tgoop.com/mihret_debebe/210
Last Update:
ሁለቱ ሰካራሞች
👉ሁለት ሰካራም ቀዛፊዎች ለሊት መድረስ ያለባቸው ቦታ ቢኖርም ትንሽ ለማረፍ ብለው ከአንድ መጠጥ ቤት ገብተው መጠጣት ጀመሩ እናም እንደመስከር ሲያደርጋቸው ተነስተው ጉዞ ለመጀመር ወደ ጀልባቸው አመሩ እናም መቅዘፊያቸውን አንስተው ውሀውን ቢከፍሉትም ካሉበት መንቀሳቀስ አልቻሉም። ቡዙ ሰአት ቀዘፉ ነገር ግን ካሉበት አልተንቀሳቀሱም። እሚደርሱበት አላቸው መንገዳቸውን ያውቁታል ጀልባውም አላቸው ነገር ግን አንድ ነገር ዘንግተው ነበር ጀልባዋ የታሰረችበትን ገመድ መፍታት።
👉አብዛኛዎቻችሁ ወጣቶች እንደነዚህ ናችሁ። አላማ አላችሁ፣ መሄጃችሁን ታውቃላችሁ፣ ህልማችሁም ተገልጦላችሁዋል። ነገር ግን ካላችሁበት እንዳትንቀሳቀሱ ያደረጋችሁ የሆነ ነገር አለ። ፀባያችሁ ፣ ልማዳችሁ ፣ ቤተሰብ ፣ አጉል ጉዋደኛ ፣ ሱስ፣ ሴሰኝ ነት። የተለያዩ ነገሮች አሉ። አለማን ብቻ ማወቅ ወዳሰብነው አያደርሰንም። አላማህን ለማስፈፀም እና ወዳሰብከው ለመድረስ መክፈል ያለብህን ዋጋ ሁሉ መክፈል ይኖርብሀል። ለአዚያ እንደነዚህ ሰካራሞች ትሆናለህ። ጀልባ ኖሮህ ምትሄድበትን አውቀህ ፣ መቅዘፊያ ኖሮህ ፣ ውሀው የተረጋጋ ሆኖ ነገር ግን የጀልባዋን ማሰሪያ ባለመፍታትህ ብቻ ትቆማለህ። ስለዚህ የያዘህ ምንድነው? ልቀቀው። ቤተሠብም ይሁን ጓደኛ ወይም ፍቅረኛ ብቻ ማንም ይሁን ካሰብከው አላማ እና ግብ እሚያስቆምህ መሰናክል ከሆነ ህይወት ላይ ምን ይሰራል ? እውነቴን ነው።።
👉የማላደርገውን አልነግራችሁም። ማንም በኔ ህይወት ላይ ዋጋ የሌለው መስሎ ከተሠማኝ እና ከምሄድበት የሚያስቀረኝ ከሆነ እቆርጠዋለው። ብዙዎቹንም ቆርጫቸዋለው። ከምወዳቸው ጀምሮ። ስለዚህ አላማዬን ሁሌም አሳድደዋለው እናም እይዘዋለው። የራቀኝ ቢመስለኝም ከትላንትናዬ አንድ እርምጃ እንደቀረብኩት አስባለው።ዛሬ ላይ የፈለኩበት ቦታ ባልደርስም ከትላንትናዬ አንድ እርምጃ እንደቀረብኩት አውቃለው። የፈጀውን ይፈጃል እንጂ እደርስበታለው። ምክንያቱም ብዙ ዋጋ ከፍዬበታለው ጀልባዬን እያሰረ ያስቸገረኝን ዛሬ ላይ ሚጠቅም የመሠለኝን ነገር ነገዬን እማያሳየኝን ሁሉ በጥሼዋለው። ነገም እየበጠስኩ እሄዳለው።
👉አንተ ከምቾትህ ሳትወርድ ነው አቃተኝ እምትለው ስለዚህ ውጣ ከምቾትህ።
😘@mihret_debebe 😘
😍@mihret_debebe 😍
❤️❤️@mihret_debebe❤️❤️
💚💛❤️
BY ዶ/ር ምህረት ደበበ
Share with your friend now:
tgoop.com/mihret_debebe/210