tgoop.com/muslimprincess2024/141
Create:
Last Update:
Last Update:
👉🏼ስለ ራሳችን በገለፅንላቹ ልክ እንጂ አታውቁንም!
• መች አወቅካትና እንዲህ ነች ብለህ ለመናገር ደፈርክ..?
ሳቋ እንደሆነ ስለሷ ሁሉንም ነገር አይነግርህም።
...ጨዋታ አዋቂነቷ መግባባቷ፣ ሰው አክባሪነቷ ልቧ... የተሸከመውን አያሳይህም።
እሷ እኮ.... ብሎ ለመናገር ድፍረት ከየት አመጣኸው?
...ሰው ልቡ ከውቅያኖስ ይጠልቃል....!
•አየህ ልቧ ሀገር ቢሆን ኖሮ ሁሉንም አንደላቆ አሳርፎ ገና ብዙ ማኖር...የሚችል ይሆን ነበር....
የሰው ልብ ብዙ ሸክሞች የሚዘዋወሩበት በሞት ብቻ የሚዘጋ ወደብ ነው...
ሁሉም በልቡ ችሎ የሚኖረውን.አታውቅም።
ባየሀትና፣ ባሳየችህ ልክ አትገምታት፣ አትደምድማት።
...የልቧን ስትገልጥልህ እንዳትደነግጥ...እንደው እሷ እኮ..? ብለህ አታሸሙርባት። አንቺዬ ሰላም ለልብሽ ይሁን!
.....🌺የኔ ሴት🌹
✍ Kewni
https://www.tgoop.com/muslimprincess2024
BY አማኟ ንግስት

Share with your friend now:
tgoop.com/muslimprincess2024/141