tgoop.com/mihret_debebe/209
Last Update:
የራስን የማጋነን አባዜ
👉ለፍተን ያገኘነው ነገር እና በስጦታ ያገኘነው ነገር ልዩነት የሚፈጥርብን ለምንድነው? ስለገንዘብ ነው እማወራው። አብዛኛዎቻችን 2ሚሊዮን ብር ሎተሪ ቢወጣልን የምንጠቀምበት መንገድ የተለየ ነው። ቤት እንገዛለን ወይም እንዝናናበታለን ዱባይ ወይ ፓሪስ ቲኬት ቆርጠን አሪፍ የመዝናኛ ፓርክ ውስጥ እናሳልፋለን። ምን አገባን ገንዘቡ ቢያልቅ ለፍተን አላመጣነው። በአለም ላይ በተደረገ ጥናት ሎተሪ የሚደርሳቸው ሰዎች ስለገንዘቡ ግድ እንደማይሰጣቸው እና የትም ቢጠፋ ምንም እንደማይመስላቸው አረጋግጠዋል። ሎተሪ የደረሳቸውን ሰዎችም ህይወት ሲመረመር ተመልሰው የነበሩበት ላይ ተገኝተዋል።
👉ነገር ግን በተመሳሳይ 2ሚሊየን ብር ለፍታችሁ ብታገኙት ምን ታደርጋላችሁ? ወይ ባንክ ታስቀምጣላችሁ ወይ የሆነ ስራ ላይ ታፈሱታላችሁ ወይም ደግሞ ትቆጥቡታላችሁ። ሮልፍ ዶብሊ እንደዚህ ሲል ይጠይቃል ፦ ለፍታችሁ ያመጣችሁትም 2 ሚሊዮን ብር በስጦታ የተበረከተላችሁም 2 ሚሊዮን ብር አንድ ነው። ለፍታችሁ ስላመጣችሁት የሚቀየር ብር የለም ይላል።
👉ይሄ ነገር ብዙዎቻችን ላይ ይሰራል በበአል ቀን በልደት ቀን የምናገኛቸውን ብሮች ቤተሰብ የሚሰጠንንም ብር የትም ለማጥፋት ግድ አይሰጠንም። ይህ የራስን የማግነን አባዜ ኪሳራ ውስጥ ይጥለናል። በነገራችን ላይ እኛ ለፍተን ከምናመጣው ብር በላይ በስጦታ እና በተለያዩ የበአል ዝግጅቶች ላይ የምናገኛቸው ብሮች ብዙ ናቸው። እናም ገንዘብን መቆጠብ እና በትክክለኛ ቦታ ላይ ማዋል አግባብ ነው። ለፍታችሁ አመጣችሁትም ሳትለፉ ብር ብር ነው። ስለሆነም በትክክለኛው እና አግባብ በሆነው ቦታ ላይ አስቀምጡት። መልካም ምሽት እወዳችሁዋለው❤️
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
BY ዶ/ር ምህረት ደበበ
Share with your friend now:
tgoop.com/mihret_debebe/209