Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
1936 - Telegram Web
Telegram Web
🎤🎤🎤🎤🎤
ለ10ኛ ክረምት ለ 7 ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የልጆችና የታዳጊዎች የአቅምና ክህሎት ስልጠና በሚያምር እና በሚናፍቅ መልኩ የመዝጊያ እና የሰርተፊኬት ጊዜ አካሂዷል።
🙋🙋🙋

📖 በንቃት፥ በጉጉት እና በናፍቆት የነበራችሁ ቆይታ ባያልቅ ያሰኛል ያስናፍቃል። 

📖 ምሳሌ የሆናችሁ ወላጆች አርዓያነታችሁ ይቀጥል

🖍ሁሌም ድንቅ ናችሁ🖍

በመጨረሻም
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ለቤተሰብ ለሀገር ፍሬ አፍሩ ብለን መርቀን ተመራርቀን አጠናቀቅን።

በብዙ ማማር፥ ፍቅርና አክብሮት የሞላበት ድንቅ ቆይታ!!!

ለምታስቡልን፥ ለተሳተፋችሁ፥ ላበረታታችሁን፥ ከማይንድ ሞርኒንግ ጎን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ታላቅ ነው!!🙏🙏🙏

@mindmorning
የስልጠናው ርዕስ፣ መዝጊያና መክፈቻ

የፊታችን ቅዳሜ ጳጉሜ 02/2016 ዓ.ም.

መግቢያ ፣ በነጻ -አያምልጥዎ
ቦታው ፣ መገናኛ ስለሺ ስህን ህንጻ፡ ቢሮ ቁጥር ፣ 805
ሰዐት: 8:00-11:00
መዝጊያና መክፈቻ

አዲስ ዓመት ሲመጣ ትዝ የሚለኝ ነገር ስንቅና ትጥቅ ነው ። ሆኖም ሰንቅም ትጥቅም ምግብ አይደሉም። ማንነትና ዝግጁነት እንጂ። ማንነት መፈተሽ አለበት። ስንቅም ይቋጠርለታልና። መሸከም የሚችለውን ለማለት ነው። የማይችሉትን መሸከምም ሆነ የማይበቃን መታጠቅ የትም አያደርስም። እንኳን አንድ ዓመት ።
🖐 በእርግጥ ልምድ ያላቸው ለአመታት የሚሆን ይሰንቃሉ ።ይታጠቃሉም። ለዚህ ደግሞ ራሳችንን እንድንፈትሽ አዲስ አመት ሁሌ ይመጣል ፡ አይቀርም። አንድ ደንበኛዬ ራስን መፍጠር እንጂ ራስን ወደኋላ መፈተሽ ምን ያደርጋል ያለኝን አልረሳውም። ማንነትን ማወቅ ለስንቅም ፣ለትጥቅም አያስፈልግም እንደማለት።

🖐አንድ ፎቅ ላይ ሌላ ተጨማሪ ወለል ለመጨመር መሸከም የሚችለውን ሳናውቅ ይቻላልን ስለው አሁንም ክርክሩን ቀጠለ። መቸስ ክርክር ይቻላል ህይወት እሆንልንም እንጂ። ይህ የአዲስ አመት የመባቻ ጊዜ ማረፊያችን ነው። በር መዝጊያችን። ብዙ ድርጅቶች ቆጠራ ላይ ነን እንደሚሉት። ከዛም በር እንከፍታለን። አቅማችንን መዝነን። በር መክፈትና መዝጋት ለሚያውቅ አራት ዋና ዋና መርሆች ይኖሩታል ። እንደ ስንቅም ይገለገልባቸዋል።

👍የለውጥ አስተሳሰብ ወይንም የማደግ መርህ የህይወቱ መንገድ ይሰጠዋል።

👍ወድቆ መነሳት የስንቁን መጠን ይወስንለታል ። ትጥቁንም ከፍ ያደርግለታል።
👍ሌሌችን ተጽዕኖ ውስጥ መጣል ብቻ ሳይሆን ማበርከትም ይሆንለታል።

👍ከዛም የሁሌ ተማሪ ስለሚሆን ሙሉነትን ይጎናጸፋል። በር እንዝጋ!! በር እንከፈት !!

ስንቅ የሌለው ህዝብ መድረሻው አይታወቅም!!!
አዲሱ ዓመት የፍሬ ይሁንላችሁ !!!!!ይሁንልን!!!!!


ቪሌጅ ኢትዮጵያ -የወላጅነት አካዳሚ
Village Ethiopia-Parenting Academy
@ Mind Morning
የዚህ ሳምንት የወላጅነት በልዩነት ስልጠና ርዕስ
ሆን ብሎ መሰጠት
በማይንድ ሞርኒንግ ቢሮ መገናኛ ስለሺ ህንፃ 8ኛ ወለል በ0970414243 መደወል ይችላሉ። ቅዳሜ 04/01/2017 መግቢያ በነፃ ሰዐት ከቀኑ 9:00-12:00
🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ!!🎉🎉🎉

2017 መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!😍🌞😍🌞😍🌞😍🌞

ማይንድ ሞርኒንግ
የተወደዳችሁ ደንበኞቻችን ለዛሬ ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም የወላጅነት ስልጠና የማይኖር መሆኑን በአክብሮት እገልፃለሁ። መልካም የመስቀል በዓል!!
ለደንበኞቻችን ሁሉ አሁንም በኢሬቻ ምክንያት ለነገ ቅዳሜ አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን። መልካም በዐል
ጀምሮ የማቋረጥን፣ 🙈 የመሰላቸትን፣ 😳ያለመጨረስን ችግር የሚፈታ

👍 የልጆችዎን ንቃትና ስኬት የሚያስቀጥል የበጋ ስልጠና!!

ምዝገባ ጀምረናል!! በማይንድ ሞርኒንግ!

👐 የልጆች (የተማሪዎች) የመስከረም መነቃቃት፣ ትጋትና ፍላጎት አመቱን ሙሉ ቢዘልቅ የማይወድ አለን?
👌 ልጆችዎን በተለያየ መንገድ ማብቃት ይህን ውጤት ያመጣዋል!!

🖐 ማይንድ ሞርኒንግ ደግሞ ልጆችን በማብቃት እና የተለያዩ ክህሎቶችን በማስታጠቅ ብዙ ልምድ አለው፣ ፍሬም አፍርቷል፡፡
✍️ ስለሆነም ልጆችዎ ሳይጨናነቁ፣ ሳይሰላቹ፣ ውጤታማ ሆነው፣ በዚሁ መጀመሩበት ንቃት እንዲቀጥሉ ማይንድ ሞርኒነግ ባዘጋጀው ስልጠና ከጎንዎ ነን!!

🫵 ይደውሉ መረጃ ይውሰዱ፣ ያስመዝግቡ፣ ቦታ ይያዙ
👊 ልጆችዎ በህይወት ገጻቸው እና በትምህርታቸው ብቁ የሚሆኑበት ስልጠና!!

🤙 0912 33 30 20
🤙 0970 41 42 43

መገናኛ ስለሺ ስህን ህንፃ 8ኛ ፎቅ

@mindmorning
2025/02/16 10:42:33
Back to Top
HTML Embed Code: