tgoop.com/muslimprincess2024/138
Last Update:
10 ምክር ለእንስቶች .
እህቴ ጀግና ሴት ነኝ ካልሽ
1ኛ: ከሚያናግርሽ ወንድ ሁሉ ጋር አትሳቂ። አንዳንዴ መኮሳተር ጥሩ ነው። ድንበር የሌለው ፈገግታና ሳቅ ከመንገድሽ ያዘገይሻል።
2ኛ: በኢስላምሽ ጉዳይ አትደራደሪ፣ ምክንያቱም ኢስላምሽ ከህይወትሽ በላይ ውድ ነው። አንችን ከመከራ፣ ከስቃይ አውጥቶሻል። ከነ ህይወትሽ በሚቀብሩሽ ሰኣት ‘ለምን!?’ ብሎ ጠበቃ ሆኖ ለነፃነት አብቅቶሻል።
3ኛ: በእምነትሽ አትፍሪ፣ ረጋ ብለሽ ተጓዥ። ባለሽ ነገር ተብቃቂ። ኩርምት አትበይ። ከእምነትሽ ያፈነገጠ አለባበስና ፋሽን ተከታይ አትሁኚ አደራ። ኢስላምሽ ሰማያዊ እንጂ ዘመናዊ አይደለም።
4ኛ: ወደ ዝሙትና ወደ ወንጀል ከሚጋብዙ ነገሮች ሁሉ ራቂ። ‘ኢስላማዊ’ የሚለው ስም እንዳይሸውድሽ አደራ። ኢስላማዊ ፊልም፣ ኢስላማዊ ነሺዳ።
5ኛ: በቦርሳሽ ውስጥ የኮስሞቲክስ ነጋዴ ይመስል የቻይና እቃ ይዘሽ አትዙሪ። ይልቁንስ የእምነትሽን መመሪያ ቁርኣን መያዝን አትርሺ። ቦርሳሽ ውበት የሚኖራት ያኔ ነው።
6ኛ: ድንግልናሽን ጠብቂው። ለምታገቢው ብቻ አስቀምጪ። አላህ ካልፈቀደው ነገር ሁሉ ራቂ። ያኔ ደስተኛ ህይወትን ትኖሪያለሽ።
7ኛ: ሁሌም የምትሰሪውን ስራ አስተውይው። ሙስሊም እንስት የምትፈፅመውን እንጂ አትስሪ።
8ኛ: ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! አንቺኮ ምርጥ ነሽ። ወንድ ሁሉ ይፈልግሻል። የሚያገባሽ እንዴት ታድሏል። ተፈላጊ መሆንሽን አትርሺ። ግን ለሚያገባሽ እንጂ ለሚፈልግሽ ሁሉ አትገኚ።
9ኛ: ሁሌም እምነቴ ኢስላም ነው ብለሽ ስታስቢ በሀሴት ልትረኪ ይገባል። ምክንያቱም የጀነት እጩ ተወዳዳሪ ነሽ። ውድድሩን ለማሸነፍ መዝሀበ ሰለፍን ተከተይ አደራሽን።
10ኛ: የመጨረሻው መልእክቴ - ተውሒድና ሱናን ባገኘሽው አጋጣሚ ሁሉ ለእህቶችሽ ስበኪ። ያኔ ውበትሽ ይደምቃል።
Copy
ምክሩ ለኔም ለናንተም ነዉ::አላህ ባወቅነዉ ተጠቃሚዎች ያድርገን!!አሚን!!
BY አማኟ ንግስት
Share with your friend now:
tgoop.com/muslimprincess2024/138