡፡ ግማሽ ያህሉም ሚስጥር ላለመጠበቃቸው አልኮል መጠጣትን እንደምክን ያት አቅርበዋል፡፡ ሴቶቹ እንዳሉት ሚስጥሩን ለባሎቻቸው፣ ለፍቅር ጓደኞቻቸው፣ ለእናቶቻቸውና በጣም ምርጥ ለሚሉት ሰው ነው የሚናገሩት፡፡
በዚሁ ጥናት ላይ 83 በመቶ (83%) የሚሆኑት ራሳቸውን ታማኝ አድርገው ቆጥረዋል፡፡ በዚህም ከአራት ሶስቱ ጓደኞቻቸውን በፍጹም እንዳልበደሉ ወይም እንዳልካዱ ይናገራሉ፡፡ በጥናቱ ሌላው አስገራሚ ነገር ሴቶች በሳምንት ቢያንስ ሶስት ሐሜቶችን እንደሚሰሙ ተናግረዋል፡፡ ምንም ሆነ ምን ሴቶች ሚስጥር መያዝ የሚችሉት እስከ 47 ሰዓት (ሁለት ቀን) ብቻ መሆኑን ጥናቱ አመልክቷል፡፡
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
BY ዶ/ር ምህረት ደበበ
Share with your friend now:
tgoop.com/mihret_debebe/207